input
stringlengths
1
130k
ከእነዚህ አዋጆች መካከል የሀገሪቱ የምርጫ ስርዓትን በተመለከተ ሊደረግ ታስቦ የነበረው ማሻሻያ አንዱ መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ባለፈው ዓመት ንግግራቸው ኢትዮጵያ የምትመራበትን የምርጫ ሕግ በገዢው ፓርቲ እና በተቃዋሚዎች መካከል በሚደረግ ድርድር እንደሚሻሻል አስታዉቀዋል፡፡
የሚሻሻለው የምርጫ ሕግ አሁን ያለውን የአብላጫ ድምጽ የምርጫ ስርዓት ከተመጣጣኝ ውክልና ስርዓት ጋር በትክክለኛ ሚዛን ያጣመረ እንደሚሆንም አብራርተው ነበር፡፡
ሕጉ የሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ድምጽ የሚሰማባቸው ምክር ቤቶች እንዲኖሩ ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ እንደሚስተካከልም ቃል መግባታቸው ይታወሳል፡፡
የቀድሞው አንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ የምክር ቤት አባል አቶ ግርማ ሰይፉ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት አላቸው፡፡
የምርጫ ህጉን ለማሻሻል ሕገ መንግስት ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ያሉ ጽሁፉን ያዘጋጁ ሰዎችም አያውቁም፡፡
አሁን ደግሞ መጥተው ለሚቀጥለው ዓ ም ለሚደረገው ምርጫ የምርጫ ህጉ የሚሻሻልበት ስራ በምክር ቤት ይጸድቃል ይላሉ፡፡
ሕጉ ከመሻሻሉ በፊት ግን በዚህ ዓመት በመላው ሀገሪቱ የአካባቢ እና ማሟያ ምርጫ ይካሄዳል፡፡
ምርጫው ዲሞክራሲያዊነቱን ጠብቆ ነጻ ፍትሃዊ እና በህዝቡ ዘንድ ተዓማኒነትን ያተረፈ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች በፓርላሜንታዊ ስርዓት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ገዢው ፓርቲ ከሌሎች ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እያደረገ ያለውን ውይይት በአዎንታዊነት ጠቅሰዋል፡፡
ውይይቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ እንዲጎለብት እና የፖለቲካ ምህዳሩም ይበልጥ እንዲሰፋ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
አቶ ግርማ ሰይፉ በፓርቲዎች መካከል ውይይት እየተደረገ ነው የሚለውን የፕሬዝዳንቱን ገለጻ አይቀበሉም፡፡
አሁን ፓርቲ የመንግስት ውይይት ተጀምሯል ብለው የእውነት ያምናሉ ማለት ነው
አሁን ተሰብስበው ውይይት እያደረጉ ያሉትን ሰዎች በምን አይነት ደረጃ እንደሚመዝኗቸው አውቃለሁ፡፡
ስለዚህ ከእነዚህ ጋር እየተነጋገርን ነው ብለው በአደባባይ ወጥተው ህዝብን መዋሸት በጣም ያሳፍራል ይላሉ አቶ ግርማ፡፡
የፕሬዝዳንቱ ንግግር ሌላው የጊዜው አነጋጋሪ ጉዳይ የሆነውን የሙስና ጉዳይንም ነክቷል፡፡
አላግባብ የመጠቀም እና የሙስና ጉዳዮች ጎልተው በሚታዩባቸው ዘርፎች መንግሥት ባለፈው ዓመት ተሃድሶ ማካሄዱን ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተናግረዋል፡፡
ተሃድሶ ከተመለከታቸው ዘርፎች ቀልጣፋ እና ውጤታማ የፍትህ ስርዓት ማምጣት የፖሊስ እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ማሻሻል እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡
ተሃድሶው በአንዳንድ ቦታዎች ውጤታማ መሆን መጀመራቸውን ገልጸው በብዙ ቦታዎች ግን ገና በዝግጅት ላይ ያሉ እና የተጓተቱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
መንግሥታቸው በዘርፎቹ ውስጥ በሚስተዋለው ሙስና ላይ ስለሚወስደው እርምጃ ደግሞ ተከታዩን ብለዋል፡፡
የቀድሞው የምክር ቤት አባል አቶ ግርማ ስለፕሬዝዳንቱ ጠቅለል ያለ አስተያየታቸውን ያጋራሉ፡፡
ሁልጊዜ ተስፈኛ ስለሆንኩ ተስፋ ስለማድረግ ይሆናል የተሻለ ነገር ለማድረግ መጠቀም የሚችሏቸውን አዲስ ምዕራፎች ሳይጠቀሙባቸው እያለፉ ነው ያሉት፡፡
ለውጥ ሊኖር የሚችልባቸው አዲስ መንገዶችን አስበን እንሰራለን እንዲሉ እጠብቅ ነበር ብለዋል፡፡
የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌት በኢትዮጵያ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ፎቶ ፡ ሞክቢል ያቤሮ በዚህ መርኃ ግብር ላይ ዕድሜያቸው ከ የሆነ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ወጣቶች እየተሳተፉ ነው፡፡
ከሥር የምታገኟቸው ምስሎች በመርሃ ግብሩ መደምደሚያ የጉባዔ ቀናት ላይ የተወሰዱ ናቸው፡፡
የዶ ር አቢይ ንግግር እስረኞች ይፈቱ ና የኢትዮጵያ ቅርሶች በብሪታንያ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ኢትዮጵያዊ ሕይወት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በፊትና በኋላ አገሪቱ በድንገት ከእስር ቤትነት ወደ ነጻ ምድርነት ተሸጋግራለች ማለት ይቻላል።
ከአድማስ እስከ አድማስ ግዙፉ ግድብ እዚሕ ነዉ የኢትዮጵያንና የጎረቤቶችዋን የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ያረካል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ግድብ እዚሕ ነዉ።
ከዐባይ ወንዝ ዉኃ ኃይል የሚያመነጨዉ ግድብ ግንባታ በ ይጠናቀቃል ተብሏል።
ግዙፉ ፕሮጄክት የዉኃ ፍላጎቷን ይቀንስብኛል ብላ በሰጋችዉ ግብፅና በኢትዮጵያ መካከል የዲፕሎማሲ ዉዝግብ ቀስቅሷልም።
ጠንካራዉ ግንብ ግድቡ ሜትር ከፍታ አለዉ ኪሎ ሜትር ያክል ይረዝማል።
በዚሕም ምክንያት የግድቡ ሥራ ለኢትዮጵያዉን የኑሮ መሻሻል ተስፋ ነዉ።
ይኽ አካባቢ በሙሉ በቅርብ ዓመታት ዉስጥ በዉኃ ይሞላል ይላሉ ሜካኒካል ኢንጂነር አብዱ ይብራ ወንዙ የሚፈስበትን አካባቢ እየጠቆሙ።
የዐባይን ዉኃ የሚጠቀሙ ጎረቤቶችዋ በተለይ ግብፅ ግን ይሕን አትፈልገዉም።
የዐባይ ተጠቃሚዎች ዉዝግብ ኢትዮጵያ በሚቀጥለዉ ዓመት ዉስጥ ግድቡን መሙላት ትፈልጋለች።
ግብፅ ግድቡ ኢትዮጵያ እንዳቀደችዉ የሚሞላ ከሆነ ወደ ግብፅ የሚፈሰዉ የዉኃ መጠን ይቀንሳል ብላ ትከራከራለች።
የዉኃ እጥረት ወይም ድርቅ ቢከሰት ኢትዮጵያ ግብፅ መጠቀም ያለባትን ያክል የዉኃ መጠን ለግብፅ መፍቀድ አለባት።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በቅርቡ ደቡብ አፍሪቃን በጎበኙበት ወቅት አስተናጋጃቸዉ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንት ከግብፅ ጋር እንዲሸመግሏቸዉ ጠይቀዋል።
ፕሬዝደንት ሲይሪል ራማፎዛ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረዉን ዉዝግብ ለማስወገድ ኢትዮጵያና ግብፅን ይሸመግላሉ።
ራማፎዛ በሚቀጥለዉ የካቲት ተዘዋዋሪዉን የአፍሪቃ ሕብረት የሊቀመንበርነት ሥልጣን ይረከባሉ።
እስካሁን ድረስ አፍሪቃ ዉስጥ ያሉት ትላልቅ ግድቦች የሚያመርቱት ቢደመር የኢትዮጵያዉን አያክልም።
መዘግየትና ወቀሳዉ በፊት በተያዘዉ ዕቅድ መሰረት ግድቡ ከዚሕ ቀደም መጠናቀቅ ነበረበት።
ይሁንና የአስተዳደር ጉድለትና ሙስና ግንባታዉ በተያዘለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ እንቅፋት ሆነዋል።
ዐባይ በዚሕ ፈለግ ከኢትዮጵያ አልፎ ወደ ሱዳንና ግብፅ ይፈሳል።
ወደ ሁለቱ ሐገራት ወደፊት የሚደርሰዉ የዉኃ መጠን በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል በሚደረገዉ ድርድርና ዉይይት ላይ የተመሰረተ ነዉ።
ግብፅ ኢትዮጵያ ከምታመርተዉ የኤሌክትሪክ ኃይል መግዛት እንደምትፈልግ ግን ከዚሕ ቀደም አስታዉቃለች።
ዘርፈ ብዙዋ የህክምና ሰው የመጀመሪያዋ ሴት የህክምና ፕሮፌሰር ናቸው፡፡
በምዕራብ ኢትዮጵያ ተቋርጦ የቆየው የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት ተመለሰ ይዘት ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የጦር ወንጀል ስጋት በየመን የየመን ተቀናቃኝ ሀይሎች የጦር ወንጀል ሳይፈጽሙ አይቀርም ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰሰ።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የየመን ተቀናቃኝ ሃይሎች በንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል ሲል ከሰሰ።
በአዲሲቷ አፍሪቃዊት ሀገር በአንጋፋ ፖለቲከኞቿ መካከል አለመግባባቱ ንሮ ወደጦርነት ከተሸጋገረ ወዲህ ሁለቱ ወገኖች በተግባር ያልተገለፁ ተደጋጋሚ ስምምነቶች ተፈራርመዋል።
አደራዳሪዎቹ የታንዛኒያ ባለስልጣናትም ተቀናቃኞቹን ያደራደሩት ን የከፈለዉን ልዩነት ለማስታረቅ እንጂ የተኩስ ማቆሙና መሰሉ ድርድር አዲስ አበባ ላይ በኢጋድ እንደሚከናወን አመልክተዋል።
የሴቶች አለባበስና እና አስገድዶ መድፈር ከክፍለ ሀገር ሥራ ለመሥራት ብዬ ነው ከቤት ጠፍቼ ወደ አዲስ አበባ የመጣሁት።
ጥቃቱን ያደረሰብኝ ፖሊስ መጀመሪያ ታስሮ ነበር ግን በዋስ ተለቀቀና ጠፋ እስካሁን አልተያዘም።
ፖሊስ ጣቢያ ባልሄድ ኖሮ ይህ አይፈጠርም ነበር እያልኩ አንዳንዴ አስባለሁ።
የሚሉ ጥያቄዎችን ማቅረብ ለወንጀሉ መፈፀም ትልቁን ሚና እሷ እንደተጫወተች ያህል የሚያቀርቡ ወገኖች የወንጀል ፈጻሚውን ጥፋት ለመከላከል ይመስላል የሚሉ ጥቂት አይደሉም።
ምን ለብሳ ነበር በሚል ርዕስ የቀረበው እጅጉን የሚያሳዝን እና ልብ የሚነካ ትዕይንት ነው ይላሉ የአውደ ርዕዩ ተመልካቾች።
የነበሩት ነገሮች ሴቷ ለብሳ የነበረው ለዛ የሚጋብዝ እንዳልሆነ በደንብ ያሳያል።
ምን ለብሳ ነበር ሴታዊት የሴቶች ንቅናቄ ማሕበር በኢትዮጵያ ከሲዊድን ኤምባሲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው አውደ ርዕይ ነው።
ከኅዳር እስከ ታህሳስ ቀን ዓ ም በአዲስ አበባ ሙዚየም ለተመልካች ቀርቦ እየታየ ይገኛል።
ስትደፈር ምን ለብሳ ነበር በሚል በትዕይንቱ ላይ ዕድሜያቸው ከሰባት እስከ ዓመት ያሉ የ ሴቶች ልብስ እና ታሪካቸው ለተመልካች ቀርቧል።
ያንን መራር ወቅት አስታዋሽ ድባብ ያለው የእውነታውን ክስተት በምናብ ዞር ብሎ ላስታወሰ ልብ ይሰብራል ይላሉ የተመለከቱት።
ማሕበሩ ከአራት ዓመት በፊት የተቋቋመ ሲሆን ጾታዊ ጥቃት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሠራል።
ማሕበራቸው የፆታ እኩልነትን በተመለከተ ግንዛቤ ለመፍጠር እንቅስቃሴ እንደሚያደርግም ዶክተር ስህን ይናገራሉ።
በኢትዮጵያ በአንዳንድ ቦታ የሴቶችን ክብር ዝቅ የሚያደርጉ ልማዳዊ አስተሳሰቦች መኖራቸው ይታያል፡፡
በዚህም ምክንያት ሴቶች ለስነ ልቦናዊ አካላዊ እና ማሕበራዊ ችግሮች ተጋልጠው ይገኛሉ እንደብዙዎች አነጋገር፡፡
ያለእድሜ ጋብቻ እና ግርዛት የመሳሰሉ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች የቤት ውስጥ ጥቃት ይደርስባቸዋል።
የትምህርት ዕድል የማግኘት እንዲሁም የንብረት እና ሃብት የማፍራት መብቶቻቸውን ተነፍገው በመቆየታቸው በማኅበረሰብ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ እንዲቀንስ አድርጓል፡፡
የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችም ከማህበረሰቡ ባህላዊና ልማዳዊ አስተሳሰቦች ጋር ተቆራኝተው ይገኛሉ።
ይህ በመሆኑም ጥቃቱ ዛሬም አላቆመም ይላሉ በኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማሕበር ኃላፊ የሆኑው ወ ት ኢየሩሳሌም ሰለሞን።
አሁንም ቢሆን ሴቶች ተደፍረው የተለያየ ጥቃት ደርሶባቸው ወደ ማህበራችን ይመጣሉ።
ይህንን ባትለብሽ ኑሮ አትደፈሪም ነበር በሚል ሴቷን ለተጨማሪ ጉዳት ሊያጋልጧት አይገባም።
እናንተም ይህን የተደፈሩ ሴቶችን እውነተኛ ስሜት ለመጋራት የሚያስችል አውደ ርዕይ በሳምንቱ መጨረሻ ልትመለከቱት ትችላላችሁ።
አልቃዳ በይፋ እንደሚታወቀዉ የዩናይትድ ስቴትስ የሳዑዲ አረቢያ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሌሎችም መንግሥታት ጠላት ነዉ።
ዩናይትድ ስቴትስ የሳዑዲ አረቢያ የአረብ ኤሚሬቶች የቅርብ ደጋፊ አስታጣቂ አማካሪም ናት።
ሳዑዲ አረቢያ የአረብ የእስያና የአፍሪቃ መንግሥታትን አስከትላ በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉትን የየመን አንሳር አላሕ ወይም የሁቲ አማፂያንን ትወጋለች።
የመን የሸመቀዉ የዩናይትድ ስቴትስ ቀንደኛ ጠላት አል ቃኢዳ ዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ ወዳጅ ሳዑዲ አረቢያ ከምትመራዉ ጦር ጋር አብሮ ሁቲን ይወጋል።
ወዳጅ እና ጠላት አሸናፊ እና ተሸናፊ ማብቂያ እና መፍትሔ ያልየበት ጦርነት ሕፃን ከአዛዉንት ሲቢል ከወታደር ሳይለይ ሺዎችን ይፈጃል።
ጦራቸዉን ባዘዙ በ ኛ ሳምንቱ ግድም ባለሥልጣኖቻቸዉን ወደ ሰነዓ ላኩ።
ኢማም ያሕያ መልዕክቱ ሲደርሳቸዉ የሁለቱ ሐገራት ወታደሮች ጂዛን አሲር ናጅራት እና አል ሁዴይዳሕ ላይ ዉጊያ ገጥመዉ ነበር።
ብዙም ሳይቆይ የየመን ኢማም ጦራቸዉን ከሰወስቱ ትናንሽ ግዛቶች ለቅቆ እንዲወጣ ሲያዙ የሳዑዲ ንጉስ ደግሞ ጦራቸዉ አልሁዴይዳሕን ለየመኖች እንያስረከብ አዘዙ።
የፖለቲካ ተንታኝ እና ደራሲ ዩሱፍ ያሲን እንደሚሉት የመን የዘመተባት የማይመለስባት ሐገር ናት ትባላላች።
የዩናይትድ ስቴትስ እና የብሪታንያ ምርጥ ወታደራዊ አሰልጣኞች የሳዑዲ አረቢያ እና የተባባሪዎችዋን ወታደሮች ያሰልጥናሉ።
የአሜሪካ ሰላዮች ለሳዑዲ አረቢያ እና ለተከታዮቿ መረጃ የአሜሪካ የጦር ባለሙያዎች ምክር የአሜሪካ ጄቶች የአየር ላይ ነዳጅ ይሞላሉ።
መከላከያ ሚንስትር ጂም ማቲያስ መንግስታቸዉ በሚዝቀዉ ገንዘብ እንደሚደሰቱ ሑሉ ባደረገዉ ድጋፍም ይኩራራሉ።
አየር ላይ ያሉ ፓይለቶች እንዲተኩሱ ታዘዉ እንኳን የተሰጣቸዉን ተልዕኮ አደገኛነት ሲረዱ ቦምቡን የማይጥሉ አሉ።
ሆስፒታሎች እና ትምሕርት ቤቶች አካባቢ ተኩስ እንዳይከፈት የሚከለክል መመሪያ እንዳለ አይተናል።
በአሜሪካኖች የሚረዳ የሚሠለጥነዉ የተባባሪ ሐገራት ጦር ቦምብ ሚሳዬሉን ሠላማዊ ሕዝብ ላይ ያዝነበዋል።
በየመን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሠብአዊ እርዳታ አስተባባሪ ሊዛ ግራንዴ የጦርነቱ ዘግናኝ ዉጤት ብለዉታል።
የሳዓዳዉ ጥፋት አነጋግሮ ሳያበቃ ምዕራባዊ የመን ዉስጥ በአዉቶብስ ይጓዙ የነበሩ ሰላሳ ሰላማዊ ሰዎች በተባባሪዎቹ ሐገራት የአዉሮፕላን ጥቃት ተገደሉ።
አንድ የአካባቢዉ ባለሥልጣን እንዳሉት ሰዎቹ ከነአዉቶብሱ አመድ ነዉ የሆኑት።
ይሕ ጦርነት ይሕ ወንጀል ሰዎችን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ያለመ ነዉ።
የሰወስት ዓመት ከመንፈቁ ድብደባ ከ ሺሕ በላይ ሰላማዊ ሕዝብ ፈጅቷል።
የጂዳዉ ወኪላችን ነቢዩ ሲራክ እንደሚለዉ ዕድል ቀንቷቸዉ ሳዑዲ አረቢያ የገቡ የመኖች ስለየመን የሚተርኩት ዘግናኝ ነዉ።
የአጥኚዉ ቡድን ተወካይ እንዳሉት የየመንግሥቱ እና የቡድኑ አባላት የጦር ወንጀል ሳይፈፅሙ አይቅርም።
የሪያድ እና የአቡዳቢ ገዢዎች በሰወስት ወር ሊያጠናቅቁት የፎከሩት ጦርነት በሰወስት ዓመት ከመንፈቁም የድል ጭላንጭል አላዩም።
የፖለቲካ ተንታኝ ዩሱፍ ያሲን እንደሚሉት ደግሞ አንድም ሁነኛ ከተማ እንኳን አልተቆጣጠሩም።
የሪያድ እና የአቡዳቢ ገዢዎች በጦርነቱ እንደማያሸንፉ በትክክል ሲያዉቁ ግን በዓለም አቀፍ አሸባሪነት የሚያወግዙትን አልቃኢዳን ሳይቀር በተዘዋዋሪ ከጎናቸዉ አሰለፉ።
አል ዛይዲ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ የመን ዉስጥ የሸመቀ የአልቃኢዳ ቡድን አዛዥ ነዉ በሚል ማዕቀብ የጣለበት ሸማቂ ነበር።