Text
stringlengths
1
10.7k
Text Number
int64
0
31
License
stringclasses
6 values
Text By
stringclasses
463 values
Translation By
stringlengths
1
146
Language
stringclasses
188 values
File Name
stringlengths
9
81
Source
stringclasses
16 values
ISO639-3
stringclasses
178 values
Script
stringclasses
23 values
Parallel ID
stringclasses
822 values
Story Category
stringclasses
4 values
ግንጊሌ የተለመደውን የንቦች ድምጽ ለምን እንዳልሰማ እያሰበ ዛፉ ላይ ወጣ። ‹‹ምናልባት ቀፎው በጣም ጥልቅ ቦታ ላይ ይሆናል ያለው›› ሲል ለራሱ አሰበ። ወደሌላ ከፍ ወዳለ ቅርንጫፍ ላይ ወጣ። ያገኘው ነገር ግን ቀፎ ሳይሆን ፊት ለፊት የመጣችበትን ነብር ነበር! ነብሯ እንቅልፏን ሳታስበው ስላቋረጣት በጣም ተናደደች። ዓይኖቿን ጠበብ አድርጋ፣ አፏን ከፍታ፣ ትላልቅና ሹል ጥርሶቿን አገጠጠችበት።
8
CC-BY
Zulu folktale
Mezemir Girma
am
0072_የማር-ቆራጩ-መሪ-በቀል.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0072
asp
ነብሯ ለቀም ሳታደርገው ግንጊሌ ከዛፉ በፍጥነት መውረድ ጀመረ። በፍጥነቱም የተነሳ አንዱን ቅርንጫፍ ስቶት መሬት ላይ ክፉኛ ወድቆ ቁርጭምጭሚቱ ዞረ። በተቻለው መጠን በፍጥነት እያነከሰ ሄደ። ዕድሉ ረድቶት ነብሯ እንቅልፍ ስለተጫናት አላሳደችውም። ንጌዴ፣ የማር ቆራጩ መሪ፣ በቀሉን ተበቅሏል። ግንጊሌ ም ትምህርት ቀስሟል።
9
CC-BY
Zulu folktale
Mezemir Girma
am
0072_የማር-ቆራጩ-መሪ-በቀል.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0072
asp
ስለዚህ የግንጊሌ ልጆች የንጌዴን ታሪክ ሲሰሙ ለዚያ ትንሽ ወፍ አክብሮት አላቸው። ማር በቆረጡ ቁጥር ለማር ቆራጩ መሪ ከነእጩ ብዙ ቆረጥ አድርገው መስጠታቸውን ያረጋጣሉ።
10
CC-BY
Zulu folktale
Mezemir Girma
am
0072_የማር-ቆራጩ-መሪ-በቀል.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0072
asp
ማንበብ እወዳለሁ።
0
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ, መዘምር ግርማ
am
0087_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0087
asp
ለማን ላንብብ?
1
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ, መዘምር ግርማ
am
0087_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0087
asp
ሕጻኗ ተኝታለች።
2
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ, መዘምር ግርማ
am
0087_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0087
asp
ለማን ላንብብ?
3
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ, መዘምር ግርማ
am
0087_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0087
asp
እናቴ እና አያቴ ምግብ እያበሰሉ ነው።
4
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ, መዘምር ግርማ
am
0087_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0087
asp
ለማን ላንብብ?
5
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ, መዘምር ግርማ
am
0087_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0087
asp
አባቴ እና አያቴ መኪናዋን እየሰሩ ነው።
6
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ, መዘምር ግርማ
am
0087_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0087
asp
ለማን ላንብብ? ቁጭ ብዬ ለራሴው አነባለሁ።
7
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ, መዘምር ግርማ
am
0087_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0087
asp
ከዘመናት በፊት አበራ የተባለ ወላጅ አልባ የሆነ ህፃን ነበር። ወላጆቹ ገና የስድስት ወር ህፃን እያለ ነበር በወረበላዎች የተገደሉት። የሰፈሩ ሰዎች በሃዘን ላይ ሆነው 'አበራ' ምን እንደሚሆን ያስቡ ነበር።
0
CC-BY
Gaspah Emukuru Juma
ከድር ኢብራሂም, ፋሲካ ምንዳ
am
0088_ታዳጊው-አበራ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0088
asp
የሰፈሩ ሰዎች የህፃኑን ወላጆች ከቀበሩ በኋላ የቀበሌው አስተዳደር አቶ ሰሎሞን ስብሰባ ጠሩ። አቶ ሰሎሞን ፀጉረ ረዥም እና በአካባቢው ስዎች ዘንድ እጅግ የሚከበርና የሚፈራ ነበር። አቶ ሰለሞን ድሮ ድሮ ዛፎች ሳይቆረጡ እና ቤቶች ሳይገነቡ በጫካ ውስጥ ይኖር ነበር ተብሎ ይታመናል።
1
CC-BY
Gaspah Emukuru Juma
ከድር ኢብራሂም, ፋሲካ ምንዳ
am
0088_ታዳጊው-አበራ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0088
asp
አቶ ሰሎሞን ስብሰባ የጠሩት ስለ ህፃኑ ለመወያየት ስለነበር አንድ የመንደሩ ከበርቴ የሆነ ላቀው የተባለ ሰው አበራን ለማሳደግ ይወስደዋል። አቶ ላቀው ብዙ ሴት እና ወንድ ልጆች ነበሩት። ሴቶቹ እናታቸውን በቤት ውስጥ ስራ ሲያግዙ ወንዶቹ ደግሞ የአባታቸውን ከብቶች እንዲጠብቁ ይላኩ ነበር።
2
CC-BY
Gaspah Emukuru Juma
ከድር ኢብራሂም, ፋሲካ ምንዳ
am
0088_ታዳጊው-አበራ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0088
asp
አበራም በቤተሰቡ ውስጥ አደገ እናም በጣም ደስተኛ ነበር። በጣም ተወዳጅ እና ሁሉንም የሚወድ ነበር። በሜዳ ላይ ሆኖ ከብቶቹን መጠበቅ በጣም ያዝናናው ነበር።
3
CC-BY
Gaspah Emukuru Juma
ከድር ኢብራሂም, ፋሲካ ምንዳ
am
0088_ታዳጊው-አበራ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0088
asp
አበራ አንዷን ላም በጣም ይወዳት ስለነበር 'ቦራ' ብሎ ስም አወጣላት። ቦራ ከከብቶቹ ሁሉ በጣም ያገለገለች ነበርች። በዚህም ምክንያት ባለቤትየው ከፍተኛ ዋጋ ይሰጧት ነበር።
4
CC-BY
Gaspah Emukuru Juma
ከድር ኢብራሂም, ፋሲካ ምንዳ
am
0088_ታዳጊው-አበራ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0088
asp
አንድ ቀን እነ አበራ ከብት በመጠበቅ ላይ እያሉ ሃይለኛ ዝናብ ይጥል ጀመር እነርሱም ዝናቡ እስኪያባራ ብለው ዛፍ ሥር ቁጭ አሉ። ነገር ግን መሽቶ እስኪጨልም ድረስ ዝናቡ አላባራም ነበር። ጨልሞ ከቆየ በኋላ ዝናቡ አባራ ነገር ግን ከብቶቹን ወደ ቤት ለመውሰድ ሲፈልጓቸው የሉም።
5
CC-BY
Gaspah Emukuru Juma
ከድር ኢብራሂም, ፋሲካ ምንዳ
am
0088_ታዳጊው-አበራ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0088
asp
ከብቶቹን ሳናገኝ ወደ ቤት ከሄድን አባታችን አያስገባንም አሉና ሁለት ልጆች ወደ አጎታቸው ቤት ሄዱ ሁለቱ ልጆች ደግሞ ወደ አክስታቸው ቤት ሄዱ። ነገር ግን አበራ አጎትም ሆነ አክስት የለውም እና መሄጃ ስለሌለው ከብቶቹን እስኪያገኛቸው ድረስ ለመፈለግ ወሰነ።
6
CC-BY
Gaspah Emukuru Juma
ከድር ኢብራሂም, ፋሲካ ምንዳ
am
0088_ታዳጊው-አበራ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0088
asp
አበራ የሚወደውን ላም ዘፈን እየዘፈነ ከብቶቹን በሚያውቀው መንገድ ሁሉ ፈለጋቸው። እምቧ በይ ላሜ ቦራ እምቧ በይ እንቧ በይ ላሜ ቦራ እማቧ በይ ---እያለ ፍለጋውን ቀጠለ።
7
CC-BY
Gaspah Emukuru Juma
ከድር ኢብራሂም, ፋሲካ ምንዳ
am
0088_ታዳጊው-አበራ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0088
asp
አበራም ዘፈኑን እየዘፈነ ሌሊቱን በሙሉ ፍለጋውን ቀጠለ። የላም እበት ላይ እግሩ አረፈ ግን ቀዝቃዛ ነበር። የላም ሽንትም ላይ እግሩ አረፈ ግን ቀዝቃዛ ነበር። አበራ ግን ተስፋ አልቆረጠም።
8
CC-BY
Gaspah Emukuru Juma
ከድር ኢብራሂም, ፋሲካ ምንዳ
am
0088_ታዳጊው-አበራ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0088
asp
ለሊቱን በሙሉ ሲፈልግ ከቆየ በኋላ ሊነጋ ሲል አንዲት ትንሽዬ መንደር አገኘ ከብቶቹም በመንደሩ አስተዳደር ቤት አገኛቸው። ለመንደሩ ሊቀመንበሩ ከብቶቹ እንዲሰጡት ተማፀ ነገር ግን ሊቀመንበሩ አይሆንም አልሠጥም አለው።
9
CC-BY
Gaspah Emukuru Juma
ከድር ኢብራሂም, ፋሲካ ምንዳ
am
0088_ታዳጊው-አበራ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0088
asp
በዚህ ተስፋ የቆረጠው አበራ ዘፈኑን እየዘፈነ ወደቤቱ መመለስ ጀመረ። እምቧ በይ ላሜ ቦራ እምቧ በይ እምቧ በይ ላሜ ቦራ እምቧ በይ ሲል ቦራ ተከተለችው ከዛም ሁሉም ከብቶች በረቱን ጥሰው ወጡና አበራን ተከትለው ሄዱ። እሱም ወደ ቤት መራቸው።
10
CC-BY
Gaspah Emukuru Juma
ከድር ኢብራሂም, ፋሲካ ምንዳ
am
0088_ታዳጊው-አበራ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0088
asp
አበራ ቤቱ ሲደርስ የሠፈሩ ሰው እንዳለ ወጥቶ ስሙን እየጠራ እና እያወደሰ ተቀበሉት። አቶ ላቀው በጣም አመስገነው ቀይ የትምህርት ቤት ቦርሳ ገዝተው ሸለሙት እናም ትምህርት እንዲማር አደረጉት።
11
CC-BY
Gaspah Emukuru Juma
ከድር ኢብራሂም, ፋሲካ ምንዳ
am
0088_ታዳጊው-አበራ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0088
asp
ይቺ ካላይ ነች። ዕድሜዋ 7 ዓመት ነው። የስሟ ትርጉም በቋንቋዋ በሉቡኩሱ ‹‹ጥሩዋ ልጅ›› ማለት ነው።
0
CC-BY
Ursula Nafula
Mezemir Girma
am
0089_ካላይ-ከእጽዋት-ጋር-ትነጋገራለች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0089
asp
ካላይ ከእንቅልፏ ስትነሣ ከአንድ የብርቱካን ዛፍ ጋር ትነጋገራለች። ‹‹እባክህ አንተ የብርቱካን ዛፍ ትልቅ ሁንና ብዙ የበሳሰሉ ብርቱካኖችን ስጠን›› ትለዋለች።
1
CC-BY
Ursula Nafula
Mezemir Girma
am
0089_ካላይ-ከእጽዋት-ጋር-ትነጋገራለች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0089
asp
ካላይ ወደ ትምህርት ቤት ትሄዳለች። በመንገዷም ላይ ከሳሩ ጋር ታወራለች። ‹‹እባክህ ሳር አረንጓዴነትህን ግፋበት እንጂ እንዳትደርቅ።››
2
CC-BY
Ursula Nafula
Mezemir Girma
am
0089_ካላይ-ከእጽዋት-ጋር-ትነጋገራለች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0089
asp
ካላይ የዱር አበቦችን አልፋ ሄደች። ‹‹እባካችሁ አበቦች ለጌጥ ጸጉሬ ላይ እንዳረጋችሁ ማበባችሁን ቀጥሉ።››
3
CC-BY
Ursula Nafula
Mezemir Girma
am
0089_ካላይ-ከእጽዋት-ጋር-ትነጋገራለች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0089
asp
በትምህርት ቤት ግቢ ካለው ዛፍ ጋርም ካላይ ትነጋገራለች። ‹‹እባክህ አንተ ዛፍ ከጥላው ስር ቁጭ ብለን እንድናነብ ትላልቅ ቅርንጫፎችን አብቅልልን።››
4
CC-BY
Ursula Nafula
Mezemir Girma
am
0089_ካላይ-ከእጽዋት-ጋር-ትነጋገራለች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0089
asp
ካላይ በትምህርት ቤቷ ዙሪያ ካለው ቁጥቋጦም ጋር ታወራለች። ‹‹ጠንካራ ሆናችሁ እደጉ፤ መጥፎ ሰዎች እንዳያልፉ አግዷቸው።››
5
CC-BY
Ursula Nafula
Mezemir Girma
am
0089_ካላይ-ከእጽዋት-ጋር-ትነጋገራለች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0089
asp
ካላይ ከትምህርት ቤት ወደ ቤቷ ስትመለስ የብርቱካኑን ዛፍ አየችው። ‹‹የብርቱካን ፍሬዎችህ ገና አልበሰሉም?›› ስትል ካላይ ጠየቀችው።
6
CC-BY
Ursula Nafula
Mezemir Girma
am
0089_ካላይ-ከእጽዋት-ጋር-ትነጋገራለች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0089
asp
‹‹የብርቱካኑ ፍሬዎች ገና አልበሰሉም›› ካላይ አለች። ‹‹ነገ እመለስና አይሃለሁ የብርቱካን ዛፍ›› አለች ካላይ። ‹‹ምናልባት ያኔ የበሰሉ የብርቱካን ፍሬዎች አዘጋጅተህ ትጠብቀኝ ይሆናል!››
7
CC-BY
Ursula Nafula
Mezemir Girma
am
0089_ካላይ-ከእጽዋት-ጋር-ትነጋገራለች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0089
asp
ትንሹ ወንድሜ አርፍዶ ነው የሚነሣው። እኔ ግን ጎበዝ ስለሆንኩ ቶሎ እነሳለሁ!
0
CC-BY
Michael Oguttu
Mezemir Girma
am
0095_ዛማ-ጎበዝ-ነች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0095
asp
እኔ ነኝ ፀሐይን የማስገባት።
1
CC-BY
Michael Oguttu
Mezemir Girma
am
0095_ዛማ-ጎበዝ-ነች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0095
asp
‹‹አንቺ የጠዋት ኮከቤ ነሽ›› ትለኛለች እማ።
2
CC-BY
Michael Oguttu
Mezemir Girma
am
0095_ዛማ-ጎበዝ-ነች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0095
asp
ራሴን በራሴ እታጠባለሁ። ምንም እገዛ አልፈልግም።
3
CC-BY
Michael Oguttu
Mezemir Girma
am
0095_ዛማ-ጎበዝ-ነች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0095
asp
ቀዝቃዛ ውሃንም ሆነ ሽታ ያለውን ሰማያዊ ሳሙና አልፈራም።
4
CC-BY
Michael Oguttu
Mezemir Girma
am
0095_ዛማ-ጎበዝ-ነች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0095
asp
እናቴ ‹‹ጥርስሽን አትርሺ›› ብላ ታስታውሰኛለች። ‹‹በፍጹም አልረሳም!›› ብዬ እመልስላታለሁ።
5
CC-BY
Michael Oguttu
Mezemir Girma
am
0095_ዛማ-ጎበዝ-ነች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0095
asp
ከታጠብኩ በኋላ አያቴንና አክስቴን ሠላም እላለሁ፤ መልካም ቀንም እመኝላቸዋለሁ።
6
CC-BY
Michael Oguttu
Mezemir Girma
am
0095_ዛማ-ጎበዝ-ነች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0095
asp
ከዚያም እለባብሳለሁ። ‹‹አሁን ትልቅ ልጅ ነኝ እማማ›› እላለሁ።
7
CC-BY
Michael Oguttu
Mezemir Girma
am
0095_ዛማ-ጎበዝ-ነች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0095
asp
አዝራሮቼን እዘጋለሁ። ጫማዬንም አስራለሁ።
8
CC-BY
Michael Oguttu
Mezemir Girma
am
0095_ዛማ-ጎበዝ-ነች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0095
asp
ትንሹ ወንድሜ በትምህርት ቤት የተደረገውን ነገር ሁሉ ወሬ እንዲደርሰው አደርጋለሁ።
9
CC-BY
Michael Oguttu
Mezemir Girma
am
0095_ዛማ-ጎበዝ-ነች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0095
asp
በክፍልም ውስጥ በሁሉም መንገድ የተቻለኝን አደርጋሁ።
10
CC-BY
Michael Oguttu
Mezemir Girma
am
0095_ዛማ-ጎበዝ-ነች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0095
asp
በየቀኑ እነዚህን ሁሉ ጥሩ ጥሩ ነገሮች አደርጋለሁ። በጣም የምወደው ነገር ግን መጫወት እና መጫወት ነው።
11
CC-BY
Michael Oguttu
Mezemir Girma
am
0095_ዛማ-ጎበዝ-ነች.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0095
asp
በምስራቅ አፍሪካ በሚገኘው የኬንያ ተራራ በአንድ በኩል በሚገኝ አንድ መንደር አንዲት ትንሽ ልጅ ከእናቷ ጋር በማሳ ላይ ትሰራ ነበር። ስሟም ዋንጋሪ ይባላል።
0
CC-BY
Nicola Rijsdijk
Mezemir Girma
am
0110_ትንሽ-ዘር፣-የዋንጋሪ-ማታይ-ታሪክ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0110
asp
ዋንጋሪ ውጪ ውጪውን ማለት ትወዳለች። በቤተሰቧ የአትክልት ስፍራ አፈሩን በገጀራ ትቆፍራለች። ትናንሽ ዘሮችንም ወደ ሞቃቱ መሬት ትከታለች።
1
CC-BY
Nicola Rijsdijk
Mezemir Girma
am
0110_ትንሽ-ዘር፣-የዋንጋሪ-ማታይ-ታሪክ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0110
asp
ፀሐይ ከገባች በኋላ ያለውን ጊዜ በጣም ትወደዋለች። እጽዋቱ አልታይ ማለት በሚጀምሩበት ጊዜ ዋንጋሪ ወደ ቤቷ መሄጃው ሰዓት መድረሱን ታውቃለች። በማሳዎቹ ውስጥ ያሉትን ጠባብ መንገዶች ተከትላና ስትሄድ እንዳደረገችው ወንዙን አቋርጣ ትመለሳለች።
2
CC-BY
Nicola Rijsdijk
Mezemir Girma
am
0110_ትንሽ-ዘር፣-የዋንጋሪ-ማታይ-ታሪክ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0110
asp
ዋንጋሪ ትምህርት ቤት መሄድ የምትወድ ጎበዝ ልጅ ነበረች። እናትና አባቷ ግን እቤት ቆይታ እንድታግዛቸው ይፈልጉ ነበር። ሰባት ዓመት ሲሆናት ታላቅ ወንድሟ ወላጆቿን ትምህርት ቤት እንዲያስገቧት አሳመናቸው።
3
CC-BY
Nicola Rijsdijk
Mezemir Girma
am
0110_ትንሽ-ዘር፣-የዋንጋሪ-ማታይ-ታሪክ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0110
asp
ዋንጋሪም ትምህርት ትወድ ነበር! መጽሐፍ ባነበበች ቁጥር ብዙ እያወቀች መጣች። በትምህርቷ ጥሩ ውጤት ስላስመዘገበች አሜሪካ እንድትማር ተጋበዘች። ዋንጋሪ እጅግ ተደሰተች! ስለ ዓለም ብዙ ለማወቅም ፈለገች።
4
CC-BY
Nicola Rijsdijk
Mezemir Girma
am
0110_ትንሽ-ዘር፣-የዋንጋሪ-ማታይ-ታሪክ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0110
asp
በአሜሪካውም ዩኒቨርሲቲ ዋንጋሪ ብዙ አዳዲስ ነገሮችን ተማረች። እጽዋትንና አስተዳደጋቸውን ተማረች። ራሷ እንዴት እንዳደገችም አስታወሰች። በሚያማምሩት የኬንያ ደኖች ከወንድሞቿ ጋር የተለያዩ ጨዋታዎችን ስትጫወት ነበር ያደገችው።
5
CC-BY
Nicola Rijsdijk
Mezemir Girma
am
0110_ትንሽ-ዘር፣-የዋንጋሪ-ማታይ-ታሪክ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0110
asp
ብዙ እየተማረች ስትሄድም የኬንያን ህዝብ መውደዷ የበለጠ እየተገለጠላት መጣ። ደስተኛና ነጻ ሕዝብ እንዲሆን ፈለገች። ብዙ እየተማረች ስትሄድም የአፍሪካው ቤቷ ይበልጥ ትዝ እያላት መጣ።
6
CC-BY
Nicola Rijsdijk
Mezemir Girma
am
0110_ትንሽ-ዘር፣-የዋንጋሪ-ማታይ-ታሪክ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0110
asp
ትምህርቷን ስትጨርስ ወደ ኬንያ ተመለሰች። አገሯን ግን ተቀይራ አገኘቻት። ትላልቅ እርሻዎች አገሪቱን አጥለቅልቀዋታል። ሴቶች ለማገዶ የሚሆን እንጨት አልነበራቸውም። ህዝቡ ደህይቶ ልጆቹ ተርበዋል።
7
CC-BY
Nicola Rijsdijk
Mezemir Girma
am
0110_ትንሽ-ዘር፣-የዋንጋሪ-ማታይ-ታሪክ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0110
asp
ዋንጋሪ ምን ማድረግ እንዳለባት ታውቅ ነበር። ሴቶቹን ችግኝ እንዴት እንደሚያቸግኑና ዛፍ እንዴት እንደሚተክሉ አስተማረቻቸው። ሴቶቹም ዛፎቹን እየሸጡ ቤተሰባቸውን ማስተዳደር ቻሉ። ሴቶቹ በጣም ተደሰቱ። ዋንጋሪ አቅም እንዳላቸው እንደዲገነዘቡ ረድታቸዋለች።
8
CC-BY
Nicola Rijsdijk
Mezemir Girma
am
0110_ትንሽ-ዘር፣-የዋንጋሪ-ማታይ-ታሪክ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0110
asp
ከረጅም ጊዜ በኋላም አዳዲሶቹ ዛፎች ደን ሆኑ፤ ወንዞቹም እንደዱሮው መፍሰስ ጀመሩ። የዋንጋሪም መልዕክት በመላው አፍሪካ ተሰራጨ። ዛሬ ከዋንጋሪ ዘሮች ብዙ ዛፎች ተገኝተዋል።
9
CC-BY
Nicola Rijsdijk
Mezemir Girma
am
0110_ትንሽ-ዘር፣-የዋንጋሪ-ማታይ-ታሪክ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0110
asp
ዋንጋሪ በጣም ለፍታለች። በዓለም ዙሪያ የነበሩ ሰዎች ስራዋን አይተው ትልቅ ሽልማት ሰጧት። የዓለም የኖቤል ሽልማት ይባላል ሽልማቱ። ዋንጋሪም ይህን ሽልማት ስትቀበል የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሴት ነች።
10
CC-BY
Nicola Rijsdijk
Mezemir Girma
am
0110_ትንሽ-ዘር፣-የዋንጋሪ-ማታይ-ታሪክ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0110
asp
ዋንጋሪ በ2011 አርፋለች። የሚያምር ዛፍ ባየን ቁጥር ግን ልናስታውሳት ይገባናል።
11
CC-BY
Nicola Rijsdijk
Mezemir Girma
am
0110_ትንሽ-ዘር፣-የዋንጋሪ-ማታይ-ታሪክ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0110
asp
አንድ ቀን ጥንቸል በወንዝ ዳር እየሄደች ነበር።
0
CC-BY
Basilio Gimo, David Ker
Mezemir Girma
am
0111_ጉማሬዎች-ለምን-ጸጉር-እንደሌላቸው.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0111
asp
ጉማሬም እዚያው ነበር። እየተንሸራሸረና ጥሩ ለምለም ሳር እየበላ ነበር።
1
CC-BY
Basilio Gimo, David Ker
Mezemir Girma
am
0111_ጉማሬዎች-ለምን-ጸጉር-እንደሌላቸው.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0111
asp
ጉማሬ ጥንቸልን አላያትም ነበርና ድንገት እግሯን ረገጣት። ጥንቸልም በጉማሬ ላይ መጮህ ጀመረች። ‹‹አንተ ጉማሬ! እግሬ ላይ እንደቆምክበት አይታይህም?››
2
CC-BY
Basilio Gimo, David Ker
Mezemir Girma
am
0111_ጉማሬዎች-ለምን-ጸጉር-እንደሌላቸው.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0111
asp
ጉማሬም ጥንቸልን ይቅርታ እንድታደርግለት ጠየቃት። ‹‹ይቅርታ። አላየሁሽም እኮ። እባክሽ ማሪኝ!›› አላት። ጥንቸል ግን አልሰማም ብላ ጮኸችበት። ‹‹አውቀህ ነው ያደረከው! አንድ ቀን አሳይሃለሁ! ዋጋህን ታገኛለህ!›› አለችው።
3
CC-BY
Basilio Gimo, David Ker
Mezemir Girma
am
0111_ጉማሬዎች-ለምን-ጸጉር-እንደሌላቸው.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0111
asp
ጥንቸል እሳትን ፈልጋ ሄደችና ስታገኛት ‹‹ሂጂ፣ ጉማሬ ከውኃ ውስጥ ሳር ሊግጥ ሲወጣ አቃጥዪው። እግሬን አይረግጠኝ መሰለሽ!›› አለቻት። እሳትም ‹‹ችግር የለም ጥንቸል ወዳጄ። ያልሽኝን እፈጽምልሻለሁ›› አለቻት
4
CC-BY
Basilio Gimo, David Ker
Mezemir Girma
am
0111_ጉማሬዎች-ለምን-ጸጉር-እንደሌላቸው.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0111
asp
በኋላም ጉማሬ ከወንዙ ርቃ ሳር ስትግጥ ‹‹ውሽ!›› ብላ እሳት ከተፍ አለችባት። ነበልባሉ የጉማሬን ጸጉር ያቃጥለው ጀመር።
5
CC-BY
Basilio Gimo, David Ker
Mezemir Girma
am
0111_ጉማሬዎች-ለምን-ጸጉር-እንደሌላቸው.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0111
asp
ጉማሬ እየጮኸ ወደ ውኃ ሮጠ። ጸጉሩ በሙሉ በእሳት ተቃጠለ። ጉማሬ ማልቀስ ቀጠለ። ‹‹ጸጉሬን እሳት አቃጠለብኝ! ጸጉሬ በሙሉ አለቀ! ቆንጆ ጸጉሬን!››
6
CC-BY
Basilio Gimo, David Ker
Mezemir Girma
am
0111_ጉማሬዎች-ለምን-ጸጉር-እንደሌላቸው.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0111
asp
ጥንቸል የጉማሬ ጸጉር በመቃጠሉ ተደሰተች። እና እስካሁን እሳትን ፍራቻ ጉማሬ ከውኃ ርቆ አይሄድም።
7
CC-BY
Basilio Gimo, David Ker
Mezemir Girma
am
0111_ጉማሬዎች-ለምን-ጸጉር-እንደሌላቸው.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0111
asp
እሮጥበታለሁ።
0
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
Mezemir Girma
am
0112_አካሌ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0112
asp
እዘልበታለሁ።
1
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
Mezemir Girma
am
0112_አካሌ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0112
asp
እጨፍርበታለሁ።
2
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
Mezemir Girma
am
0112_አካሌ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0112
asp
እዋኝበታለሁ።
3
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
Mezemir Girma
am
0112_አካሌ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0112
asp
ገመድ እዘልበታለሁ።
4
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
Mezemir Girma
am
0112_አካሌ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0112
asp
እለጋበታለሁ።
5
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
Mezemir Girma
am
0112_አካሌ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0112
asp
አመልጥበታለሁ።
6
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
Mezemir Girma
am
0112_አካሌ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0112
asp
ግን ልበርበት አልችልም።
7
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
Mezemir Girma
am
0112_አካሌ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0112
asp
ቱሊ አጭር ፀጉር አላት።
0
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
ፋሲል አሠፋ (Fasil Assefa)
am
0120_ፀጉር.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0120
asp
አና ረጅም ፀጉር አላት።
1
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
ፋሲል አሠፋ (Fasil Assefa)
am
0120_ፀጉር.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0120
asp
ካቲ ደግሞ ከሁሉም የረዘመ ፀጉር ነው ያላት።
2
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
ፋሲል አሠፋ (Fasil Assefa)
am
0120_ፀጉር.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0120
asp
ዛማ ፀጉሯን ተጎንጉናለች።
3
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
ፋሲል አሠፋ (Fasil Assefa)
am
0120_ፀጉር.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0120
asp
ባባ ደግሞ ፂም አለው።
4
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
ፋሲል አሠፋ (Fasil Assefa)
am
0120_ፀጉር.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0120
asp
ዛኔሌ ፀጉሯን አበጥራዋለች።
5
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
ፋሲል አሠፋ (Fasil Assefa)
am
0120_ፀጉር.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0120
asp
ታቦ ፀጉሩን ተቆርጧል።
6
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
ፋሲል አሠፋ (Fasil Assefa)
am
0120_ፀጉር.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0120
asp
ቴምባ ፀጉሩን ተላጭቷል።
7
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
ፋሲል አሠፋ (Fasil Assefa)
am
0120_ፀጉር.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0120
asp
አየለ ወደ ት/ቤት ለመሄድ እየተዘጋጀ ነው።
0
CC-BY
Zimbili Dlamini, Hlengiwe Zondi
ሂሩት, መዘምር ግርማ
am
0121_ገንፎ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0121
asp
አባት ለቁርስ ገንፎ እያዘጋጀ ነው።
1
CC-BY
Zimbili Dlamini, Hlengiwe Zondi
ሂሩት, መዘምር ግርማ
am
0121_ገንፎ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0121
asp
‹‹እናቴ ምርጥ ገንፎ ትሰራለች!››አለ አየለ።
2
CC-BY
Zimbili Dlamini, Hlengiwe Zondi
ሂሩት, መዘምር ግርማ
am
0121_ገንፎ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0121
asp
ገንፎ ለአየለ ሀይል ሰጠው።
3
CC-BY
Zimbili Dlamini, Hlengiwe Zondi
ሂሩት, መዘምር ግርማ
am
0121_ገንፎ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0121
asp
ገንፎው ተዘጋጅቷል።
4
CC-BY
Zimbili Dlamini, Hlengiwe Zondi
ሂሩት, መዘምር ግርማ
am
0121_ገንፎ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0121
asp
አባቱ በፍቅር ወተቱን ቀዳለት።
5
CC-BY
Zimbili Dlamini, Hlengiwe Zondi
ሂሩት, መዘምር ግርማ
am
0121_ገንፎ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0121
asp
‹‹አባቴ ይህ ገንፎ ተጨማሪ ስኳር ያስፈልገዋል››አለ አየለ።
6
CC-BY
Zimbili Dlamini, Hlengiwe Zondi
ሂሩት, መዘምር ግርማ
am
0121_ገንፎ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0121
asp
‹‹የናቴ ገንፎ ከአባቴ በጣም የተሻለ ነው››ብሎ አየለ አሰበ።
7
CC-BY
Zimbili Dlamini, Hlengiwe Zondi
ሂሩት, መዘምር ግርማ
am
0121_ገንፎ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0121
asp
‹‹አባቴ እባክህ ተጨማሪ ስኳር ማግኘት እችላለሁ?››አየለ ጠየቀ።
8
CC-BY
Zimbili Dlamini, Hlengiwe Zondi
ሂሩት, መዘምር ግርማ
am
0121_ገንፎ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0121
asp
አባቱ ለአየለ ተጨማሪ ስኳር አደረገለት።
9
CC-BY
Zimbili Dlamini, Hlengiwe Zondi
ሂሩት, መዘምር ግርማ
am
0121_ገንፎ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0121
asp
‹‹ዋው! አባቴ! ገንፎዬ ውስጥ ጨው ጨመርክበት!››
10
CC-BY
Zimbili Dlamini, Hlengiwe Zondi
ሂሩት, መዘምር ግርማ
am
0121_ገንፎ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0121
asp
‹‹አባቴ መቼ ነው እናቴ ቤት የምትመጣው?››
11
CC-BY
Zimbili Dlamini, Hlengiwe Zondi
ሂሩት, መዘምር ግርማ
am
0121_ገንፎ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0121
asp
ማንበብ እወዳለሁ።
0
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ
am
0122_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0122
asp
ለማን ማንበብ እችላለሁ?
1
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ
am
0122_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0122
asp
ህጳኗ ተኝታለች።
2
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ
am
0122_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0122
asp
ለማን ማንበብ እችላለሁ?
3
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ
am
0122_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0122
asp
እናቴ እና አያቴ ምግብ እያበሰሉ ነው።
4
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ
am
0122_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0122
asp
ለማን ማንበብ እችላለሁ?
5
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ
am
0122_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0122
asp
አባቴ እና አያቴ መኪናዋን እየሰሩ ነው።
6
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ
am
0122_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0122
asp
ለማን ማንበብ እችላለሁ? ቁጭ ብዬ ለራሴ አነባለሁ።
7
CC-BY
Letta Machoga
ስሂን ተፈራ
am
0122_ማንበብ-እወዳለሁ.md
global-asp/asp-source
amh
Ethi
asp_0122
asp
ከእንቅልፌ ነቃሁና እሳት አያያዝኩ።
0
CC-BY-NC
Clare Verbeek, Thembani Dladla, Zanele Buthelezi
Dawit Girma
am
0129_ሰነፉ-ታናሽ-ወንድሜ.md
global-asp/sbc-source
amh
Ethi
asp_0129
asp