input
stringlengths
1
130k
ወደ አራት ሺህ የሚጠጉ የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎች በሌላ ቦታ ተጠልለው መመልከታቸውን እኚሁ ተፈናቃይ ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል፡፡
ተፈናቃዩ እንዳሉት በኬንያ ግዛት የአካባቢው አስተዳደር እና የቀይ መስቀል ሰዎች ምግብ እና መጠጥ ለተፈናቃዮቹ ያደሉ ሲሆን ዛሬም ምዝገባ ሲያካሄዱ ውለዋል።
ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ግን ማንም ሰው መጥቶ እንዳልጎበኛቸው አስረድተዋል፡፡
ሌተናል ጄነራል ሀሰን ትላንት በሞያሌ የተፈጠረውን ሁኔታ የተሳሳተ መረጃ በመያዝ የተፈጠረ ግጭት ሲሉ የጠሩት ሲሆን ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በግጭቱ ተሳትፏል የተባለ የአንድ ሻለቃ ጦር ትጥቅ እንዲፈታ ተደርጎ አምስት አባላቱ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የአዲግራት እስርቤት ግድያና ግጭት ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የአውሮፓ ህብረትና የምስራቅ አውሮፓ ሃገራት ትብብር የአውሮፓ ህብረት የህብረቱ አባል ያልሆኑ የምሥራቅ አውሮፓ ሃገራትን ይበልጥ ለማቅረብ እየጣረ ነው ።
በትብብሩ ውስጥ የተካተቱት ከአውሮፓ ህብረት ጋር የሚጎራበቱት የቀድሞዎቹ የሶቭየት ህብረት ሪፐብሊኮች አርመን አዘርባጃን ቤላሩስ ጆርጅያ ሞልዶቫ እና ዩክሬን ናቸው።
ከዚህ ሌላ ህብረቱ በሃገራቱ የሚካሄዱ ተሃድሶ እርምጃዎችንም ያበረታታል ።
የሃሳቡ ጠንሳሽ ፖላንድ ስትሆን ከስዊድን ጋር በጋራ ነበር ሃሳቡን አዘጋጅተው ያቀረቡት ።
የሁለቱ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጎርጎሮሳዊው ግንቦት ሃሳቡን ብራሰልስ ውስጥ ለአውሮፓ ህብረት የአጠቃላይ ጉዳዮችና የውጭ ግንኙነቶች ምክር ቤት አቀረቡ ።
በዓመቱ ግንቦት ፕራግ ቼክ ሪፐብሊክ ውስጥ የህብረቱና የስድስቱ የቀድሞዎቹ የሶቭየት ህብረት ሪፐብሊኮች ትብብር እንቅስቃሴ ተጀመረ ።
የሁለቱ ወገኖች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በትብብሩ ማዕቀፍ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያ ስብሰባቸውን ብራሰልስ ቤልጂግ ውስጥ ታህሳስ ዓም አካሄዱ ።
ከዚያን ጊዜ አንስቶም የትብብሩ አባል ሃገራት መሪዎች በየሁለት ዓመቱ ጉባኤ ያካሂዳሉ ።
የትብብሩ አራተኛ ጉባኤ በወቅቱ የአውሮፓ ህብረት ሊቀ መንበር በላትቪያ ዋና ከተማ ሪጋ ውስጥ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ተካሂዷል ።
የአውሮፓ ህብረት ከ ቱ የምስራቅ አውሮፓ ሃገራት ጋር በመሰረተው ትብብር ሩስያ ደስተኛ አይደለችም ።
ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን በተለያዩ አጋጣሚዎች ቅሬታዋን ከመግለፅ ወደ ኋላ ብላ አታውቅም ።
ትብብሩ እንደተመሰረተ የያኔው የሩስያ ፕሬዝዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቬ ፋይዳ ቢስ ሲሉ አጣጥለውት ነበር ።
ሩስያ ህብረቱ ትብብሩን በሃገራቱ ላይ የተፅእኖውን አድማስ ለማስፋት የሚጠቀምበት መሣሪያ ነው ስትል ስጋትዋን ታሰማለች ።
በሩስያ አባባል ህብረቱ ትብብሩን ለነዳጅ ዘይት ማፈላለጊያ እየተጠቀመበት ነው ።
ከዚህ በተጨማሪም ሩስያ ህብረቱ በተለይ በቤላሩስ ላይ ከመጠን ያለፈ ጫና እያደረገባት ነው ስትልም ትከሳለች ።
ሃገራቱ እንደ ሉዓላዊ ግዛት መውሰድ መያዝ በሚፈልጉት አቋም ላይ ህብረቱ ይጫናቸዋል ስትል በደጋጋሚ ጊዜያት ትወቅሳለች ።
ሆኖም የትብብሩ ሃሳብ አመንጪ ፖላንድ አስተያየቱ ተቀባይነት የለውም ስትል ታጣጥላለች ።
የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ቱስክ በሪጋው ጉባኤ ላይ የሁለቱ ወገኖች ግንኙነት በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ነው የሚናገሩት ።
ትብብራችንም ሆነ የሪጋው ጉባኤ ተለዋዋጭ ውሳኔዎችን የማሳለፍ ዓላማ የላቸውም ወይም ደግሞ ግዙፍ እርምጃዎችንም ለመውሰድ ያለሙ አይደሉም ።
የምሥራቅ አውሮፓ ሃገራት የአውሮፓ ህብረት እሴቶችን የመቀበል ፍላጎት ካሳዩ የራሳቸው ሉዓላዊ ውሳኔ ነው የሚሆነው ።
ማንም ቢሆን ይህን ራሳቸውን የሚመርጡትን መንገድ የማመቻቸት መብት የለውም ።
ከምሥራቅ አውሮፓ ሃገራት ጋር ጉድኝት መፍጠሩ የአውሮፓ ህብረት የማስፋፋፍያ መሣሪያ አይደለም ።
ይህም ህብረቱ የአውሮፓ ህብረት ላልሆነ ሃገር እስከዛሬ ከሰጠው ብድር ከፍተኛው ነው ።
ህብረቱ ከዚህ ቀደምም ለዩክሬን ዩሮ የሚጠጋ ገንዘብ አበድሯል ።
ከትብብሩ አባላት መካከል በተለይ ዩክሬን ጆርጅያና ሞልዶቫ ከህብረቱ ጋር ቅርብ ፖለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ ግንኙነት መፍጠር የሚያስችሉ ስምምነቶች ፈርመዋል ።
ለነዚህ ሃገራትም በሚቀጥሉት ዓመታት እስከ ቢሊዮን ዩሮ የሚደርስ ውረታን ለመሳብ የሚያስችላቸው ሚሊዮን ዩሮ ለመስጠት ቃል ገብቶላቸዋል ።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ ኢራኪል ጋሪባሽዊሊ ዜጎቻቸው በህብረቱ አባል ሃገራት በነፃ እንዲዘዋወሩ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል ።
በብዙ ዘርፎች ጎላ ያሉ ለውጦች አድርገናል ብዬ አስባለሁ ።
እንደሚመስለኝ የጆርጅያ ዜጎች ቪዛ የማያስፈልገው ዝውውር ሊፈቀድላቸው ይገባል ።
ከ ቱ የምስራቅ አውሮፓ ሃገራት አርመንያና ቤላሩስ የሩስያው የዩሮ ኤዥያ የኤኮኖሚ ህብረት አባል ናቸው ።
በአንፃሩ ዩክሬን ጆርጅያና ሞልዶቫ ከህብረቱ ጋር ጥብቅ ግንኙነት መመሥረት ይፈልጋሉ ።
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ ትብብሩ ከሩስያ ጋር ሌላ ግጭት የሚፈጥር እንዳይሆን መጠንቀቅ እንደሚገባ አሳስበው ነበር ።
ዓለም የመካከለኛው ምስራቅ የሠላም ሂደቱና ውድቀቱ በየመሀከሉ ከመታወክ ያላመለጠውና ለ ዓመታት የቆየው የፍልስጥኤም እስራኤል የሠላም ድርድር አደጋ እንዳንዣበበት ተገለፀ።
ሰላማዊ ሰልፈኞች በእስራኤል ሶሪያ ድንበር ግንቦት ለፍልስጤማውያንም ለእስራኤላውያንም ልዩ ቀን ሆኖ ነበር ያለፈው።
በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ በቅርቡ ሕይወቱ ያለፈው ሙዚቀኛው ኤልያስ መልካ በእጅጉ ታስቦበታል።
ኛው አሜሪካ ሳልት ሌክ ሲቲ ላይ እና ኛው በ ኢጣሊያ ቱረን ላይ ነበር የተካሄዱት።
እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ ታዲያ ገና ከጅምሩ ማለት ይቻላል ወቀሳና ነቀፌታም ግን ኣልተለያቸውም።
ከሰብዓዊ መብት ይዞታ አንጻር ሩሲያ በተለይም የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን በመከልከሏ በምዕራባዊያኑ ዘንድ ስትወነጀል ቆይታለች።
በኦሎምፒኩ ዋዜማ በመርዝ በፈጀቻቸው ኣውደልዳይ ውሾች ጉዳይ ሳይቀር ስትኮነን ሰንብታለች።
በተለይም የሲርኮዚያን ብሔራዊ ድርጅት የዛሬ ዓመት ገደማ የሩሲያ ተስፋፊዎች በህዝባቸው ላይ ያፈጸሙትን የዘር ማጥፋት ወንጀል በማውሳት የሶቺ ኦሎምፒክ እንዲሰረዝ ጠይቐል።
በ ዓም በሲርኮዚያኑ መግለጫ መሰረት የሩሲያ ወራሪዎች በነባሩ የሲርኮዚያን ህዝብ ላይ በከፈቱት ዘመቻ በትንሹ ሚሊየን ገደማ ሲርኮዚያንን ፈጅቷል።
እናም ይላል ድርጅቱ ኣውስትራሊያ በ አሜሪካ በ እና ከናዳ በ ዓም እንዳደረጉት ሁሉ ሩሲያም በይፋ ይቅርታ መጠየቅ ይኖርባታል።
የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች በበኩላቸው ሩሲያ በሶቺ ያስገነባችው የኦሎምፒክ መንደር የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃን ያላገናዘበ በመሆኑ ኃላፊነት የጎደለው ነው ሲሉ ይሟገታሉ።
ዓለም ዓቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ግን ግንባታው ምንም ይሁን ምን በሶቺ ኦሎምፒክ ከዝግጅቱ ጀምሮ በመስተንግዶው ጭምር መርካቱን ኣስታውቐል።
ጀርመናዊው የኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚደንት ቶማስ ባህክ በመክፈቻው ስነስርዓት ላይ እንደተናገሩት ሩሲያ ምስጋና ይገባታል ሲሉ ኣሞካሽቷታል።
የመንግስታት መሪዎች ኦሎምፒክን ለፖለቲካ ዓላማቸው መጠቀሚያ ከማድረግ እንዲቆጠቡም ባህክ ኣበክረው ኣሳስቧል።
እናም በኦሎምፒክ ታሪክ ከፍተኛ ወጪ የወጣበት ውድ ኦሎምፒክም ተብሏል።
በሰሜናው ካውካስ ግዛት የጸጥታ ጥናት ተቐም ተንታኝ የሆኑት ቫርቫራ ፓቾሜንኮ በበኩላቸው የ ን ስጋት ይጋራሉ።
የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አኃዱ ያለው በሆኪ የበረዶ ሸርተቴ የሩሲያዋ ዋና ተቀናቃኝ የ አሜሪካ አትሌት ነው።
የአዲስ አበባ ሙስሊሞች ዛሬ ከጁመዓ ሶላት በኋላ በተለይ የሐይማኖት ነፃነት የተደነገገበት አንቀፅ ሃያ ሰባት መጣሱን አዉግዘዋል።
የኢትዮጵያን ሕገ መንግሥት የማስከባሩ ሐላፊነት ከሐገሪቱ መንግሥት ይልቅ የመብት፥
ነፃነት ተሟጋቾችና ሐላፊነት የሚሰማቸዉ ወጣቶች የመሆኑ እንቆቅልሽ ገሐድ እየወጣ ነዉ።
መንግሥት ሕገ መንግሥቱን ጥሶ በሐይማኖታዊ ጉዳያችን ጣልቃ ገብቷል የሚሉት ኢትዮጵያዉን ሙስሊሞችም ሕገ መንግሥቱ እንዲከበር አበክረዉ እየጠየቁ ነዉ።
ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ዝርዝር መግለጫ አውዲዮውን ያዳምጡ።
የሪይክ ማቻር ቃል አቀባይ ቡድናቸው ጥምር መንግሥቱ ውስጥ መግባት እችላለሁ ብሎ እንደማያምን በዚሁ ሳምንት ረቡዕ ዕለት ይፋ አድርገዋል።
ትኩረት በአፍሪቃ በነጻነት ማግስት በእርስ በእርስ ጦርነት በተጠመዱት ተፋላሚዎቿ ጦስ እንደዘበት ግማሽ ሚሊዮን ግድም ነዋሪዎቿን አጥታለች።
በሚሊዮን የሚቆጠሩት ደግሞ ሞት ሰቆቃ እና እንግልትን ፍራቻ ቀዬያቸውን ጣጥለው ተሰደውባታል ደቡብ ሱዳን።
ከስድስት ዓመታት የእርስ በእርስ መቆራቆስ በኋላም በደቡብ ሱዳን ዛሬም ግድያ እና ስደት አላባራም።
ከዚያ በፊት ግን ጥምር መንግሥቱ ይመሰረታል ብለው እንደማያምኑ የዋነኛው ተቃዋሚ ቡድን መሪ የሪይክ ማቻር ቃል አቀባይ ይፋ አድርገዋል።
ተቀናቃኝ ቡድናቱ እጅ እግሬን ሲሉ ግን ወደ ቀነ ገደቡ እየተጠጉ ነው።
እንዲያም ኾኖ የሪይክ ማቻር ቃል አቀባይ ቡድናቸው ጥምር መንግሥቱ ውስጥ መግባት እችላለሁ ብሎ እንደማያምን በዚሁ ሳምንት ረቡዕ ዕለት ይፋ አድርገዋል።
ለተቃዋሚዎችም ጥሪ አስተላልፈዋል እንዲህ ሲሉ፦ እንኳን ደህና መጣችሁ ማለት መራር ጥላቻውን ሁሉ መርሳት እሻለሁ።
ከሦስት ወራት በፊት ስምንተኛ ዓመት የነፃነት ቀንዋን ባሰበችው ደቡብ ሱዳን ውስጥ ተፋላሚዎች የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ለመመሥረት እጅግ ተስኗቸዋል።
ለግንቦት ቀን ዓ ም የያዙት የአንድነት መንግሥት ምሥረታ ቀጠሮ ፈርሶ በስድስት ወራት የተራዘመውም የሚሳካ አይመስልም።
ቀነ ገደቡ እንዲራዘም የተጠየቀው በደቡብ ሱዳን ዋነኛ የተቀናቃኞች መሪ ሪያክ ማቻር ጥያቄ ነበር።
በወቅቱ አዲስ አበባ ውስጥ በተደረገው ስምምነት ለስድስት ወራት የተራዘመውን ቀነ ገደብ የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት ዕውቅና ሰጥቶት ነበር።
ሪያክ ማቻር በቃል አቀባያቸው በኩል ረቡዕ ዕለት እንዳስታወቁት፦ የሣልቫ ኪር መንግሥት የሠላም ሒደቱን በሚፈለገው መንገድ አላስኬደም ሲሉ ወቅሰዋል።
ከአንድ ዓመት በፊት በተፈረመው የሰላም ውል መሠረት ለፕሬዚዳንት ሣልቫ ኪር ታማኝ የኾኑ ሺህ ወታደሮችን ከተቃዋሚዎች ጋር ማቀላቀል የሚለው ይገኝበታል።
ሪይክ ማቻር በመዲናዪቱ ጁባ የሚገኙ ባለሥልጣናት ቃል የገቡትን እየተገበሩ አይደሉም ሲሉም በብርቱ ወቅሰዋል።
የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ከመመስረቱ አስቀድሞም የደቡብ ሱዳን መንግሥት በስምምነቱ መሠረት ቃል የገባውን ሊተገብር ይገባዋል ብለዋል።
እሳቸው ግን እንደምክንያት ያቀረቡት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለሠላም ሒደቱ ማስኬጂያ የገባውን ቃል አለመጠበቁን ነው።
ዩናይትድ ስቴትስ ስምምነቱን ዕውቅና የማትሰጠው ከኾነ ምዕራባውያን ኃይላት ገንዘባቸውን አይከፍሉም።
አደጋ እንዳይደርስባቸው በመስጋት ስማቸውን የሸሸጉ ታማኝኝ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ውስጥ ዐዋቂዎችም በሚባለው ይስማማሉ።
ዩናይትድ ስቴትስ በገንዘብ እጥረትም ኾነ በሌላ ምክንያት የደቡብ ሱዳን የሰላም ሒደት ከእንግዲህ ተሰናክሎ ማየት አትሻም።
የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ለመመስረት የተሰጠው ቀነ ገደብ የሚጣስ ከኾነ ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ እንደምትጥል በመግለጥ ስትዝት ቆይታለች።
ተፋላሚ ኃይላቱ ግን ከዩናይትድ ስቴትስ ዛቻ ይልቅ የተፈራሩት እርስ በእርሳቸው ነው።
ወደ እርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ለመዘፈቅ ግን ብዙም አልቆየች።
ኹለቱም መሪዎች ጎሳዎቻቸውን አስተባብረው እርስ በእርስ ሲገዳደሉ ዓመታትን አስቆጥረዋል።
እስከ አኹንም ድረስ በሀገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት የተነሳ ከ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።
ከሀገሪቱ ሚሊዮን ግድም ነዋሪ መካከል አንድ ሦስተኛው ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሏል።
ሊገባደድ ጥቂት ቀናት በቀሩት ቀነ ገደብ ውስጥ ግን የብሔራዊ አንድነት መንግሥቱን ደቡብ ሱዳን ውስጥ ማቋቋም እንደማይቻል ኹኔታዎች ያመላክታሉ።
የስፖርት ዘጋባዎች ላይ የቀረበው ወቀሳ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ባህል የመድረክ ተውኔት በዶቼቬለ የባህል መድረክ ቴአትር የተለያዩ ባህሎችን በማቀራረብ የሚያበረክተው ድርሻ ላቅ ያለ ነው።
እዚህ ጀርመን ሐገር ቦን ከተማ ውስጥ ዶቼ ቬለ ሬዲዮ ጣቢያ ባዘጋጀው ዓለምአቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ጉባኤ ላይ የታየውም ይህንኑ አባባል ያስረግጣል።
ተውኔቱ አንዲት የ ዓመት ታዳጊ በሆነች አፍሪቃዊት ተማሪ ህልም ዙሪያ ያጠነጥናል።
ካሬምቦ በመጠነኛ ቁሳቁስ አፍሪቃዊ ድባብ የተላበሰው መድረክ ላይ ካሬምቦ ከወላጆቿ በስተግራ ሲል በተነጠፈ ምንጣፍ ላይ ተኝታለች።
እናቷ እና አባቷ ደግሞ ከመድረኩ በስተቀኝ በተመሳሳይ ሁኔታ ተጋደመው እያለሙ ነው።
ከመድረኩ በተቃራኒ አቅጣጫ ከታዳሚያኑ ጀርባ ከሚገኘው ኮምፒውተር በፕሮጀክተር የተለቀቀ የአንድ ቤት ምስልም ግድግዳው ላይ ይታያል።
ኮረብታው ላይ ለብቻው ጉብ ያለ የሳር ክዳን የተላበሰ ጎጆ ነው።
ታሪኩ የሚከናወነው እዚህ ጉብታ ላይ በብቸኝነት በተቀለሰው ጎጆ ቤት ውስጥ ነው ለማለት የታቀደ ይመስላል።
ከመድረኩ በስተግራ በክብ ቅርፅ ተፈልፍሎ የተሰራ የእንጨት ጌጥ በድጋፍ ቆሟል።
መድረኩ መሀል ላይ ደግሞ ከእንጨት ተፈልፍሎ የተሰራ ባለረዥም መደገፊያ ወንበር ተሰድሯል።
የድራማው ደራሲ ኬኒያዊው ክሪስፒን ሙዋኪዲዮ ትዕይንቱን ለምን ከደቡብ አፍሪቃ በተገኘ የሕዝብ መዝሙር መጀመር እንደፈለገ በዚህ መልኩ ይገልፃል።