input
stringlengths
1
130k
አደጋዉ እዚሕ እላይ ያለዉ ነገር ምን ያሕል አደገኛ እንደሆነ አረጋገጠ።
በአስር ሺሕ የምንቆጠር ሰዎች ለተቃዉሞ አደባባይ መዉጣት የጀመርነዉም ከዚያ ጊዜ በኋላ ነዉ።
እሳቸዉም ባለቤታቸዉም የኑክሌር ጦር መሳሪያን የሚቃወመዉ የሐይልብሮን የሠላም ምክር ቤት የተባለዉ ስብስብ አባላት ናቸዉ።
ተቃዉሞዉ ግን ቦን ላይ ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ ካሰለፈ በኋላ በድፍን አዉሮጳ ከዚያም በዓለም ተዛምቶ ዓለም አቀፍ ንቅናቄ ሆኗል።
ሕዝባዊዉ ግፊት ሶቭየት ሕብረት ከተደረገዉ የመሪዎች ለዉጥ ጋር ተዳምሮ ፕሬዝደንት ሮናልድ ሬገንና ዋና ፀሐፊ ሚኻኤል ጎርቫቾቭ የተባለዉን ስምምነት እንዲፈራረሙ አስገድዷል።
ይሕ ሥርዓትና የምንፈርመዉ ሥምምነት ለትዕግሥት ዉጤት እጅግ በጣም ጥሩ ምሳሌዎች ናቸዉ።
ከስድት ዓመታት በፊት ሕዳር ነበር ዜሮ አማራጭ የሚለዉን ሐሳብ ያቀረብኩት።
ከዚሕ ቀደም እንደነበሩት ስምምነቶች የነበረዉን መቀነስ ወይም አዲስ የጦር መሳሪያዎችን ክምችት የሚገታ ብቻ አይደለም።
በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር የሚለዉ ቋንቋ የጦር መሳሪያ ቅነሳ በሚለዉ ተለዉጧል።
በዚሕ ዉል መሠረት የሶቬየትና የዩኤስ የኑክሌር ሚሳዬልን ማጥፋት ነዉ።
በርግጥም በስምምነቱ መሠረት ዩናይትድ ስቴትስ ሶቭየት ሕብረት ደግሞ ሺሕ የአጭርና የመካከለኛ ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳዬሎቻቸዉን አጥፍተዋል።
እስከ መጀመሪያ ድረስም አዉሮጳ ሰወስተኛዉ የዓለም ወይም ምናልባትም የመጀመሪያዉ የኑክሌር ጦር ዉጊያ ይጫርባታል የሚለዉ ሥጋት ቀንሶ ነበር።
የሩሲያ ፌደሬሽን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ማርሻል ዩሪ ባሉየቭስኪይ የዋይት ሐዉስ ማማኸኛን ሩሲያን እንደማጃጃል ነበር የቆጠሩት።
የፕሬዝደንት ጆር ቡሽ ዉሳኔ እንደተሰማ ለአፀፋ የዛቱት የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በ የተሰኘዉን ሚሳዬል አሰሩ።
የጀርመኑ የፀጥታ ጉዳይ ተኝታኝ ማርኩስ ካይም እንደሚሉት ፕሬዝደንት ባራክ ኦቦማ የሩሲያን እርምጃ ደበቅ አድርገዉ ጉዳዩን በድርድር ለመጨረስ ሞክረዉ ነበር።
የኑክሌር ስምምነቱን ጥሰዉ እኛ መስራት የተከለከልነዉን መሳሪያ እንዲሰሩ አንፈቅድላቸዉም።
ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፒዮ መንግስታቸዉ ከቅዳሜ ጀምሮ ከስምምነቱ መዉጣቱን አወጁ።
ዉጪ ጉዳይ ሚንስትራቸዉ ሠርጌይ ላቭሮቭ ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስን ዉሳኔ ሥጋት ብለዉታል።
የቀዝቃዛዉ ጦርነት መለያ እንደነበረዉ የጦር መሳሪያ ምርት እሽቅድምድም ዉስጥ አንገባም።
እርግጥ ነዉ ዩናይትድ ስቴትስ ከአጭርና ረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ የኑክሌር ሚሳዬል ሥምምነት በመዉጣታዋ የፈጠረችዉን ሥጋት ለመቋቋም ወታደራዊና ቴክኒካዊ አቅምን መጠቀማችን አይቀርም።
የፖለቲካ ተንታኞችም መጪዉ ጊዜ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ስጋት የሚንርበት ይሆናል ባዮች ናቸዉ።
ቅዳሜ የፈረሰዉ ስምምነት ታዛቢዎች እንደሚሉት የዓለምን ሠላም ለማስከበር ከመጥቀሙ እኩል ለቻይና ልዩ እድል ነበር የፈጠረላት።
ሁለቱ ኃያላን መንግሥታት ስምምነቱን ሲፈራረሙ እንደስጋት ያላይዋት ቻይና ዛሬ የዘመናዊዉ የኑክሌር ሚሳዬል አምራች ሆናለች።
የጦር መሳሪያ አዋቂዎች እንደሚሉት ቻይና በስምምነቱ ከታገደዉ ከ ኪሎ ሜርትር ርቀት በላይ የሚወነጨፍ ሚሳዬል አምርታለች።
አሁን የስምምነቱ መፍረስ ዩናይትድ ስቴትስ የቻይናን አዳዲስ ሚሳዬሎች የሚገታ ሚሳዬል ለማምረትና እስያ ላይ ለመትከል ይረዳታል ባዮች አልጠፉም።
ኢትዮጵያ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ሲያስተምራቸው የነበሩ ሺህ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡
በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ያወጀዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተመለከተም ተሳታፊዎች ንግግር አሰምተዋል።
የፓርላማ አባላት የኮሚሽኑ እና የልዩ ልዩ ድርጅቶች ተወካዮች በተካፈሉበት በዚሁ ውይይት ላይ በብራሰልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካዮችም ተገኝተዋል ።
በውይይቱ ላይ የፓርላማ አባላት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግር አለበት ባሉት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ኮሚሽኑ ለዘብተኛ አቋም ይከተላል ሲሉ ወቅሰዋል ።
ኢንተርኔትን እና ሚዲያን የሚገድበው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳም ጠይቀዋል።
የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጥሪ በማስተላለፍ እስሩ አሁንም እንደቀጠለ ነው ያሉት ወ ሮ አና ጎሜሽ የአውሮጳ ኅብረት ጠንካራ ርምጃ ባለመውሰዱ ወቅሰዋል።
የጀርመን መራኂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የኢትዮጵያ ጉብኝትንም አጥብቀው ተችተዋል።
አምባሳደሩ በስብሰባው ላይ በኦሮምያ የዘረኝነት ችግር አለ መባሉን እንዳስተባበሉ ውይይቱን የተከታተለው የብራሰልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ ዘግቧል ።
ስፖርት ግንቦት ዓም መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
መቀመጫውን በሲሊከን ቫሊ ያደረገው ህሩይ አማኑኤል ከኮደርስ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር የመጀመሪያውን ገበያ የተሰኘ የሶፍትዌር ፕሮግራሚንግ ማሰልጠኛ በኢትዮጵያ ከፍቷል።
የተቃዋሚዎች ተወካዮች ድርድሩን ረግጠው ቢወጡም መንግስት ግን አሁንም ይቀጥላል እያለ ነው።
በአምነስቲ ዘገባ መሰረት የሶስት አካባቢያዊ አስተዳደሮች ባለስልጣናት በተቃውሞ ሰልፎች ላይ ገደብ ጥለዋል የተቃውሞ ሰልፎች ህጋዊ እውቅና ተነፍገዋል።
ይሁንና የገዢው ጥምር ፓርቲ ደጋፊዎች በፖሊስ እና አካባቢያዊ አስተዳደሮች አመቻችተውላቸው የአደባባይ ሰልፎችን አካሂደዋል።
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ ከ ዓመታት የስልጣን ዘመን በኋላ በጎርጎሮሳዊው ዓ ም መገባደጃ ይለቃሉ ይለቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ፕሬዝዳንቱ እስካሁን የሥልጣን ዘመናቸው ሲጠናቀቅ መንበራቸውን ስለማስረከባቸው አሊያም ለተጨማሪ ዓመታት በስልጣን ለመቆየት በድጋሚ ለመወዳደራቸው በግልፅ ያሳወቁት ነገር የለም።
አገሪቱ በመጪው ህዳር ከምታካሒደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት የጀመረችው የብሔራዊ እርቅ ጉባኤ እንደታቀደው አልሰመረም።
ባለፈው ሳምንት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ድርድሩን ረግጠው ወጥተዋል።
የተቃዋሚዎቹ ውሳኔ ድርድሩ ላለመሳካቱ ምልክት ሳይሆን አይቀርም እየተባለ ነው።
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግስት ቃል አቀባይ ራማዛኒ ሻዳሪ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ረግጠው በመውጣት እንደ መደራደሪያ ሊጠቀሙበት ከጅለዋል ሲሉ ይወነጅላሉ።
ይህ ድርድሩ አብቅቶለታል ወይም ተቃዋሚዎች ራሳቸውን አግልለዋል ማለት አይደለም።
ምናልባት በሌሎች ቦታዎች አገሮች እንደሆነው ወደ ድርድር ጠረጴዛው መመለስ አለብን ብለው ሊያምኑ ይችላሉ።
ተቃዋሚዎች ሁለቱ ምርጫዎች በተከታታይ መካሔድ አለባቸው የሚል ቁርጥ አቋም ይዘዋል።
ተቃዋሚዎች ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው በሕገ መንግስቱ መሰረት የጆሴፍ ካቢላ የስልጣን ዘመን ከማብቃቱ ዘጠና ቀናት በፊት ሊካሔድ ይገባል ብለው ይከራከራሉ።
በእነሱ እምነት መሰረት አካባቢያዊ ምርጫዎች ፕሬዝዳንታዊውን ተከትለው ሊካሔዱ ይገባል።
ሞይሴ ካቱምቢ ቪታል ካሜርሔ እና ኤትየን ሺሴኬዲ የጋራ ጥምረት የመሰረቱት በቅርቡ ነበር።
መንግስት ድርድሩን በስልጣን ለመቆየት እንደ መሳሪያ እየተጠቀመበት ነው ሲሉም ይወነጅላሉ።
በርካታ ተከታዮች ያሏቸው ሌላው የተቃውሞ ፖለቲካ መሪ የ ዓመቱ ኤትየን ሺሴኬዲ አንድነት ለዴሞክራሲ እና ማሕበራዊ ለውጥ ፓርቲ መሪ ናቸው።
ይሁንና በድርድሩ የተቃዋሚዎች ሁነኛው ተወካይ ለኮንጎ አንድነት የተባለው ፓርቲ ተወካይ ቪታል ካሜርሔ ናቸው።
ካሜርሔ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለድርድሩ መጓተት ገዢውን ጥምር ፓርቲ ተጠያቂ አድርገዋል።
ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ የፕሬዝዳንታዊ ሃያላን ጥምረት ጓደኞቻችን የሚቀጥለውን እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ሊረዱ ይገባል።
ማዘግየትን እንደ ሥልት ገዢው የፕሬዝዳንታዊ ሃያላን ጥምረት ፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ከአካባቢያዊው በኋላ ለማካሔድ ቆርጠው ተነስተዋል።
ተቃዋሚዎች ይህ በ ታኅሣሥ ወር የሚጠናቀቀውን የፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ ሥልጣን ለማራዘም የሚጠቀሙበት ሥልት ነው ሲሉ ይከራከራሉ።
እስካሁን ካለየለት የምርጫ ሰሌዳ በተጨማሪ የመዘገባቸውን ድምፅ ሰጪዎች ዝርዝር ማሻሻል የሚጠበቅበት የምርጫ ኮሚሽን ከፊቱ ፈተና ተደቅኖበታል።
እንደ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባለ ሰፊ እና ምቹ መንገዶች በሌሉበት አገር የመራጮች ምዝገባን ለማሻሻል ቀላል አይደለም።
እስካሁን የመራጮች ምዝገባ የተጀመረው በሰሜናዊ የኡባንጊ ግዛት ብቻ ነው።
አሁን እኛ የምርጫ ኮሚሽኑን የቆጠራ ውጤት በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን።
ሲሉ የምርጫ ተቆጣጣሪ የሆኑት አንድሬ ካዮምቤ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
ሁሉንም ግዛቶች ለማዳረስ ግን እስከ አስራ ስድስት ወራት ይፈጃል።
ይህ ማለት ደግሞ ፕሬዝዳንት ካቢላ በህገ መንግስቱ እና የምርጫ ውጤት ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ በስልጣን ይቆያሉ ማለት ነው።
ፍርድ ቤቱ ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው የስልጣን ቅብብሎሹን ለማስጠበቅ እና በከፍተኛው አመራር ዘንድ የሚፈጠር ክፍተትን ለማስወገድ መሆኑን ገልጧል።
የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በ ዓመታቸው ባለፈው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የመለያ ምርጫ በአፍጋኒስታን አፍጋኒስታን በሚያዝያ ወር ባካሄደችዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የብዙሃኑን አብላጫ ድምፅ ያገኘ ተፎካካሪ ባለመኖሩ የመለያ ምርጫ ለማካሄድ ወሰነች።
የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካና ሠራተኞቹ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የመሬት መንቀጥቀጥ በኢትዮጵያ ሁሉም ረጭ ባለበት ድንገት በእኩለ ሌሊት ነው የተከሰተው።
ብርጭቆዎች ከየመደርደሪያቸው እየተውረገረጉ ረግፈዋል ትሪዎች ከየተሰቀሉበት ግድግዳ እየሸሹ ከመሬቱ ጋር ኹካታ ገጥመዋል።
ከአልጋቸው ተንከባለው የወደቁም ነበሩ ከዚያ ባለፈ ግን ምን ያኽል ጉዳት እንደደረሰ በውል አይታወቅም የመሬት መንቀጥቀጥ በኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ ከተሞች።
ርእደ መሬቱ ከኤርታአሌ ቅልጥ አለት ሐይቅ ሙላት አቅራቢያ እስከ ላንጋኖ ከዝዋይ እስከ አዋሳ ታይቷል በሌሎች ከተሞችም ንዝረቱ ተሰምቷል።
ከሰሜን እስከ ደቡብ የተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙበት ታላቁ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ውስጡን ሁሌም እንደተናጠ ነው።
በኢትዮጵያ በቅርቡ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ብቻ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጦች ተከስተዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት በወቅቱ እስከ አዲስ አበባ ድረስ ሊሰማም ችሎ ነበር።
ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ደግሞ ከመሬት መንቀጥቀጡ ባሻገር ሌላም አስገራሚ ክስተት ተፈጥሯል።
ወትሮ በተንጣለለበት የእሳት ሐይቅ ላይ የሚንተከተከው የኤርታአሌ ቅልጥ አለት ከረቡዕ ጥር ቀን ዓም ጀምሮ ሞልቶ መፍሰስ ይዟል።
የኤርታአሌ ቅልጥ አለት ሐይቅ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው መባሉን መስማታቸውን ተናግረዋል።
የኤርታአሌ የማግማ ሐይቅ የቅልጥ አለቱ ሐይቅ ሞልቶ ፈሷል መባሉን ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ሀገር ጎብኚዎች ለመስማት ችለናል።
እኛ ግን በእኛ ጣቢያዎች መረብ የመዘገብነው በጣም ትንሽ የቅልጥ አለት እንቅስቃሴ የሚያመላክት መረጃ ነበር።
እና ይህ ማለት ቅልጥ አለቱ ወደ ላይ ወጥቶ ምንም እንደ መሬት መንቀጥቀጥ ብዙ እንቅስቃሴ ሳይፈጥር መፍሰስ ችሏል።
በአፋር የኤርታሌ ሐይቅ ውስጥ ሲንፈቀፈቅ ዘመን የፈጀው ቅልጥ አለት ከወትሮው በተለየ መልኩ ከመፍሰሱም ባሻገር በአቅራቢያው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
ጃንዋሪ ደግሞ ጥር ቀን በእኛ ልኬት መጠኑ ወደ የሚደርስ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቧል ።
ግን ብዙ ዓለም አቀፍ ማዕከላትን ስናመላክት መጠኑ ከዚያም በላይ ወደ እና ይደርሳል ተብሎ የሚገመት የመሬት መንቀጥቀጥ ኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ።
ብዙ ሰው ጉዳት ሊደርስበት በሚችል መልኩ ነው የተከሰተው ሁሉም ሰው በየቤቱ ሊገባ ስለሚችል ማለት ነው።
እናም በጣም ብዛት ባላቸው የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ባሉ ከተሞች ተሰምቷል አዲስ አበባን ጨምሮ ማለት ነው።
የአውሮጳ እና ሜድትራኒያን የርዕደ መሬት ጥናት ማዕከል በበኩሉ በሬክተር ስኬል መለኪያ እንደተመዘገበ ገልጧል።
ተቋሙ ጠንካራ ያለው ርእደ መሬት የተከሰተው ከአዋሳ ሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ ኪሎ ሜትር ርቀት ከምሽቱ ሰአት ከ ደቂቃ ላይ እንደነበር ጠቅሷል።
ገና ሲታቀድ ጀምሮ ነው መጀመሪያ መፍትኄ ለመፈለግ ጥረት የሚደረገው።
ችግር ሲፈጠር ሰዎች የሚሰባሰቡበት ገላጣ ቦታ በቅርብ ርቀት መገኘት መቻል አለበት።
እንግዲህ ህንጻዎቹ ጋር ከመድረሳችን በፊት ገና በዕቅድ ደረጃ ማለት ነው መሬት አጠቃቀም ላይ ችግር ሲመጣ መቋቋም እንዲቻል።
ለምሳሌ እሳት ሲኖር ወጥተህ ሌላ ቦታ ላይ ገላጣ ቦታ ላይ እንደምትሄደው ርእደ መሬትም የዚያን አይነት በየአካባቢው ያስፈልጋል።
ሽመልስ ወልደ ሠርባ የተባሉ በዶይቸ ቬለ የአማርኛ ቋንቋ ክፍል የፌስቡክ ተከታታይችን ነዋሪነታቸው የተፋፈጉ ቤቶች በሚበዙባት በመዲናዪቱ አዲስ አበባ አይደለም።
ርእደ መሬቱ ሲከሰት አዋሳ በሚገኝ እቤት ውስጥ ግድግዳ ተደግፈው ነበር።
እንዲህ ነበር ያሉን፦ ምሽት ወደ ፡ ሀዋሳ ላይ የተከሰተ ሲሆን ግድግዳ ተደግፌ ስለነበር፥
ግርግዳውን ሌላ ሰው ከውስጥ እየገፋው መስሎኝ ነበር ክስተቱን አጠገቤ የነበሩትም ሰዎች አስተውለውታል፡፡
ሌሎች አስተያየት ሰጪዎችም የመሬት መንቀጥቀጡን በስምጥ ሸለቆ ከተሞች ውስጥ መታዘባቸውን ተናግረዋል።
በኮንስትራክሽን ሚንስትር የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ዋና ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ሥዩም መሥሪያ ቤታቸው ለመሬት መንቀጥቀጥ ብሎ በተለይ እንደማይንቀሳቀስ ገልጠዋል።
ሆኖም ግን ርእደ መሬት በአጠቃላይ የግንባታዎች ደኅንነት ጉዳይ ጋር እንደሚካተት አክለዋል።
የመሬት መንቀጥቀጥን በተለየ መልኩ እንደ አንድ ጉዳይ አንስተን የተንቀሳቀስንበት የለም በተለይ በእኛ በዳይሬክተር ደረጃ።