input
stringlengths
1
130k
በመጀመሪያ ደረጃ የመዝሙሩ ዓላማ ሰዉ ጉባኤው ላይ በንግግር ብቻ ሊሰላች ስለሚችል እንዲነቃቃ ለማድረግ ነው።
ይህ በራሱ በተውኔቱ ውስጥ ሙዚቃ ለመጠቀሜ ሌላኛው ምክንያት ነው።
ክሪስፒን አያይዞም ይህ የዚምባብዌ ሕዝባዊ መዝሙር ወንዶች ወደ ጦርነት ሲሄዱ ድል አድርገው በሠላም እንዲመለሱ ሴቶች ምኞታቸውን የሚገልፁበት ነው ብሏል።
በተውኔቱ ውስጥ ከተሳተፉት ተዋንያን ከሁለቱ በስተቀር ሌሎቹ በአጠቃላይ መድረክ የመጀመሪያቸው በመሆኑ እንዲበረታቱ ለማድረግም እንደተጠቀመበት አክሏል።
ተዋንያኑ ቀደም ሲል ያደመጥነውን ሕዝባዊ መዝሙር እየዘመሩ እና ከመሀከላቸው አንዱ ከበሮ እየደለቀ ወደ መድረኩ ብቅ ሲሉ ታዳሚያኑ በአግራሞት መመልከታቸውን ቀጠሉ።
እናም አምስቱ ጋዜጠኛ ተዋንያን ወደ መድረኩ ተጠግተው የበማድመጥ ድራማ የካሬምቦ ህልምን ያቀርብላችኋል እንኳን ደህና መጣችሁ
ካሬምቦ እና ወላጆቿ ወለሉ ላይ ግራ እና ቀኝ ተጋድመዋል።
እናም ፈራ ተባ እያለች አባዬ ለምንድን ነው ትምህርቴን እንድቀጥል የማታደርገኝ
አሁን እንደውም እናትሽን መርዳት ነው ያለብሽ በይ ወደ እንቅልፍሽ ተመለሺ ሲሉ ይቆጧታል።
እናት ወ ሮ ሊፒ ህፃኑን ሲያባብሉ አቶ ዱሩ ፊታቸውን በኬሻ ባርኔጣ ሸፍነው ተመልሰው በመተኛት ማንኮራፋት ይጀምራሉ።
ከአፍታ በኋላ ከበሮው በድንገት እና በፍጥነት መደለቅ ሲጀምር ህፃኑ ማልቀሱን ይቀጥላል እናት አባት እና ካሬምቦ ከመኝታቸው ተነስተው ይቆማሉ።
አባትየው ልጃቸው ምክር ልትለግሳቸው መጣሯን ልጅ ለእናቷ ምጥ አስተማረች ከሚለው ብሂል ጋር ያዛመዱት ይመስላል።
እናም አሁን በቁጣ ተውጠው ሆስፒታሉ ሩቅ መሆኑን በመግለፅ እንደውም ህፃኑን አዲስ ወደ መጡት ባለውቃቢ መውሰድ እንዳለባቸው አስረግጠው ይናገራሉ።
እናም ወደ መድረኩ ግራ እና ቀኝ በፍጥነት እየተመላለሱ በቃሽ
አስተማሪዬ ይህን አለ አስተማሪዬ ያን አለ ሴትዮ ተነሽ ወደ ባለውቃቢው ዘንድ እንሂድ ይላሉ።
የተውኔቱ ደራሲ እና ተባባሪ አዘጋጅ ኬኒያዊው ክሪስፒን ሙዋኪዲዮ ተውኔቱ በመክፈቻው ላይ ከሰማነው መዝሙር ባሻገር ሌሎች ባህላዊ አላባዎችን አካቷል ይለናል።
ሌላ ደግሞ አባትየው ሴት ልጁ ከትምህርት ቤት ቀርታ ቤት ውስጥ እንድትወሰን የመፈለጉ ሁኔታ አለ።
ይህ በእርግጥ እየተቀየረ ቢሆንም በአብዛኛው የአፍሪቃ ገጠሮች አሁንም ድረስ ያለ ነገር ነው።
ደሀዎች አረ እንደውም ሀብታሞች ጭምር ከሳይንስ እና ዘመናዊ ህክምና ይልቅ በባለውቃቢ እና በጥንቆላ የማመን ሁኔታ ይታይባቸዋል።
በእርግጥም የካሬምቦ ወላጆች የታመመ ህፃን ልጃቸውን ይዘው ወደ ባለውቃቢው ቤት ሲያመሩ ይታያል።
በከበሮው ምት መሀል ባለውቃቢው ከእንጨት ተፈልፍሎ የተሰራው ዥንጉርጉር ጌጥ ላይ አተኩሮ ግራ በሚያጋባ ቋንቋ ማውራት ይጀምራል።
ተዋንያኑ ከመድረኩ በስተግራ በድጋፍ የቆመችው ክብ የእንጨት ፍልፍል ዥንጉርጉር ምስልን ዙሪያዋን እየተሽከረከረ ነው የሚያወራው።
በየመሀከሉ ይህንኑ ጭራ ሄድ መለስ እያለ ክቧ እንጨት ላይ ነስነስ ያደርጋል።
ለካሬምቦ ወላጆች ጀርባውን እንደሰጠ ሁለት ሰዎች ይታዩኛል እንደውም ህፃን ልጅ ይዘዋል ይላል።
በእርግጥ የካሬምቦ ወላጆችን ቀደም ብሎ ቢያያቸውም ሳይመለከታቸው እንደተገለፀለት አድርጎ ነው ለማስመሰል የሞከረው።
አባትዬው ጉሮሮዋቸውን ስለው በመሽቆጥቆጥ ታላቁ ሚዛንጃ ሲሉ አጎንብሰው ይጣራሉ።
አባትየው አሁንም አቀርቅረው ታላቁ ሚዛንጃ ልጃችን ለምን የሆድ ቁርጠት እንደያዘው ሊነግሩን ይችላሉ
ባለውቃቢውም ልጃቸው የታመመው ወንድ ልጅ በመውለዳቸው ጎረቤታቸው ቅናት ስለያዘው እንደሆነ ይጠቅሳል።
በዚህ ጊዜ ባለውቃቢው ሚዛንጃ ታዳሚውን ሳቅ በሳቅ ያደረገ ያልተጠበቀ ጥያቄ ያቀርባል።
እዚህ ላይ ተውኔቱ አፍሪቃ ውስጥ ጎጂ ልማዶችና እምነቶች ኅብረተሰቡን ምን ያህል እየጎዱት እንደሆነ ለማሳያነት የተጠቀመበት ነው።
ልክ እንደሌላው የጥበብ ዘርፍ ሁሉ ተውኔትም የተለያዩ ማኅበረሰቦችን ለማገናኘት ታላቅ ሚና ይጫወታል።
እንደ ጭፈራ ሽለላ ቀረርቶ ዘፈን የመሳሰሉትን የተውኔት አላባዎች ማየት ይቻላል።
በእርግጥ ተውኔት አፍሪቃ ውስጥ ያን ያህል በተገቢው ሁኔታ ጥቅም ላይ አልዋለም።
በማድመጥ መማር የሬዲዮ ድራማም እንደዛው በመጀመሪያ የሚፃፈው በእንግሊዘኛ ሲሆን በኋላ ላይ ወደ አምስት የተለያዩ ቋንቋዎች ይተረጎማል።
የበማድመጥ መማር መርሀ ግብር ትምህርት ለአፍሪቃእድገትቁልፍሚናእንዳለው በማመን ኅብረተሰቡን እያዝናና ማስተማርን ዓላማው አድርጎ የተነሳ ነው።
የካሬምቦ ወላጆች ባለውቃቢው ምንም የማያውቅ መሆኑ የገባቸው በኋላ ላይ እንደሆነ በመጥቀስ ይሳሳቃሉ።
ህፃኑ ወንድሜ የታመመው ባልታጠበ እጅ ስንነካው ባክቴሪያ እና ጀርሞች ወደ ሆዱ ገብተው ነው ትላቸዋለች።
አባት እንግዲያውስ ማንም ሰው ቢሆን ልጄን ከእንግዲህ እጁን ሳይታጠብ እንዳይነካ ሲሉ በማስጠንቀቅ ጎመን በጤና ከእንግዲህ ባክቴሪያ አልፈልግም ሲሉ ይሄዳሉ።
ከአፍታ በኃላ ግን ከአንድ ባለፀጋ ጋር በስካር መንፈስ ተውጠው እየተወዛወዙ ወደ ጎጆው ይገባሉ።
በጣም ወሳኝ ሰው ይዤ መጥቻለሁ አታፍጪብኝ ሂጂና ምግብ አምጪ ሲሉ ይጮሃሉ።
እንግዳው ገንዘብ ችግር ሊሆን አይችልም ችግር ሴቶች ናቸው ሲሉ ይሳለቃሉ።
በማከልም ካሬምቦን ለማግባት ለባለቤትዎ ገንዘብ ሰጥቼዋለሁ ሲሉ እየተንተባተቡ ለማብራራት ይሞክራሉ።
እናት ይናደዳሉ ከትምህርት ቤት በጥሩ ውጤት በማለፏ ደስ ብሏት የመጣችው ካሬምቦ የሰማችውን ነገር ማመን አቅቷት ትጮሃለች።
እናት አባት እና ካሬምቦ ከእንቅልፋቸው ሲነቁ የሆነው ነገር ሁሉ ለካ ህልም ነበር።
አባት ልጄ ትምህርቷን መቀጠል አለባት ብለው ቃል ሲገቡ የካሬምቦ ህልም የተሰኘው አጠር ያለ የመድረክ ተውኔትም ይፈጸማል።
ኤቦላ ከበሽታው የተረፉትን መደገፍ የኢቦላ ተዛማች በሽታን ተቋቁመው የተረፉ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ መገለል እና አድልዎ ይገጥማቸዋል።
ብዙዎቹ ከዚህ በሽታ የተረፉ ሰዎች ወዳጆቻቸው ከእነሱ ጋር ምንም ነገር ማድረግ እንደማይፈልጉ ይገነዘባሉ አንዳንዶቹ እንደውም ሥራቸውን ሁሉ ያጣሉ።
ስለዚህም ከኢቦላ በሽታ የተረፉ ሰዎች የኢቦላ ተሐዋሲ ምልክቶች ከሰውነታቸው ላይ ከጠፉበት ጊዜ አንስቶ ቢያንስ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት ኮንዶሞችን ሊጠቀሙ ይገባል።
ከኢቦላ በሽታ የተረፉ ሰዎች ደም በኢቦላ ተሐዋሲ ዳግም እንዳይጠቁ የሚያስችሉ የሰውነት በሽታ ተከላካዮችን የያዘ ነው።
እነዚህ የበሽታ ተከላካዮች የኢቦላ ኅመምተኞችን ለመርዳት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።
እጅግ በጠና ኅመም ተሠቃይተዋል ብዙዎቹ በተሐዋሲው የቤተሰብ አባላቸውን አጥተዋል።
ውጥረት በቡሩንዲ የጦር አዛዡ የንቅናቄው ዋንኛ ዓላማ በየቀኑ ንኩሩዚዛን በመቃወማቸው ብቻ በየጎዳናው ይገደላሉ ያሏቸውን ዜጎች ደህንነት ማስጠበቅ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሜይ የገጠማቸው ፈተና ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
በቴክኖሎጂ ምጥቀት ወደ አንድ መንደርነት በተቀየረችው ዓለም ኮሮና ነግሶ እንቅስቃሴን ገቶ ሰዎችን አስጨንቆና አስጠብቦ ዓለምን እያዳረሰ ነው።
ሲከሰት የቻይና ችግር ብቻ ተደርጎ ችላ የተባለው ኮሮና አሁን በተለየ አውሮጳ እና ዩናይትድ ስቴትስን ብዙ ዋጋ እያስከፈለ ነው።
ተህዋሲው በቴክኖሎጂ በሃብት እና በእውቀት የተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛሉ የሚባሉትን የበለጸጉ ሃገራት ገመና አደባባይ አስጥቷል።
ለሌላ ይተርፉ የነበሩ ሃገራት ዛሬ በህክምና መሳሪያዎች እና በቁሳቁስ እጥረት እየተቸገሩ ነው።
ከመካከላቸው ልዕለ ኃያሏ አሜሪካ ከአውሮጳ ኢጣልያ እንዲሁም ከእስያ ኢራን ይገኙበታል።
በአሁኑ ጊዜ ኮሮና በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ተጽእኖ ያላሳደረበት መንግሥትም ሆነ ሰው የለም ማለት ይቻላል።
መንግሥታት የበሽታውን ሥርጭት ለመቀነስ ልዩ ልዩ ገደቦችን እና ክልከላዎችን ተግባራዊ እያደረጉ ነው።
ድንበር የዘጉ የአውሮፕላን በረራ ያቆሙ ከቤት አትውጡ አንስቶ ህብረተሰቡ አካላዊ ርቀትን እንዲጠበቅ ትዕዛዝ ያሳለፉ በርካታ ሃገሮች ናቸው።
በኮሮና ተህዋሲ የተያዙ ሰዎች በተገኙባት በኢትዮጵያም ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃዎች ተወስደዋል።
የኢትዮጵያ ዝግጅት እና የበሽታው ሥርጭት የዛሬው እንወያይ የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ናቸው።
የዜና መጽሔት የካቲት ዓ ም ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ቱርክ እስራኤልና ሩሲያ በሥምምነቱ መሠረት እስራኤል ጦሯ ለገደላቸዉ ቱርካዉያን እና አሜሪካዊ ቤተሰቦች ሚሊዮን ዶላር ካሳ ትከፍላለች።
ቱርክ ለፍልስጤሞች በእስራኤል ወደብ በኩል የርዳታ ምግብ መድሐኒትና ቁሳቁስ ትልካለች።
ሌዲ ለይላ የተባለቸዉ የቱርክ መርከብ ሺሕ ቶን የሚመዝን የመጀመሪያዉን የርዳታ ቁሳቁስ ጭና ባለፈዉ አርብ መሕለቋን አሽዶድ ወደብ ጥላለች።
የዋሽግተን ለንደን ፓሪስ መሪዎች እንደየራሳቸዉም እንደየቀዳሚዎቻቸዉም ምንም አለማዳርጋቸዉ ለምንአንዳሰኘ ለምዕራባዉያን ያደረዉ የቱርክ ጦር የሩሲያን የጦርጄት መትቶ ጣለ።
እርምጃዉ ኤርዶኸንን ሱልጣን አብዱልመጂድ ቀዳማዊን ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቱንን ባንፃሩ ንጉስ ኒኮላስ ቀዳማዊን አሰመስሏቸዉነበር።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በዘር በሐይማኖት በፖለቲካ መርሕ በሥልጣን ዘመንም ከመሐመድ ዓሊ ፓሻ ጋር ጨርሶ አይገናኙም።
የሚመሯት ሐገር ግን የቱርኩ ሰፊ ግዛት አካል እንደነበረች እዉነት ነዉ።
የጦር ሐይሏ ጥንካሬ የሐብቷ ብዛትም ከመሐመድ ዓሊ ግዛቶች ቢበልጥ እንጂ አይተናነስም።
ጠብ ዉዝግብ ፉከራቸዉ እንዳልጠቀመና እንደማይጠቅማቸዉ ተረድተዉ የሚጠቅማቸዉን ለማድረግ ተስማሙ።
ከቱርክ ጋር ሥላደረግነዉ ሥምምነት ለዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ኬሪ አስረድቻቸዋለሁ።
ባንድ በኩል ግንኙነቱን ወደነበረበት የሚመልስ በሌላ በኩል ደግሞ ለእስራኤል ምጣኔ ሐብት ከፍተኛ ጥቅም አለዉ።
በሥምምነቱ መሠረት እስራኤል ጦሯ ለገደላቸዉ ቱርካዉያን እና አሜሪካዊ ቤተሰቦች ሚሊዮን ዶላር ካሳ ትከፍላለች።
የቱርኩ ጠቅላይ ሚንስትር ቢናሊ ዪልዲሪም እንዳሉት ቱርክ ከእስራኤል ጋር ያደረገችዉ ሥምምነት ለፍልስጤሞች ምግብና ቁሳቁስ በማቀበል ብቻ አይቆምም።
በእስራኤል ከበባና ማዕቀብ ለሚማቅቀዉ የጋዛ ሕዝብ ዘመናይ ሆስፒታል እና መኖሪያ ቤት ለመገንባትም አቅዳለች።
በሥምምነቱ መሠረት ጋዛ ዉስጥ ሁለት መቶ አልጋ ያለዉ ዘመናይ ሆስፒታል እናስገነባልን።
ከዚሕም በተጨማሪ የቱርክ የቤቶችና የግንባታ መስሪያ ቤት ጋዛ ዉስጥ አዳዲስ መኖሪያ ሕንፃዎችን ይገነባል።
እስራኤል ሙስሊሞች ከሚበዙበት ሐገራት ሁሉ ጠንካራ ግንኙነት የነበራት ከቱርክ ጋር ነበር።
ባለፉት ስድት ዓመታት ግን የሁለቱ ሐገራት ግንኙነት በጠብ ዉግዘት እሰጥ አገባ ተቀይሮ ነበር።
በእስራኤል የቀድሞዉ የቱርክ አምባሳደር ኦጉዝ ሴሊኮል እንደሚሉት ወደ ቱርክ የሚጓዘዉ እስራኤላዊ ሐገር ጎብኚ ቁጥርም ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።
ሥምምነቱ የእስራኤል ሐገር ጎብኚዎችን ቁጥር በ ወደነበረዉ ያደርሰዋል ተብሎ ይታሰባል።
ብዙ ታዛቢዎች እንደሚሉት ከምጣኔ ሐብቱ ይልቅ ድርድር ዉይይት ሰላም በማያዉቀዉ ምድር በድርድር ዉይይት ጠብን የማርገቡ አስትምሕሮ ነዉ የሚጎላዉ።
ቱርክ በጥቁር ባሕር ከምትዋሰናት ሐይል ጎረቤትዋ ሩሲያ ጋር ካለፈዉ ሕዳር ጀምሮ የገጠመችዉን ጠብ ለማርገብም ተስማምታለች።
ባለፈዉ ዓመት ይሕን ጊዜ ከ ሚሊዮን በላይ ሩሲያዊ ሐገር ጎብኚ ቱርክ መዝናኛ ሥፍራዎች ይርመሰመስ ነበር።
ዘንድሮ ግን ሩሲያ ቱርክን ለመበቀል በጣለችዉ ማዕቀብ ምክንያት አንድም ሩሲያዊ ሐገር ጎብኚ ወደ ቱርክ ዝር አላለም።
የቱርክና የሩሲያ የንግድ ልዉዉጥ በወር በአማካይ ከ ሚሊዮን በላይ ነበር።
የአዉሮጳ ሕብረትና ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያ ላይ ማዕቀብ ከጣሉ ወዲሕ ደግሞ የሁለቱ ሐገራት የንግድ ልዉዉጥ አሻቅቦ ነበር።
ሁለቱ ሐገራት ግንኙነታቸዉን ወደነበረበት ለመመለስ ባለፈዉ ሳምንት ከተስማሙ በኋላ የቱርኩ ጠቅላይ ሚንስትር ቢናይሊ ዪልዲሪም ከእንግዲሕ ይለወጣል ብለዋል።
ፕሬዝደንት ጠይብ ኤርዶኻን ከአንካራ ቭላድሚር ፑቲን ከሞስኮ ይወራወሩ የነበሯቸዉ ቃላት በ ክሪሚያን ያነደደዉ ጦርነት ከመለኮሱ በፊት የነበረዉን ድባብ አስታዋሽ ነበር።
ለሞቱ የሚያጣጥረዉን የኦስማን አገዛዝና ሞስኮ ላይ አዲስ የጎለበተዉ ሐይል የገጠሙትን ዉጊያ ሁለቱንም የሚያዳክም በመሆኑ ለለንደንና ለፓሪስ ሰርግና ምላሽ አይነት ነበር።
አትራፊዎቹ እንደገና ኋላ የዓለም ልዕለ ሐያልነቱን የተቆጣጠሩት የለንደን ፓሪስ ገዢዎችና ተከታዮቻቸዉ ናቸዉ።
የሩሲያ ማዕቀብ ቱርክን ሲሸንቁጣት ግን ዞር ብሎ ያያት የለም።
ይላሉ ሩያዉያን ከሚዘወትሩት መዝኛ ስፍራ ያንዱ አካባቢ ታክሲ ነጂ።
የቱርክ ገበያ ማጣት ለምዕራባዉያን መገናኛ ዘዴዎች ከጥሩ የዜና ርዕሶች አንዱ ነዉ የሆነዉ።
ሌላዉ ቱርክ መሸበሯ ወይም ከመቶ ዓመት በፊት አርመኖችን መግደሏ ከዚሕ ካለፈ የቱርክ መንግሥት ሰብአዊ መብት መርገጡ ነበር የምዕራባዉያን ትኩረት።
ለፕሬዝደንት ፑቲን በላኩት ደብዳቤ በተፈጠረዉ ነገር ጥልቅ ሐዘን የተሰማን መሆኑን ገልጫለሁ።
ለጤናማ አኗኗር አልክሆል መጠጥ እና ትንባሆ አይመከሩም አውዲዮውን ያዳምጡ።