input
stringlengths
1
130k
ሊባኖሶች ጠቅላይ ሚንስትራቸዉ ያሉበትን ሥፍራና ሁኔታ ለማወቅ ኃያላንን ሲማፀኑ ፈጣሪያቸዉን ሲፀልዩ ሰንብተዉ ትናንት ማታ ተንፈስ አሉ።
የመኖችን ብዙ ያስጨነቀዉ የጦርነቱ አልበቃ ብሎ በኮሌራና ረሐብ ብዙ ወገኞቻቸዉ ማለቃቸዉ ነዉ።
ቀጠሮች ያየር የምድር የባሕር ሕልቅታቸዉ ተይዞ እስትፋሳቸዉ በቱርክ እና ኢራኖች ደግነት ላይ ከተንጠለጠለች አምስተኛ ወራቸዉ።
ከኢትዮጵያዉያን ክርክር እስከ ቴሕራኖች ዛቻ ከየመኖች እልቂት እስከ ሊባኖስ ሥጋት ምክንያት የሆነች አንድ ትልቅ ግን በትንሽ ወጣት የምትመራ ሐገር አለች።
ሳዑዲ አረቢያ የአረቡ ዓለም ዋና በጥባጭ ኃይል ከመሆን አፋፍ ላይ ናት ይላል የስለላዉ ድርጅት ዘገባ።
የጀርመን የዉጪ መርሕ ማሕበረሰብ የተሰኘዉ ተቋም ባልደረባ ሴባስቲያን ዞንስ ግን የሐገራቸዉ የስለላ ድርጅት ጥቆማን ብዙም የሚቀበሉት አይመስሉም።
ዞንስት እንደሚሉት ወጣቱ ልዑል በተለይ በእድሜ አቻዎቻቸዉ ዘንድ እንደ ለዉጥ አራማጅ ነዉ የሚታዩት።
ልዑሉ ሲናገሩ ግልፅ መልዕክት ያስተላልፋሉ ነባሩን ሥርዓት ተቺም ናቸዉ።
በሳዑዲ አረቢያ የእስከ ቅርብ ዘመን ታሪክ ሐራም ወይም አይኔ ይመስል የነበረዉን አስተሳሰብ ጥሰዉ ሴቶች መኪና እንዲነዱ ፈቅደዋል።
የሚወስዱትን እርምጃ ይቃወማሉ የሚባሉ አክራሪ የኃይማኖት መሪዎችን ሰብሰበዉ አስረዋል።
ጂዳ ሳዑዲ አረቢያ የሚኖረዉ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክም ይሕን ማስተዋሉን ይመሰክራል።
አልጋወራሹ የመከላከያ ሚንስትርነቱን ሥልጣን በ እንደያዙ መጀመሪያ የወሰዱት ትልቅ እርምጃ የመንን መዉረር ነበር።
እርግጥ ነዉ የመን እንደሐገር ከቆመችበት ጊዜ ጀምሮ የሳዑዲ አረቢያ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሐብታዊ ጣልቃገብነት ተለይቷት አያዉቅም።
ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን ግን ያያት አጎቶቻቸዉን ጥንቃቄ የተሞላበት ሥልት ጥሰዉ አሁን የመንን ካየር እና ከባር የሚቀጥቅጥ ጦር ነዉ ያዘመቱት።
አዲሶቹ የሳዑዲ አረቢያ ገዢዎች ጦር ያዘመቱበት ምክንያት እንደ አያት አጎቶቻቸዉ በሶሻሊስቶች የሚደገፉ ሪፐብሊካዊያን አስግተዋቸዉ አይደለም።
የመንን እንኳ በቅጡ ያልተቆጣጠሩት ሁቲዎች ለትልቋ ሳዑዲ አረቢያ የሚያሰጉ ሆነዉ አይደለም።
በአካባቢዉ ፖለቲካ የተበለጡ ሥለመሰላቸዉ ነዉ ይላል የጀርመኑ የስለላ ድርጅት ማስታወሻ።
በአካባቢዉ ፖለቲካ ላለመበለጥ የፈለገዉ ኪሳራ ቢያመጣም ወታደራዊ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ኃብታዊ እርምጃ ለመዉሰድ መቁረጣቸዉን የሚያረጋግጥ ነዉ።
የሳዑዲ ገዢዎች በፖለቲካ ይበልጡናል ብለዉ የሚፈሩት የረጅም ጊዜ የአረብ ጠላት የምትባለዉ እስራኤልን አይደለም።
እንደነሱዉ ሁሉ በእስልምና ግን በሺዓ ሐራጥቃ የሚመሩትን ኢራኖችን እንጂ።
ያም ሆኖ ሪያዶች ለሰወስት ወራት አቅደዉ የተሞጀሩበት ጦርነት እነሆ ሰወስተኛ ዓመቱን ሊደፍን አራት ወር ቀረዉ።
በሪያዶች ግፊት የየመኑን ወረራ እኩል ከጀመሩት የአካባቢዉ መንግሥታት አንዷ የሪያድ ጠላት ከሆነች አምስተኛ ወሯን ያዘች።
የዶኻዎች ጥፋት ጋስ እየተዛቀ ዶላር የምታፈስባት ትንሽ ሐገራቸዉን ከሪያዶች ፍላጎት እና ፍቃድ ዉጪ ከፍከፍ ማድረጋቸዉ ነዉ።
የቢን ሠልማን ቤተሰቦች ቀጠርን መቅጣት ማግለላቸዉን የተሐድሶ ለዉጥ እርምጃችን ሊሉት በርግጥ አይቃጣቸዉም።
አልጋወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማን ይመሩታል የተባለዉ የፀረ ሙስና ኮሚቴ በቅርቡ ልዑላንን ሚንስትሮችን የጦር አዛዦችንን እና ቱጃር ነጋዴዎችን ጠራርጎ አስሯል።
ድጋፉ ምክንያታዊ የሚሆነዉ ግን አሳሪዎቹ ከታሳሪዎቹ ይበልጥ ከሙስና የፀዱ መሆናቸዉ ሲረጋገጥ ነዉ።
ብዙ ታዛቢዎች እንደተስማሙበት ወጣቱ አልጋወራሽ በአንድ ድንጋይ ብዙ ወፍ ነዉ የገደሉት።
ሥልጣን ሊቀናቀኗቸዉ የሚችሉ የንጉስ አብደላሕ ልጆችን አይነት ልዑላንን እና ደጋፊዎቻቸዉን አሽመድምዶ መጣል ቀዳሚዉ ነዉ።
ልዑላኑም ሆኑ ቱጃሮቹ የሚቆጣጠሩትን ሥልጣንና የሥራ መስክ ለታማኞቻቸዉ በማደላደል የታዛዦቻቸዉን ቁጥር ማበራከት ሁለት።
ለወደፊቱም ቀና የሚል ተቺ ተቀናቃኛቸዉ ካለ እነሱን አይተሕ ተቀጣ ሌላዉ ምክንያት ነዉ።
ጋዜጠኛ ነብዩም ግልፅ የሆኑ ነገሮች የሉም ከማለት ሌላ ብዙም የሚለዉ ያለ አይመስልም።
ሳዑዲ አረቢያ ሰነዓ ቤተ መንግሥት ልትዶላቸዉ የምትዋጋላቸዉ የየመኑ ፕሬዝደንት አብድረቦ መንሱር ሐዲ ልጃቸዉ እና ሚንስትሮቻቸዉን አስከትለዉ ሳዑዲ አረቢያ ከመሸጉ ቆይተዋል።
ባለፈዉ ነሐሴ ወደ አደን የመን ለመሔድ ከሪያድ ተነስተዉ ነበር።
አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ግን የፀጥታ ኃይሎች ከሳዑዲ አረቢያ እንዳይወጡ አገዷቸዉ።
አረብ ኒዉስ አንድ የየመን ጦር አዛዥን ጠቅሶ ባለፈዉ ሳምንት እንደዘገበዉ ሐዲ እና ተከታዮቻቸዉ ሪያድ ዉስጥ በቁም ታስረዋል።
ሥልጣን ለቀቅኩ ካሉ በኋላ አንድ ሳምንት ጠፉተዉ ትናንት ቴሌቪዢን ፊት ቀርበዉ ለሥልጣናቸዉም ለሕወታቸዉም ለሐገራቸዉም ኢራንን ወነጀሉ።
ሁለቱ የመካከለኛዉ ምሥራቅ ኃያል ሙስሊም ሐገራት ቀጥታ ዉጊያ ለመግጠም መፈለጋቸዉን ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች ይጠራጠራሉ።
ጦርነት ከተጫረ ግን ሴባስቲያን ዞንስት እንደሚሉት ለአካባቢዉም ለመላዉ ዓለምም ትልቅ ጥፋት ነዉ።
በኢራንና ሳዑዲ አረቢያ ቀጥታ ዉጊያ ቢገጥሙ ደግሞ መካከለኛዉ ምሥራቅን በሙሉ ያጋያዋል።
ከጦርነቱ የአካባቢዉም ሆነ ከአካባቢዉ ዉጪ ያሉት ኃይላት የሚጠቀሙ አይመስለኝም።
አልጋወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማን የጀመሩት የተሐድሶ ለዉጥ በርግጥ የብዙዎችን ድጋፍ አትርፏል።
ከዉስጥም ከዉጪም ባንድ ጊዜ ብዙ ቁልፍ መነካካታቸዉ ግን የተሐድሶ ለዉጥ ሳይሆን ሥልጣን የመጥቅለል የኃያልነት እና ምናልባት ያለማወቅ ሥሕተት እንዳይሆን ያሰጋል።
ምናልባት ዋሽግተኖችን አይዞሕ አይዞሕ አምነዉ ከሌላ ጦርነት ከተሞጀሩ ደግሞ መዘዙ መመለሻ ማግኘቱ አጠራጣሪ ነዉ።
ዳርክኔት ሐምሌ ቀን ዓም ዴቪድ ዓሊ ሶምቦሊ በጀርመኗ የሙኒክ ከተማ ውስጥ ዘጠኝ ሰዎችን ተኩሶ በመግደል በመጨረሻ እራሱን አጠፋ።
የኢትዮጵያውያኑ አስከሬን የነበረበት መቃብር የተገኘው ከሲርጥ ከተማ አቅራቢያ ነው።
በወቅቱ የኢትዮጵያ የመንግሥት ቃል አቀባይ የነበሩት አቶ ሬድዋን ሁሴን በታጣቂዎቹ የተገደሉት ሰዎች በእርግጥ ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው ማረጋገጥ እንዳልቻሉ ተናግረው ነበር።
በሊቢያ የሚደረገው ምርመራ እና ዓለም አቀፍ ሕጋዊ ሒደት ከተጠናቀቀ በኋላ አስከሬኖቹ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚላኩ የወንጀል ምርመራ ክፍሉ ያሰራጨው መረጃ ይጠቁማል።
ካብ አዲስ አስመራ ይዘት ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የጀርመን የተለያዩ የብዙሃን መገናኛዎችም የእዉቁን የሥነ ጽሑፍ ሰዉ ሥራዎች እያነሱ ደራሲዉን በመዘከር ላይ ይገኛሉ።
ከሥነ ጽሑፍ ሌላ በማሕበራዊና ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የሰላ ብዕራቸዉን በመሰንዘራቸዉ ይታወቁ የነበሩት ጉንተር ግራስ የፖለቲካ ፈጣሪም ተደርገዉ ይታዩ ነበር።
ጉንተር ግራስ በጎርጎረሳዉያኑ ዓ ም በዛሬዋ የፖላንድ የወደብ ከተማ ዳንትዚግ ዉስጥ ነዉ የተወለዱት።
በዚሁም ሥነ ጽሑፋቸዉ በጎርጎረሳዊዉ ዓ ም የሥነ ጽሑፍ ኖቤል ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል።
ከቪሊ ቭራንት ጋር በጋራ በመሥራት ያበረከቱትም ድርሻ የሚደነቅ ነው።
በሌላ በኩል ጉንተር ግራስ እንደ አንድ የተከበረ ታላቅ ምሑር በጀርመንና በአዉሮጳ በተካሄዱ ክርክሮችና ዉይይቶች ላይ የበኩላቸውን አሻራ ያሳረፉ ደራሲም ነበሩ።
በጉንተር ግራስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ከብዙሃኖች ጋር በጋራ ጥልቅ ሃዘን ላይ እንገኛለን።
ጉንተር በዚህ ጉዳይ ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ ሁሉ ነገር የተከሰተዉ እያወቅን ነዉ ነበር ያሉት።
እስካሁን ድረስ የሆነ መንፈስ ጀርመኖችን ጥፋት እንዲሰሩ ያታለላቸዉ ወይም የገፋፋቸዉ ተደርጎ ነው ሲቀርብ የነበረው።
በዚያን ጊዜ በነበረኝ የወጣትነት አመለካከቴ እንኳን ይህ ልክ እንዳልሆነ አዉቅ ነበር።
ግራስ የወግ አጥባቂ የቀን ክንፍ ቡድኖችን ወይም ናዚዎችን ባሰሙዋቸው ንግግሮቻቸው ከመተቸት ወደ ኋላ ብለው አያውቁም ነበር።
ስለ ታዋቂዉ ጀርመናዊ የሥነ ጽሑፍ ኖቤል ተሸላሚ ጉንተር ግራስ ያወሳንበትን መሰናዶ የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።
የካርቱም ገዢዎች ሱዳን በ የራስዋን ሕዝባዊ አመፅ አስተናግዳለች በማለት የጥያቄ ንግግሩን ትኩረት ለማስቀየስ መጣጣራቸዉ አልቀረም።
አቅጣጫ ለማስቀየር ሲጣጣሩ አቅጣጫ የጠፋባቸዉ የካርቱሙ ጨቋኝ ጨካኝ ግዙፍ ዋርካ ተገነደሰ።
የሱዳኖች ብሶት የምጣኔ ሐብቱ ድቀትና የፖለቲካዊዉ ኪሳራ ሰበብ ምክንያት ብዙ ዉስብስብ የኃያላን ክርን የቱጃሮች መዳፍ የሚጫጨነዉ መሆኑ በርግጥ አያጠያይቅም።
የጎላዉ ግን አል በሽር ሊቢያን ከመጎብኘታቸዉ ከ ዓመት በፊት ናይቫሺ ኬንያ ላይ የፈረሙት ሰነድ ነበር።
እንደአብዛኛዉ አምባገነን ገዢ ሰላም በማስፈን ሰበብ የጠቀለሉት ሁለት አጫጭርና ስልጣን ላይ የመቆያ ስልት ነበር።
የመጀመሪያዉ ምዕራባዉያን በተለይም ዋሽግተኖች የሚፈልጉትን ስምምነት በመፈረም ከዋሽግተኖች የሚገኝ ፖለቲካዊና ምጣኔ ሐብታዊ ፍርፋሪ ካለ መቃረም ነዉ።
የምዕራቦች ከደገፉት የዳርፉር አማፂያን ከጠፉ ቃዛፊን መሰል ጠላቶች ከተደካሙ የእኒያን ጠንካራ ጄኔራል ጠንካራ ክንድ ማን ይዳፍራል ነበር ድምር ስሌቱ።
እንዲያዉም የዳርፉር ጣጣ ያን ብዙ የተለፋለትን የአል በሽርን ስልጣን ሊያስጠብቅ ቀርቶ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ከመከሰስ አንኳ አላዳናቸዉም።
አልበሽር በተገኙበት እንዲታሰሩ የዘ ሔጉ ፍርድ ቤት ዋራንት በቆረጠባቸዉ በሁለተኛ ዓመቱ ደቡብ ሱዳኖች ነፃነታቸዉን አወጁ።
በዘመናት ጦርነት የላሸቀዉ በማዕቀብ በመገለልና በሙስና የጫጫዉ ምጣኔ ሐብት የሚደጎመዉ በአብዛኛዉ ከዛሬዋ ደቡብ ሱዳን ከሚወጣዉ ነዳጅ ነበር።
ደቡብ ሱዳን የነዳጅ ጉርጓዶችዋን ይዛ ከሱዳን ስትገነጠል የሱዳን ምጣኔ ሐብት ሙገሌ እንደተመታ በሬ ባጭር ጊዜ ተሽመደመደ።
የቀድሞ አማፂዎችን ከመደበኛዉ ፀጥታ አስከባሪ ጋር ለመቀየጥ እንረዳችኋለን ቀጠሉ የካርቱሙ ጄኔራል ።
አል በሽር ትሪፖሊ ላይ ያሉትን ከማለታቸዉ ከዘጠኝ ወራት በፊት የኑሮ ዉድነት የከበደዉ ሕዝባቸዉ የቀሰቀዉን አመፅ ለጊዜዉ ደፍልቀዉ ነበር።
የአል በሽር የርዳታ ተስፋ እንደ ፓሪስ ለንደን ዋሽግተን መሪዎች ቃል ሁሉ ሸፍጥነቱ ገሐድ ከወጣ ከረመ።
የነሙስጠፋ የመሪነት ብቃት ሐብታም ሰፊ ስልታዊቱን ሊቢያን የአሸባሪዎች መፈልፈያ የወሮበሎች መናሐሪያ የጦር አበጋዞች መፈንጪያ በማድረጉ ጥፋት ከተረጋገጠ ዓምስት አለፈዉ።
አመፁ ትንሺቱ ከተማ በመጀመሩ ምክንያቱም የዳቦ ዋጋ ንረት ስለነበረ የካርቱም ገዢዎችን ማዘናጋቱ አልቀረም።
ሰልፈኛዉም የዳቦ ፉል ዋጋ ንረትን ከመቃወም አልፎ ገዢዎቹን ያወግዝ ነፃነቱን ይጠይቅ ገባ።
የዑማ ፓርቲ መሪ ሳዲቅ አልመሕዲ ለሕዝባዊዉ አመፅ ወጥ ፖለቲካዊ ዓላማና ግብ አበጁለት።
በጣም አስፈላጊዉ ጥያቄ ይሕ ስርዓት ተወግዶ በብሔራዊ የሽግግር መንግስት መተካት አለበት።
የሽግግር መንግሥቱ ኃላፊነትም ሰላም ማስፈን ሰብአዊ መብት ማስከበርና ነፃነትን ማረጋገጥ መሆን አለበት።
የሕዝቡን ችግር የሚያቃልል የምጣኔ ሐብት እና የለዉጥ መርሐ ግብር መንደፍ ሕገ መንግሥት የሚያረቅ ብሔራዊ ጉባኤ መጥራት አለበት።
አል በሽር አመፁን ለመደፍለቅ ሰልፈኞችን ያስገድሉ ያስደበድቡ ያሳስሩ ገቡ።
የሰላሳ ዘመን ብሶት ያማረረዉን ሕዝብ አመፅ መግታት ግን አልቻሉም።
የሕዝባዊዉ አመፅ መጠናከር ደራሹ ሕዝባዊ ጎርፍ ጠራርጎ እንዳይወስዳቸዉ የፈሩትንም የአልበሽርን መንበር ለመቀማት የሚያደቡትንም ወይም ለሕዝብ የወገኑትንም ጄኔራሎች ባንድ አቆማቸዉ።
እኔ አሁን እንደ መከላከያ ሚንስትርና እንደ የፀጥታ ላዕላይ ምክር ቤት የበላይ ኃላፊ የማስታዉቀዉ ነገር ይሕን ስርዓት ከስልጣን ማስወገዳችንን ነዉ።
እርግጥ ነዉ የሱዳን ሕዝብ ለአደባባይ ሰልፍ አመፅ እንግዳ አይደለም።
በተለይ በ ያደረገዉ የጥቅምቱ አብዮት በዘመኑ የነበሩ አምባገነን ገዢን አስወገዷል።
ይሁንና ከየስልጣናቸዉ የሚወገዱትን አምባገነን ገዢዎች የሚተኩት አዳዲስ የጦር መሪዎች በመሆናቸዉ የአድማ አመፁ ዉጤት ዉል እንደሳተ ነዉ።
አምና ሚያዚያም አልበሽርን ከስልጣን ያስወገዱት የጦር ጄኔራሎች ሥልጣኑን ጊዚያዊ በሚል ሽፋን ለራሳቸዉ መያዛቸዉ ታሪክ ራሱን የመደገሙ ማረጋገጪያ ነበር።
አመፅ አድማዉ ጠንከር ጠጠር አድመኞቹ በርከት መፈክራቸዉ ደገምገም ሲል እኒያ ቀጭን ጠይም ሸበቶዉ ጄኔራል የርዕሠ ብሔርነቱን ስልጣን ለቀቁ።
በዕለታት ዕድሜ የ ዓመቱ የኃይለኞች ኃያለኛ በተረኛ ኃይለኛ ከስልጣን ተወገዱ።
ጄኔራሉ እንዳሰቡት የመንታዉ ስልት ጥቅል ዉጤት ሰልፈኛዉ ፈርቶ በጊዜ ሒደት ተሰላችቶ ወይም በመሪዎቹ ላይ እምነት አጥቶ ይበተናል ነበር።
ጄኔራል አብዱል ፈታሕ ቡርሐን ያዘመቱት ጦር ሰላማዊ ሰዎችን ለመግደል ማቁሰሉ የሰልፈኛዉን መሪዎች ወነጀሉ።
ስለዚሕ በፈጣሪ ፊት በሕዝባችን በጦራችንና በአብዮታችን ፊት የሚከተሉትን የመወሰን ኃላፊነት አለብን።
ስምምነቱ እንዲቀጥል ተገቢዉን ድባብ ለመፍጠር ይቻል ዘንድ ድርዱን ለ ሰዓታት ማቋረጥ።
የቁጭታ አድማ በሚደረግባቸዉ አካባቢዎች የቆሙ መከላከያ አጥሮችን በሙሉ ማስወገድ።
በነዳጅ ዘይትና በሌሎች ሸቀጦች እጥረት ችግር ላጋጠማቸዉ ግዛቶች ሸቀጦቹ እንዲደርሱ የተዘጋዉን የባቡር መስመር መክፈት።
ሰልፈኛዉን አደራጆቹን ሌላዉ ቀርቶ ሐኪሞችን ሳይቀር እያሳደደ ያስር ይደበድብ ያቆስል ሲከፋም ይደፍርና ይገድል ገባ።
ወንዶቹ ሲደክሙ ሲወድቁ ወይም ሲቆስሉ ሴቶቹ የመሪነቱን ሥፍራ እየተረከቡ ሰልፈኛዉን የደም ዋጋ ደም ነዉ ን ያስፈክሩት ያዙ።
ሰኔ የሆነዉ ግን በሱዳን የተቃዉሞ ሰልፍ ታሪክ ብዙም የማይታወቅ ነዉ።