input
stringlengths
1
130k
እ ጎ አ በ ታዋቂው የሃሚልተን ናኪ ክሊኒካል ስኮላርሽፕ ተመስርቷል።
አላማውም የበለጠ ምርምር ለማካሄድ አቅም የሌላቸውን ደቡብ አፍሪካውያን ተማሪዎችን የመደግፍ ነው።
በዕለተ ማክሰኞ የሶርያው አምባገነን በሺር ኧል አሳድ በንጹሃን ሰላማዊ ሰዎች ላይ አደኛ አሰቃቂ የኬሚካል ጥቃት ፈጽመዋል።
ዛሬም ምሽት በሶርያ የኬሚካል ጥቃቱ በተጀመረበት የጦር አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት እንዲፈጸም ትዕዛዝ አስተላልፊያለሁ።
በሜድትራኒያን ባሕር ላይ ከሚንሳፈፉ የዩናይትድ ስቴትስ መርከቦች የተምዘገዘጉት ሚሳይሎች ከሖምስ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘውን የሻራያት የጦር አውሮፕላኖች ማረፊያ ደብድበዋል።
የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ ባወጡት የጋራ መግለጫ የዩናይትድ ስቴትስን ጥቃት ደግፈዋል።
ሁለቱ መሪዎች ለጥቃቱ መፈጸም ኃላፊነቱን የሚወስዱት የየሶርያው ፕሬዝዳንት በሺር ኧል አሳድ ናቸው ሲሉ ኮንነዋል።
የአውሮጳ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ቱስክ የሚሳይል ድብደባው አሰቃቂውን የኬሚካል ጥቃት ለማስቆም አስፈላጊ ነው ሲሉ ተስማምተዋል።
የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት አጋሮች የሆኑት ዩናይትድ ኪንግደም ቱርክ እና ጣልያንም የኃይል እርምጃው አዎንታዊ ነው ባይ ናቸው።
በሌላ ወገን የቆሙት ሩሲያ እና ኢራን የባላንጣቸውን እርምጃ ኮንነዋል።
የኃይል እርምጃው በሽብር ላይ ለተከፈተው ዓለም አቀፍ ዘመቻም እንቅፋት ነው ባይ ነች ሩሲያ።
አገራቸው ከሩሲያ ጋር ያላትን ወዳጅነት ለማረቅ በተደጋጋሚ ቃል የገቡት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁነኛ ፈተና የገጠማቸው ይመስላል።
ሩሲያ ከጥቃቱ በኋላ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በሶርያ የነበራትን ወታደራዊ ሥምምነት ለጊዜው ማቋረጧን አስታውቃለች።
ሥምምነቱ የሩሲያ እና የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይሎች በሶርያ በሚወስዱት የኃይል እርምጃ ድንገተኛ ያልታሰበ ግጭት ውስጥ እንዳይገቡ የታቀደ ነበር።
የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን መንግሥት የሶርያን የአየር መከላከያ እንደሚያጠናክር አስታውቋል።
ዩናይትድ ስቴትስ በሶርያ የወሰደችውን የኃይል እርምጃ ያወገዙት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቦሊቪያ አምባሳደር ሳቻ ሎሬንቲ ዓለም አቀፍ ሕግ ተጥሷል ብለዋል።
እያንዳንዱ ነገር በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ሊስተናገድ ይገባል።
ኃይልን መጠቀም ሕጋዊ የሚሆነው ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አንቀፅ ጋር ሲጣጣም እና ራስን ለመከላከል ሲሆን ብቻ ነው።
ባለፈው ማክሰኞ የአሳድ መንግሥት ሆን ብሎ የኬሚካል ጦር መሳሪያ በመጣል አሰቃቂ በሆነ መንገድ በርካታ ሰዎች ገድሏል።
ከሦስት ዓመት ተኩል በፊት የሶርያ መንግስት የኬሚካል ጦር መሳሪያ መጠቀም የሚያግደውን ውል የመፈረሙ አገሮችን ለመቀላቀል ቃል ገብቶ ነበር።
የኬሚካል ጦር መሳሪያዎቻቸውን ብዛት ለማሳወቅ እና ለማጥፋት ተስማምቶ ነበር።
የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ቋሚ እና ተለዋጭ አባላት በሶርያ የተፈጸሙ የኬሚካል ጥቃቶችን ለመመርመር የሚያስችል የውሳኔ ኃሳብ አርቅቀዋል።
የውሳኔ ኃሳቡ ድምፅን በድምጽ የመሻር ሥልጣን ያላቸው ሩሲያ እና ቻይና ድጋፍ ማግኘቱ ግን አጠራጣሪ ነው።
ለስድስት ዓመታት በዘለቀው የሶርያ የርስ በርስ ጦርነት ዩናይትድ ስቴትስ ቀጥተኛ ተሳትፎ ስታደርግ የአሁኑ የሚሳይል ጥቃት የመጀመሪያው ነው ።
ሚሳይል መተኮስ አስደናቂ እና ከፍተኛ ጉዳት የሚያመጣ ሊመስል ይችላል።
ነገር ግን የተመታው የጦር አውሮፕላን ማረፊያ ያን ያክል ግልጋሎት የሚሰጥ አልነበረም።
ስለዚህ ትረምፕ በዚህ እርምጃ ለሩሲያ ለአጋሮቻቸው እንዲሁም ለሶርያ መንግሥት እንዲህ አይነት እርምጃዎች እንወስዳለን ተጠንቀቁ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
ትራምፕ በዕለተ ቅዳሜ ለአገራቸው ምክር ቤቶች በፃፉት ደብዳቤ አስፈላጊ እና ተገቢ ሲሆን ተጨማሪ እርምጃ እወስዳለሁ ብለዋል።
የሚሳይል ጥቃቱ በሺር ኧል አሳድን የሚደግፉትን ሩሲያ እና ኢራን ሊተነኩስም ይችላል።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጄፍ ዴቪስ አገራቸው ለሩሲያ አስቀድማ ማሳወቋን ተናግረዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ እርምጃ ለበሺር ኧል አሳድ ማስጠንቀቂያ ይሁን ቋሚ የጦር ግንባር እስካሁን በግልፅ የታወቀ ነገር የለም።
የሶርያ ሰብዓዊ መብቶች ታዛቢ ቡድን እና የሕክምና ባለሙያዎች እንደገለጡት ከሟቾቹ መካከል ሕፃናት ይገኙበታል።
የዓለም ጤና ድርጅት የጥቃቱ ሰለባዎች ሳሪን የተሰኘው ገዳይ ኬሚካል መጋለጣቸውን አስታውቋል።
ለስድስት ዓመታት ከዘለቀው የርስ በርስ ጦርነት በኋላም ዓለም ለጥቃቱ የሰጠው ምላሽ ከቀደሙት የተለየ አልነበረም።
ሶርያ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ለመጠቀሟ ምንም ክርክር ሊኖር አይገባም።
በዚህም ምክንያት የስደቱ ቀውስ እየከፋ የቀጣናው ደኅንነትም እየተቃወሰ መሔዱን ቀጥሏል።
ከአራት ዓመታት በፊትም ከደማስቆ አቅራቢያ በተፈጸመ ተመሳሳይ ጥቃት ሶርያውያን ተገደሉ።
የያኔው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ቀይ መስመር አሰመሩ።
ሩሲያ የበሺር ኧል አሳድ መንግስት የኬሚካል ጦር መሳሪያውን እንደሚያስወግድ ቃል ገባች።
የብሪታንያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንም እንደ ትራምፕ ሁሉ ኃላፊነቱን በበሺር ኧል አሳድ ትከሻ ላይ ጥለውታል።
ከተገደሉት ወደ የሚገመቱ ሶርያውያን ለአብዛኞቹ ሞት ኧል አሳድ ተጠያቂ ናቸው ይላሉ የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር።
ቦሪስ ጆንሰን በጎርጎሮሳዊው ዓ ም የተፈረመው የጄኔቫ ሥምምነት የኬሚካል ጦር መሳሪያ መጠቀምን እንደሚከለክል አስታውሰዋል።
የጀርመኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒሥትር ዚግማር ጋብርኤል ይሕ ድርጊት ኧል አሳድን የጦር ወንጀለኛ ያደርጋቸዋል ባይ ናቸው።
ይኸው መርማሪ ሥራውን ለመጀመር ሚሊዮን ዶላር ቢያስፈልገውም በቂ ገንዘብ አላገኘም።
ሩሲያን ጨምሮ ልዕለ ኃያላኑ እዚህም እዚያም የሞከሯቸው ድርድሮችም አልሰመሩም።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ማኅበራዊ ሚድያን ለሰብዓዊ መብት ማራማጃ የሚጠቀምበት የዞን ዘጠኝ ጻሕፍት አባል በፍቃዱ ኃይሉ ጉዳዩን ሲሰማ ማዘኑን ገልፆአል።
በኢትዮጵያ ቴሌኮም በኩል ያለዉ በሙሉ ጭፍን ትያትር ነዉ ብዬ እወስዳለሁም ብሏል።
በፍቃዱ የኢንተርኔት ተደራሽነት በጣም ደካማ በሆነበት አገር በኢትዮጵያ ማኅበራዊ ሚድያ ለመንግስት አደጋ መሆኑን መንግስት መረዳቱን ተናግሯል።
ማኅበራዊ ሚድያ ላይ የሚወጡ ጉዳዩች የአስተዳደራቸዉ ድክምት መሆኑንምን የመንግስት ኃላፊዎች ሊረዱ አልቻሉም እናም መንግስት የህዝቡን ብሶት አልተረዳም ሲል አክሎአል።
ይህን ጉዳይ በተመለከተ በዶይቼ ቬሌ የፌስቡክ ድረገጽ ላይ አስተያየታቸዉን በድምፅ የሰጡንም አሉ።
የአፋር ክልል ነዋሪ የሆኑት መሃመድ አዋል መኅበራዊ ሚድያን በመከልከላቸዉ ታፍነናል እናም ማኅበረሰቡ ተበሳጭተዋል ብለዋል።
የዶይቼ ቬለ ተከታታይ ጉተማ ቴስፋዬ በበኩላቸዉ መንግስት የወሰደዉ ርምጃ በከፊልም ቢሆን ተገቢ ነዉ ይላሉ።
በአዲስ አበባ ሊደረግ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በመንግስት ተራዘመ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
በአማራ ክልል ሚሊዮን ብር የወጣቶች ብድር አልተመለሰም መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የቪዥን ኢትዮፕያ ፎር ዴሞክራሲ ፖለቲካዊ ዓ ጥናት የገዢው ፓርቲ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዴሞክራሲያዊ ህብረተሰብ በመገንባቱ ረገድ ድርሻቸውን ከፍ እንዲያደርጉ ተጠየቁ።
ኢትዮጵያ የታክሲዎች አድማ በአዲስ አበባ አዲስ አበባ በታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ ጭር ብላ ውላለች።
የጭነት ተሽከርካሪዎች እና የመንግስት የሰራተኛ ማመላለሻ አውቶብሶች የታክሲ አገልግሎት ፈላጊዎችን ሲያጓጉዙ የሚያሳዩ ምስሎችም ይገኙበታል።
የአዲስ አበባ የታክሲዎች የሥራ ማቆም አድማ በአካባቢዋ የሚገኙ ከተሞችንም ማዳረሱ እየተነገረ ነው።
ዛሬ በተደረገዉ አድማ የተሳፋሪዎች ጉዞ መስቶጋጎሉን በዶይቼ ቬሌ ፌስቡክ ድረ ገፅ ላይ የተወያዩት ተሳታፊዎች አስታውቀዋል።
አዲሱን የቀላል ባቡር የተጠቀሙም የባቡሩ ተሳፋሪዎች በጣም አስቸጋሪና አጨናናቅ ነበረ ብለዋል።
ብሬግዚት በብሪታንያ ፖለቲካ ላይ ያስከተለው ጣጣ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
አፍሪቃ ውጥረት በቡሩንዲ የምርጫ ዋዜማ በቡሩንዲ በአዲስ መልክ ግጭት ቢቀሰቀስም የምክር ቤት ምርጫ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚካሄድ የቡሩንዲ መንግስት አስታውቋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ በመንግሥት እና በተቃዋሚዎችን በኩል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
የቡሩንዲ መንግሥት ግን ከተቃዋሚዎች ጋር የሚደረገው ንግግር መቋረጡን አስታውቋል።
ንግግሩን ዳግም ለማስጀመር ልዑኩ የሃይማኖት አባቶችን እና የማኅበረሰቡ ተወካዮችን ቢጋብዙም የቡሩንዲ መንግሥት ግን ራሱን ከንግግሩ እንዳገለለ ትናንት አስታውቋል።
በቡሩንዲ የተሰኘው ገዢው ፓርቲ ሊቀ መንበር ፓስካል ንያቤንዳ መንግሥታቸው በንግግሩ የማይሳተፍበትን ምክንያት አስታውቀዋል።
ምክንያቱም እንደሚታየው ከሆነ የዚህ ንግግር ዓላማ ምርጫውን ማወክ ነው።
ቡሩንዲያውያን ጊዜያቸውን ከማባከን በምርጫው ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባቸዋል ሲሉ የመንግሥት ተወካዩ ተናግረዋል።
ከሦስት ሣምንታት በፊት በቡሩንዲ ሊካሄድ ታቀዶ የነበረው የምክር ቤት ምርጫ ከአምስት ቀናት በኋላ የፊታችን ሰኞ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
ከፊታችን ሰኞ ሁለት ሣምንታት በኋላ ደግሞ እጅግ ሲያወዛግብ የከረመው የፕሬዚዳንት ምርጫ እንደሚኪያሄድ ተጠቅሷል።
ፕሬዚዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛ ለሦስተኛ የሥልጣን ዘመን ለመወዳደር ማቀዳቸው የውዝግቡ ሰበብ ሆኖ ከርሟል።
የመንግስት ተቃዋሚዎች የፕሬዚዳንቱ ድርጊት ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ነው በሚል ምርጫው እንዳይከናወን ጥረት ሲያደርጉ መክረማቸው ይታወቃል።
የቡሩንዲ ምርጫ ኮሚሽን ኃላፊ ክላቨር ንዳዪካሪ ግን ለምርጫው የሚያስፈልጉ ነገሮች ተሟልተዋል ምርጫውም በታቀደለት የጊዜ ገደብ ይከናወናል ብለዋል።
ሰኔ የሚካሄደውን የምክር ቤት ምርጫን በተመለከተ ሁሉም ነገር ተጠናቋል።
ቴክኒካዊ ጉዳዮችን ጨምሮ በሀገሪቱ ሁሉም ነገሮች ዝግጁ ናቸው በቡሩንዲ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቀደም ሲል በምርጫው እንደማይሳተፉ መግለጣቸው ይታወሳል።
የምርጫ ኮሚሽኑ በይፋ በምርጫ ላለመሳተፍ ያመለከተ ፓርቲ የለም ሲል ተናግሯል።
ተቃዋሚዎች የምርጫ ኮሚሽኑ እና የፍርድ ስርዓቱ ለገዢው ፓርቲ የቆሙ ናቸው ሲሉ ይወቅሳሉ።
አንድ ወር ከመንፈቅ ባስቆጠረው የቡሩንዲ ቀውስ እስካሁን ሰዎች ተገድለዋል።
የቦንብ ጉዳቱን ያደረሰው በመባባል መንግሥት እና ተቃዋሚዎች ጣት ተቃስረዋል።
የአውሮጳ ኅብረት ለግጭት ሰበብ የሚሆኑ ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ ሊጥል እንደሚችል ሰኞ ዕለት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
ቡሩንዲ የአመት በጀቷን አጋማሽ የምታገኘው ከአውሮጳ ኅብረት መሆኑ ይታወቃል።
ሆኖም እንደ ቤልጂግ እና ኔዘርላንድን የመሳሰሉት ሃገራት ለቡሩንዲ የሚሰጡትን የልማት ርዳታ ቀንሰዋል።
ያም ሆነ ይኽ የቡሩንዲ መንግሥት ምርጫው በታቀደለት መሰረት ሰኞ ከመካሄድ የሚያግደው አንዳችም ነገር የለም ሲል በተደጋጋሚ አስታውቋል።
ዓለም የሩስያ ወታደሮች በክሬሚያ ተኩስ ከፈቱ ሩስያ ክሪሚያን ይፋ የግዛትዋ አካል አድርጋ ከተቀበለች በኋላ ሩስያ በዚያ በይፋ የጦሩ ቁጥጥሯን አጠናከረች።
በየጉባኤ ድርድሩ የአዉሮጳ ሕብረትን አርማ ከፍአድርገዉ የሚያዉለበልቡት መራሒተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ከበርሊን ቦኒስ አይሪስ ለመድረስ ኡራ ወጡበት።
የሙጋቤ ሰባተኛ የሥልጣን ዘመን አንደኛ ዓመት የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ለሰባተኛ የስልጣን ዘመን ዳግም ከተመረጡ ዛሬ አንድ ዓመት ደፈኑ ።
ኢትዮጵያ የሲቪክ ማሕበራት እና የአውሮጳ ኅብረት ድጋፍ የአውሮጳ ኅብረት በኢትዮጵያ ሲቪክ ማሕበራት ተጠናክረው መንቀሳቀስ እንዲችሉ ድጋፉን እንደሚያደርግ አመለከተ።
ይህን በሚመለከትም የሚሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አዲስ አበባ ላይ ተወያይተዋል።
ይህን ችግር ለመቅረፍም ሕብረቱ የ ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ እንደሚያደርግ ለ ገልጸዋል።
ከአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘገባ ልኮልናል።
የኢትዮጵያ መንግስት በወሰነው መሰረት ለአራት ዓመት የዉጭ አገር የስራ ስምሪት ላይ ጥሎ የነበረዉ እገዳ የተነሳው ከትንንት አንስቶ ነው።
እርምጃው ለሕገወጥ ጉዞ መንገድ ከፍቶ ነበር ሲሉ የሚከራከሩ ጥቂት አልነበሩም።
ሕጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸዉ በሳዑድ አረብያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የውጭ ዜጎች በቅርቡ አገሩን ለቀው እንዲወጡ መደረጉ ይታወሳል።
ወደ አገራቸዉ የተመለሱትን መንግስት እንዴት እየተቀበላቸው እንደሆነ አቶ ባሳዝን ደርቤ ይናገራሉ።
ኢትዮጵያ በጎንደር የጥምቀት በዓል አከባበርና የደረሰዉ አደጋ የጥምቀት በዓል ከፍተኛ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት በተገኙበት በጎንደር ከተማ በድምቀት ተከብሯል።
አራማጆቹ በሚቀጥለው ሳምንት ለከባቢ አየር ለውጥ መፍትሔ የሚያበጁ ፖሊሲዎች እንዲዘጋጁ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሔድ አቅደዋል።
የከባቢ አየር ለውጥ ትኩረት እንዲያገኝ የሚወተውቱ አራማጆች በበርሊን ከተማ ከመራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ፅህፈት ቤት ደጃፍ መጠለያ መገንባት ጀመሩ።
የጀርመን መንግሥት በቅርቡ ያዘጋጀው ምክረ ሐሳብም ሆነ ከዚህ ቀደም ሥራ ላይ የነበረው ፖሊሲ በቂ አይደለም ሲሉ ቦትዝኪ ተችተዋል።
ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ የበርሊን ከተማ ዋና ዋና መንገዶችን ይዘጋል ተብሎ ይጠበቃል።
መንግሥት እንደ ፊልምና ትያቴር ቤት ሁሉ የስዕል ጋለሪ ይከፈትልን ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።