input
stringlengths
1
130k
ኢትዮጵያ የአዲግራት እስርቤት ግድያና ግጭት የከተማይቱ ነዋሪዎች የሟችና የቁስለኛ ቤተሰቦች እንደሚሉት ግጭቱ የተቀሰቀሰዉ በስፖርት ዉድድር ሰበብ ነዉ።
የከተማይቱ ነዋሪዎች የሟችና የቁስለኛ ቤተሰቦች እንደሚሉት ግጭቱ የተቀሰቀሰዉ በስፖርት ዉድድር ሰበብ ነዉ።
አረና ትግራይ የተባለዉ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ግን በትግራይ ክልል በሚገኙ እስር ቤቶች ዉስጥ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈፀማል ባይ ናቸዉ።
ባለፈዉ ዕሁድ ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ቢያንስ አስር የአዲግራት ወሕኒ ቤት እስረኞች ወዳልታወቀ ሥፍራ መወሰዳቸዉንም የፓርቲዉ መሪ አስታዉቀዋል።
የወሕኒ ቤቱ አዛዦችና የምስራቃዊ ትግራይ የፀጥታ ኃላፊዎች ስለጉዳዩ ለመናገር ፈቃደኛ ዓይደሉም ወይም አልተገኙም።
ተመሳሳዩን እርምጃ ለመድገም የሰጠችው ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ቀርተውታል፡፡
ያኔ ወደ ኢትዮጵያ በተመለሱ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን የስነልቦና እና ማህበራዊ ጉዳት ባለሙያዎች ጥናት አካሄደውበታል፡፡
በስነልቦና እና ማህበራዊ ቀውስ እንደተጠቁ ተደርሶበታል ታህሳስ ዓ ም፡፡
የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ማስተናገጃ ግቢ ውስጥ ከሳዑዲ አረቢያ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ተሰብስበዋል፡፡
ከእነርሱ ውስጥ አንዷ የሆነችው ዘይነባ ከሰሜን ኢትዮጵያ ወሎ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የተጓዘች ነበረች፡፡
ያኔ እምባዋን እያዘራች ለዶይቸ ቨለ እንደዚህ የሚሆን ስላልመሰለኝ ነው፡፡
የዘይነባ ድምጽ በሳዑዲ አረቢያም ሆነ በመካከለኛው ምስራቅ በቤት ሰራተኝነት የሚያገለግሉ ኢትዮጵያውያንን ስሜት የሚወክል ይመስላል፡፡
ዶ ር አበባው ጥናታቸውን ያከናወኑት የዓለም ጤና ድርጅት ያስቀመጠውን የአእምሮ ደህንነት መለኪያ ተጠቅመው ነው፡፡
በጣም የተለያዩ ግፎች ይደራረቡና ይከማቹና መጨረሻ ላይ ጠብቀው የሄዱት ነገር አለ አይደል
በገንዘብም የተሻለ ይዞ መምጣት በኑሮም የተሻለ መኖር ቤተሰብን መደገፍ እንዲህ አይነት የጠበቋቸውን ነገሮች አለማግኘት የሚያስከትለው ነገር ጭንቀት ነው፡፡
ራስን ዝቅ አድርጎ የማየት ራስን ተጠያቂ አድርጎ የመውሰድ ያልተሳካላት ሰው አድርጎ ራስን የመውሰድ ነገር ይታይባቸዋል ፡፡
ለምሳሌ ራሴን አመመኝ ይፈልጠኛል የምግብ ፍላጎቴ ቀነሰ ጨጓራዬን አመመኝ እንደዚህ እንደዚህ የሚሉ መገለጫዎች ውስጥ ይገባሉ፡፡
ሌላው በአብዛኛው ከሰዎች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነትም የመራቅ ነገር ይሆናል ፡፡
ለእነሱ የወጣው ያልተመለሰ ገንዘብ አለ ቤተሰብ ከእነርሱ የሚጠብቀው ብዙ ነገር አለ፡፡
የመሸማቀቅ የመሳቀቅ ስሜቶች ሁሉ ከዚህ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ ሲሉ ዶ ር አበባው በጥናታቸው ያስተዋሉትን የስነልቦና ችግር ከእነመንስኤው ያስረዳሉ፡፡
የአእምሮ ህምሞችን በሁለት የሚከፍሉት ዶ ር አበባው አሳሳቢው ጠንከር ያለ ቀውስ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
በእዚህ የተጠቁቱ ራሳቸውን የማጥፋት ስሜት በየጊዜው የሚመጣባቸው እንደሆኑ ይገልጻሉ፡፡
በጥናቶቻቸው ካስተዋሏቸው ውስጥ በመሀል ለየት ያለ ሀሳብ እየመጣ የሚረብሻቸው ይገኛሉ፡፡
ለምሳሌ አንዲቱ ልጅ በቁጥሩ ከሚገለጸው ውጭ በሀተታዊ ጥናት ከገለጸችው ነው የምነግርህ፡፡
የቀን ህልም ወይም የቀን ቅዥት የሚሉት ዓይነት ውስጥ ይገባሉ፡፡
አንዳንዶቹ እኮ አየር ማረፊያ ላይ ጸጉራቸውን እየነጩ የሚቆሙ አሉ፡፡
በተመሳሳይ መልኩ የሳዑዲ ተመላሾች ላይ የደረሰውን ማህበራዊ ጥናት ያጠኑት አቶ ደሳለኝ ቢራራ ስደተኞቹ ማህበራዊ ቀውስ እንደገጠማቸው በጉልህ ማስተዋላቸውን በጥናታቸው አካትተዋል፡፡
በዚያን ምክንያት ብዙዎቹ አብሮ ከመኖር ይልቅ እንደገና የመሰደድ ዝንባሌ ነበር የታየባቸው፡፡
ሁለተኛው ደግሞ ቤተሰብ የሚጠብቃቸው አምጥተው ያሳልፉልናል ለችግራችን ደራሽ ይሆናሉ ገንዘብ ልከው እኛን ይረዱናል በሚል ነው፡፡
እንዲህ አይነትማህበራዊ ችግር የሚገጥማቸው ተመላሾች ሶስት አይነት አማራጮችን አንደሚጠቀሙ አቶ ደሳለኝ በጥናታቸው ጠቁመዋል፡፡
አጥኚዎቹ በቀደምት የሳዑዲ ተመላሾች ላይ በታዘቡት ላይ ተመስርተው የስነልቦናም ሆነ ማህበራዊ ቀውስ እንዳይገጥማቸው በቂ ትኩረት ተሰጥቶ አልተሰራም ይላሉ፡፡
ተመሳሳይ ችግር በድጋሚ እንዳይከሰት ቅድመ ዝግጅት መደረግ እንዳለበት ይመክራሉ፡፡
ስፖርት ስፖርት መጋቢት ቀን ዓ ም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ባደረጓቸው ውድድሮች ትናንት ድል ቀንቷቸዋል።
ጀርመን ውስጥ በሁለት ከተሞች ማለትም በመዲናዪቱ በርሊን የግማሽ ማራቶን በቦን ደግሞ ኪሎ ሜትር ፉክክር ተደርጓል።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ባደረጓቸው ውድድሮች ትናንት ድል ቀንቷቸዋል።
ጀርመን ውስጥ በሁለት ከተሞች ማለትም በመዲናዪቱ በርሊን የግማሽ ማራቶን ሲከናወን በቦን ደግሞ የግማሽም የ ኪሎ ሜትርም ውድድር ነበር።
የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል አትሌቶቹን በውድድር ቦታው በመገኘት አነጋግሯቸዋል።
ወደዚያ ከማቅናታችን በፊት ግን ቦን ከተማ ውስጥ ወደተደረገው የማራቶን ሩጫ እንሻገር።
ትናንት ቦን ከተማ ውስጥ ከ ሺህ በላይ ታዳሚዎች በተገኙበት የማራቶን ሩጫ ሺህ አትሌቶች ተሳታፊ ነበሩ።
በውድድሩ ያለፈው ዓመት አሸናፊ ኬኒያዊው ኤድዊን ኮስጌይ አለያም ኢትዮጵያዊው ዘመኑ ወቅርነህ እንደሚያሸንፉ በብዙዎች ዘንድ ተጠብቆ ነበር።
ትናንት የቦን ከተማ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የአየር ጠባዩ አመቺ የሚባል ነበር።
ዘመኑ ከኬንያዊው አሸናፊ ደቂቃ ከ ሰከንድ ዘግይቶ ነበር የገባው።
በቦን ማራቶን የሴቶች ፉክክር አሸናፊ የኾነችው ኬንያዊቷ ፕሪስካ ኪፕሮኖ ናት።
ትናንት ለስለስ ባለው የቦን ከተማ ጸሓያማ ቀን የማራቶን ሩጫ ሲከናወን ነፋሻማ በሆነው በርሊንም የግማሽ ማራቶን ፉክክር ነበር።
በበርሊኑ ኛው የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ከ ሃገራት የተውጣጡ አትሌቶች ተሳታፊ ነበሩ።
ሺህ የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎችም ውድድሩንም በተለያዩ አውራጎዳናዎች በመታደም ተከታትለዋል።
ኪሎ ሜትር የፈጀው ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበሩ አትሌቶችንም አበረታትተዋል።
ከበርሊን ግማሽ ማራቶን እና ከቦን የማራቶን ሩጫ ውድድር ባሻገር በሮም ከተማም በዝናማማ የአየር ጠባይ ኢትዮጵያውያን አሸናፊ ኾነዋል።
በወንዶች ፉክክር በመሮጥ ኢትዮጵያዊው አትሌት ሹራ ቂታታ አሸናፊ ለመሆን ችሏል።
ሲከታተሉት የነበሩት ሁለት ኬንያውያን አትሌቶች ዶሚኒክ ሩቶ እና ቤንጃሚን ቢቶክ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ አግኝተዋል።
በሴቶች ተመሳሳይ ውድድርም አሸናፊ የኾነችው ኢትዮጵያዊቷ ራህማ ጡሳ ስትሆን ውድድሩን ለማጠናቀቅ የፈጀባት ጊዜ ነበር።
ኢትዮጵያውያቱ አትሌት መስተዋት ታደሰ እና አበባ ተክሉ ተከትለዋት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ወጥተዋል።
የኢትዮጵያውያኑ የትናንቱ አመርቂ ውጤት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት በከተማዪቱ የነበረውን ድል አስታውሷል።
ትናንት በካሊፎርኒያ በተከናወነው የ ሜትር የሩጫ ፉክክር የኦሎምፒክ የብር ሜዳሊያ ባለቤቱ ኢትዮጵያዊው አትሌት ደጀን ገብረመስቀል ለአምስተኛ ጊዜ አሸናፊ ኾኗል።
እግር ኳስ በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ የእግር ኳስ ግጥሚያ ትናንት አርሰናል ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ባደረገው ግጥሚያ ሁለት እኩል በመለያየት ነጥብ ጥሏል።
አርሰናል ነጥብ ይዞ ከሚገኝበት ስድስተኛ ደረጃ ወደላይ ፈቅ ለማለት ቀሪ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎቹን በሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ይጠበቅበታል።
ያም ብቻ አይደለም ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች የቀሩት ማንቸስተር ዩናይትድ እንዲሸነፍም መጸለይ አለበት።
ማንቸስተር ዩናይትድ ነገ የሚጋጠመው ሰባተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ኤቨርተን ጋር ነው።
የፊታችን እሁድ የሚገጥመው ደግሞ ነጥብ ይዞ የደረጃ ሠንጠረዡ ጥግ ኛ ላይ ከሚያጣጥረው ሰንደርላንድ ጋር ነው።
በትናንቱ ጨዋታ የደረጃ ሰንጠረዡ ታች የሚገኙት ሚድልስቦሮው እና ስዋንሲ ሲቲም ያለምንም ግብ ተለያይተዋል።
የቦን ማራቶን የመጨረሻ መስመር ላይ ታዳሚያን አሸናፊውን ሲጠባበቁ ቅዳሜ ዕለት ኤቨርተንን ለ ያሸነፈው ሊቨርፑል ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
መሪው ቸልሲ በክሪስታል ፓላስ ለ በመረታቱ በ ነጥቡ ተወስኗል በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኘው ቶትንሀም አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ይቀረዋል።
በጀርመን ቡንደስሊጋ ባየር ሙይኒክ ነጥብ እና የተጣሩ ግቦች ይዞ እየገሰገሰ ነው።
ዶርትሙንድ ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው የሰሜን ጀርመኑ ሐምቡርግ ጋር የሚያደርገው ግጥሚያም ነገ ማታ በተመሳሳይ ሰአት ይከናወናል።
ኤኮኖሚ ይነጥፋል የተባለው የስዑዲ ሃብት የሳውዲ አረብያ የተፈጥሮ ሃብት ሃገሪቱን ባለፀጋ እና ተሰሚነት ያላት አገር እንድትሆን አድርጓል ።
ይነጥፋል የተባለው የስዑዲ ሃብት በዓለም የገንዘብ ድርጅት ትንበያም የሃገሪቱ የሃብት ክምችት ከጥቂት ዓመታት በኋላ መንጠፍ ይጀምራል።
የዛሬዉ ጥያቄ የአያቶላሕ ሩሑላሕ ሆሚኒዋ ታላቅ ሠይጣን የድብቅ ዲፕሎማቶች፥
የእስራኤል ኛ ዓመት ምስረታ ቤተ እስራኤላዉያን እስራኤል የተመሰረችበት ኛ ዓመት ነገ በይፋ እንደሚከበር ተገለፀ ።
በሺዎች በሚቆጠሩ በእስራኤል ከተሰዉት መካከል በአሸባሪ ጥቃትና በጥበቃ ስራ ላይ ሳሉ በደረሰ አደጋ የተሰዉ ቤተ እስራኤላዉያንም ይገኙበታል።
ዛሬ ሲደረግ የዋለዉ የመታሰብያ ሥነ ስርዓት ምሽት ላይ የተሰዉ የእስራኤል ጀግኖችን በሚከብረዉ ችቦ ማብራት ስነስርዓት ይጠቃለላል።
በሌላ በኩል ሃገራችንን ወረዋል ሲሉ በሚከሱት ፍልስጤማዉያን ጥያቄ የእስራኤል ሰባኛ ዓመት ምስረታ ጥላ አጥልቶበት ይገኛል።
በእስራኤል ስለ ኛ ዓመት ምስረታ ክብረ በዓል በተመለከተ በእስራኤል የቀድሞዉ የአፍሪቃ ስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ዋና ተጠሪን አቶ ዮሃንስ ባዩን አነጋግረንናል።
አፍሪቃ ሃሚልተን ናኪ፦በአፓርታይድ ወቅት ተመራማሪው ባለሙያ ሃሚልተን ናኪ ከአትክልተኛነት እስከ የጤና ቤተ ሙከራ ረዳትነት የበቁ ሰው ናቸው።
የሃሚልተን ናኪ ልደትና ሞት ሃሚልተን ናኪ እጎአ ገደማ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ሴንቴን በተላለችው መንደር በዛሬው የኬፕ ታውን ምስራቃዊ ክፍል ተወለዱ።
የደሀ ቤተሰብ ልጅ በመሆናቸዉ ገና በለጋ ዕድሜያቸው እራሳቸውን ለማስተዳደር ተገድደዋል።
ሃሚልተን ናኪ ባለትዳር የአራት ወንዶች እና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበሩ።
እ ጎ አ ግንቦት ቀን ዓ ም በልብ ድካም ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
ናኪ በ ዓመታቸዉ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ስራ ፍለጋ ወደ ኬፕ ታውን ሄዱ።
ናኪ እ ጎ አ በ በቤተ ሙከራ ውስጥ እንስሳትን ይንከባከቡ ነበር።
የልብ ሐኪም እና ሳይንቲስት ሮበርት ጎትዝ ናኪ ልዩ ችሎታ እንዳላቸው የተገነዘቡትም በዚህ ወቅት ነው።
ኋላም ናኪ የምርምር ሕክምና ትምህርት ቤቱ ውስጥ የቤተ ሙከራ ቴክኒሽያን ሆነው መስራት ጀመሩ።
ከጊዜ በኋላ በቤተ ሙከራ ውስጥ በእንስሳት አካላት ላይ ንቅለ ተከላ እንዴት ማከናወን እንደሚቻል ተማሩ።
በሰዎች ላይ የመጀመሪያውን የልብ ንቅለ ተከላ ካከናወኑት የልብ ሐኪም ፕሮፌሰር ክሪስቲያን በርናርድ ጋር አብረው መስራት የጀመሩትም በዚህ አጋጣሚ ነው።
ናኪ በስራቸው ስኬታማ እየሆኑ የሄዱት ደቡብ አፍሪቃ በአፓርታይድ የዘር መድሎ ሥርዓት በምትገዛበት ወቅት ነው።
ጥቁር ስለነበሩም ነጮች ቀዶ ህክምና የሚያካሄዱበት ክፍል እንዲሰሩ አይፈቀድላቸውም ነበር።
ጥቁር የጤና ባለሙያ ሠራተኞችም ከነጭ ህሙማን ጋር እንዳይገናኙ በሕግ የተከለከለ ነበር።
ስለሆነም የናኪ አስተዋፅዎ ለቀዶ ህክምና የሚያስፈልጉ ቴክኒካዊ ነገሮች ላይ ምርምር በማካሄድ የተወሰነ ነበር።
ሃሚልተን ናኪ በመጀመሪያው የልብ ንቅለ ተከላ ወቅት ያበረከቱት አስተዋጽኦ ምን ነበር
እ ጎ አ ታህሳስ ቀን በልብ ሐኪም ክሪስትያን በርናርድ በተመራው የቀዶ ህክምና ቡድን ውስጥ ሃሚልተን ናኪ አልተሳተፉም።
የነቅሎ ተከላውም የተከናወነው ዴኒዝ ዳርቫል ከተባሉ ሟች ለጋሽ የተወሰደው ልብ ወደ ተቀባዩ ሉዊስ ዋሽካንስኪ በመትከል ነበር።
ይኼ ችሎታቸውም በቤተ ሙከራው የቀዶ ህክምና ረዳት ሆነው እንዲያገለግሉ ማዕረግ አሰጥቷቸዋል።
ይላል በዚህ ሚናቸዉም ናኪ ለበርናርድ ስኬት መንገዱን ካመቻቸው ቡድን አባል ነበሩ።
ሃሚልተን ናኪ በመጀመሪያው የልብ ንቅለ ተከላ የቀዶ ህክምና ወቅት መሳተፋቸውን የተለያዩ ምንጮች ይጠቅሳሉ።
የናኪ ታሪክ ግን የብዙ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያንን ታሪኮች የሚያንፀባርቅ ሲሆን ከአመት አመት ደግሞ ጎልቶ እንዲታይ ሆኗል።
እ ጎ አ በ የተሰወረ ልብ የሚለው ዘጋቢ ፊልም የናኪ ሚና ዝቅተኛ ግምት ተሰጥቶት ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል።
በቅርብ ዓመታትም የናኪ የቤተሰብ አባላት ንቅለ ተከላውን ያደረጉት ናኪ ነበሩ ሲሉ ቁጣቸውን ገልጸዋል።
የናኪ ልጅ ቴምቢንኮሲ ናኪ ነገሩ በጣም ነው የጎዳኝ ክሪስትያን በርናንድ ሁሉንም ሽልማት ሲያገኙ አባቴ ግን ምንም አላገኘም ብለዋል።
ክሪስታና በርናርድ ስለ ሃሚልተን ናኪ አስተዋጽኦ ምን ይሉ ነበር
ክሪስትያን በርናርድ በመጨረሻዎቹ የህይወት ዘመናቸው ለሃሚልተን ናኪ ከፍተኛ ክብር ሲገልፁ ተደምጠዋል።
እ ጎ አ በ ናኪ ከኬፕ ታውን ዩኒቨርስቲ የህክምና ሳይንስ የክብር ዲግሪም አግኝተዋል።