input
stringlengths
1
130k
የሶሻል ዴሞክራቶቹ ውሳኔ ላለፉት አምስት ወራት በሞግዚት ስትተዳደር ለቆየችው ጀርመን አዲስ መንግስት ያስገኝላታል፡፡
ከ ሺህ በላይ የፓርቲው አባላት ስምምነቱን መቀበል ወይንም አለመቀበላቸውን የወሰኑበት ድምጻቸውን በደብዳቤ እንዲልኩ ተጠይቀው ነበር፡፡
የጥምር መንግስቱ ደጋፊዎች ቁጥር አስቀድሞ ከተገመተው በላይ ከፍ ያለ ነው ተብሏል፡፡
በመቶው ለጥምር መንግሥት ምስረታው የይኹንታ ድምፃቸውን ሲሰጡ ከመቶው አልተስማሙም የፓርቲው ተጠባባቂ ሊቀመንበር ኦላፍ ሾልዝ ውሳኔው ለ ቀላል አልነበረም ብለዋል፡፡
የጥምር መንግሥት ምስረታው ስምምነት ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የጀርመን ምክር ቤት ቡንደስታግም ሜርክልን በድጋሚ መራኂተ መንግሥት አድርጎ ይመርጣል ተብሏል፡፡
አዲስ የሚመሰረተው ጥምር መንግሥት ሜርክል በመሪነት በቆዩባቸው ዓመታት ውስጥ ሦስተኛው ይሆናል፡፡
የሶሻል ዲሞክራቶቹ አባላት ውሳኔን በተመለከተ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ጋር የተደረገው ሙሉ ቃለ መጠይቅ ከታች የድምፅ ማዕቀፉ ውስጥ ይገኛል።
ዉድድር ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትነት ቦታ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለፕሬዝዳንትነት የሚቀርቡትን እጩዎች እየመረጠ ነው።
የተመድ በርዋንዳ አሰማርቶት የነበረውን ጦሩን በዚያን ጊዜ ማስወጣቱ የሚታወስ ነው።
በአፍሪቃ ለተካሄደው ትልቁ የጎሣ ጭፍጨፋ ግን የፕሬዚደንት ሀቢያሪማን ሞት ብቸኛው ምክንያት አይደለም።
በሁለቱ ጎሣዎች መካከል ውጥረቱ ከቅኝ አገዛዙ ዘመን ጀምሮ ያለ ነው።
በመዲናይቱ ኪጋሊ በሚገኝ አንድ ኮረብታማ ቦታ የጊሶዚ መታሰቢያ ማዕከል ይታያል።
ማዕከሉ እአአ በ ዓም ከተከፈተ ወዲህ ማንኛውም ርዋንዳን የሚጎበኝ ሰው ቱሪስት ሆነ ርዕሰ ብሔር ይህንኑ መታሰቢያ ማዕከል ሳይጎበኝ አይሄድም።
በማዕከሉ የሚታዩት ፎቶዎች ልብሶች እና የግል ቁሳቁሶች የጎሣው ጭፍጨፋ ከሚያዝያ እስከ ሰኔ በተፈፀመው አስከፊ የግድያ ተግባር ሕይወታቸውን ያጡትን ሰለባዎችን ያስታውሳል።
የጊሶዚ ማዕከል የሕፃናት ክፍል በሚባለው ክፍል ውስጥ ትላልቅ ፎቶዎች ተሰቅለዋል።
ከነዚሁ ፎቶዎች መካከል አንዱ ፈግግታ የሚታይባት የቆንጆዋ ፍራንሲን ፎቶ ነው።
እንቁላል እና የድንች ጥብስ መብላት ወተት እና ፋንታ መጠጣትም ትወድ ነበር።
ርዋንዳ ውስጥ የጎሣው ጭፍጨፋ በተካሄደባቸው ሦስት ወራት በጣም ብዙ አስከሬን በየመንገዱ ተትረፍርፎ ይታይ ነበር።
ዳታኞ ሀቢንትዋሊ አንዳንዴ ቁጥሩ የጎሣ ጭፍጨፋ በትክክል ምን መሆኑን መረዳትን አዳጋች ያደርግብናል።
ይህን ለመረዳት አንድ ሰው ከጎሣው ጭፍጨፋ ከተረፈ ሰው ጋ ብዙ ጊዜ ማሳለፍ ይኖርበታል።
ውን ቀን በፍርሀት ተውጦ እና በረሀብ ተሰቃይቶ እንዴት እንዳሳለፈው ደቂቃ በደቂቃ እንዲያስረዳ ጊዜ መስጠት ያስፈልጋል።
መኖሪያ ቡቱ በእሳት ጋይቶ እና ተዘርፎ ቤተሰቡም በጠቅላላ ተገድሎ ማግኘት ማለት ምን እንደሆን እንዲያብራራ ጊዜ መስጠት ይገባል።
የጎሣ ጭፍጨፋ ማለት ይህ ወደ አንድ ሚልዮን የሚጠጋ ሰው የገጠመው ነው።
የጅምላው ጭፍጨፋ በደቡባዊ ርዋንዳ በምትገኘው የትውልድ ከተማው ቡታሬ ሲካሄድ የአምስት ዓመት ሕፃን ነበር።
የአሩሻ ፍርድ ቤት የርዋንዳ ሕዝብ ባለፉት ዓመታት ዕርቀ ሰላም ለማውረድ ረጅም መንገድ ተጉዞዋል።
ፕሬዚደንት ካጋሜ የሚመሩት የርዋንዳ መንግሥት በመጀመሪያ የወሰደው ርምጃ በሕዝቡ መታወቂያ ሰነድ ላይ የግለሰቡን ጎሣ የሚጠይቀውን ጥያቄ መሰረዝ ነው።
ሕዝቡ በጋራ ለህብረተሰቡ የሚጠቅም አገልግሎት የሚያበረክትበትን በሀ ገሩ ቋንቋ ኡሙጋንዳ የሚለውን አሰራርም እንደገና አስተዋውቋል።
ጋቻቻ ባህላዊ ፍርድ ቤት የጅምላው ጭፍጨፋ በተዘጋጀበት ድርጊት የተሳተፉት ብዙዎቹ የመንግሥት ሚንስትሮች ታስረው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
የጅምላው ጭፍጨፋ እንዲካሄድ ጠንክረው የተሳተፉ በርካታ የጦር መኮንኖች እና ወታደሮች ሚሊሺያዎች የሀይማኖት አባቶች እና የመገናኛ ብዙኃን ተወካዮችም ጭምር በሕግ ተጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱ የመጨረሻውን የክስ ጉዳይ እአአ በ ዓም የዘጋ ሲሆን እአአ እስከ አጋማሽ ድረስ የይግባኝ ማመልከቻዎችን ብቻ ይመለከታል።
በፍርድ ቤቱ ክስ ከተመሠረተባቸው የርዋንዳ ዜጎች መካከል በ ላይ ብቻ ረጅም የእስራት ቅጣት በመበየኑ ከኪጋሊ ብርቱ ወቀሳ ተፈራርቆበታል።
የደ ሱዳን ተቀናቃኞች የፊት ለፊት ንግግር የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ለዛሬ እንደተቀጠረዉ ለፊት ለፊቱ ዉይይት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በሳምንቱ አጋማሽ ይፋ ያደረገው የታሪፍ ማሻሻያ በማህበራዊ መገናኛዎች ተጠቃሚዎች ዘንድ በጎ ምላሽ አስገኝቶለታል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እና ነባር ታጋዮች የሚያደርጓቸው ስብሰባዎች በተለየ አትኩሮት መታየት ይዘዋል።
የመጀመሪያዉ የአማርኛ ሰዋሰዉ በ ኛዉ ክፍለ ዘመን በጀርመናዉያን ታትሟል አውዲዮውን ያዳምጡ።
አዲሱ የ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አውዲዮውን ያዳምጡ።
ጋዜጠኞቹ በሽብርተጠረጠሩ እንጂ ፖሊስ ለምን እንደጠረጠራቸዉ መግለጽ አልቻለም አውዲዮውን ያዳምጡ።
በየክፍለ ከተማዉ በየወረዳዉና እና ቀበሌዉ ያሉ ወጣቱን እያደናቀፉ ያሉ ሰዎች ለመሰደድ ዋና ምክንያት ናቸዉ።
ልዑካኑ የሚሄዱት ለሰላም ጥረቱ አዎንታዊ አስተዋፅኦ ለማድረግ መሆኑም ተገልጿል።
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ይህን የተናገሩት ዛሬ በኤርትራ እየተከበረ በሚገኘዉ በ ኛዉ የሰማዕታት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ ባደረጉት ንግግር ነዉ።
አክለውም ከኢትዮጵያ በኩል ባለፉት ቀናት የተሰሙት አዎንታዊ ምልክቶች የኅብረተሰቡ ግልፅ ምርጫ መሆኑን እንደሚያመላክትም ገልጸዋል።
በኬንያ የኤርትራ አምባሳደር በየነ ርዕሶም በበኩላቸው በሁለቱ ሃገራት መካከል አዲስ የሰላም እና የእርቅ ምዕራፍ መከፈቱን መግለፃቸውን አሶሲየትድ ፕረስ ዘግቧል።
በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በነበረዉ ዉዝግብም የሁለቱ ሃገራት ሕዝብ ሁለት ትዉልዶች የግማሽ ምዕተ ዓመት ዕድልን አጥተዋልም ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለኤርትራ ልዑካንም መልካም አቀባበል ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ማስታወቃቸውንም አቶ ፍፁም ጠቅሰዋል።
ቡድኑን ለመዋጋት የተመሠረተው ከአካባቢው ሃገራት የተውጣጣው ወታደራዊ ግብረ ኃይል ለችግሩ መፍትሄ ይሆናል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል።
የናይጀሪያው ፕሬዝዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ሥልጣን ከያዙ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረጉት የካሜሩን ጉብኝት ብዙዎች ሲጠብቁት የነበረ ነው።
የዚህም ምክንያቱም ሁለቱ ሃገራት የጋራ ችግር ውስጥ መውደቃቸው ነው።
በአሁኑ ጊዜ የናይጀሪያው ደፈጣ ተዋጊ ቡድን የፅንፈኛው ቦኮሃራም ወታደራዊ እንቅስቃሴ መዳከሙ ቢታመንም አልሞት ባይ ተጋዳይነቱ ግን አይሏል።
ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ቡድኑ በጣላቸው የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃቶች ወደ የሚጠጉ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል ።
ቡሃሪ ያውንዴ ውስጥ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት የሁለቱ ሃገራት የጋራ ጠላት በሆነው በቦኮሃራም ላይ መንግሥታቸው የያዘውአቋም ከቀድሞው የተለየ አይደለም ።
ናይጀሪያ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችንን ህይወት ያጠፋውን ያቆሰለውን ብዙዎችንም መኖሪያ አልባና ያደረገውንና ህይወታቸውንም ያሰናከለውን ቦኮሃራምን ለመውጋት አሁንም በቁርጠኝነቷ እንደፀናች ነው ።
ቦኮሃራም በናይጀሪያና በአካባቢው ሃገራት የሚጥላቸው የሽብር ጥቃቶች በሃገራቱ ኤኮኖሚ ላይ ተፅእኖ ማሳደሩ ነው የሚነገረው ።
ይህም እንደ ኦዱስ በሃገሬው ህዝብም ሆነ በውጭ ዜጎች ላይ ተፅእኖ ማሳደሩ አልቀረም ።
በዚህና በሌሎችም የሽብር ጥቃቱ ባስከተላቸው ተፅእኖዎች ሰበብ ከቅርብ ወራት ወዲህ የአካባቢው ሃገራት ወታደራዊ ትብብራቸውን አጠናክረዋል ።
በጎርጎሮሳዊው በ መጀመሪያ ላይ የቻድ ወታደሮች ቦኮሃራምን ከሰሜን ምሥራቅ ናይጀሪያ በማስወጣት ትልቅ ሚና ተጫውተዋል ።
በአሁኑ ጊዜ የደፈጣ ተዋጊው የቦኮሃራም የመጨረሻው ዋነኛ ምሽግ ካሜሩን ድንበር ላይ የሚገኘው የዛምቢዛ ጫካ ሆኗል ።
ቦኮ ሃራም ያልታጠቀ ማህበረሰብ ላይ ነው የበቀል እርምጃ የሚወስደው ።
ይህ ደግሞ አሁን በሽሽት ላይ መሆኑንና ከዚህ ቀደም ናይጀሪያ ውስጥ የያዛቸውን አካባቢዎች መልሶ የመቆጣጠር አቅም እንደሌለው ያመለክታል ።
በርግጥ ይህን መሰሉን እርምጃ ማቆም እስከሚቻል ድረስ ጊዜ ይወስዳል ።
ምክንያቱም ታጣቂ በሌለበት መንደር አንድ የታጠቀ ሰው ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላልና።
ናይጀሪያ ካሜሩን ቻድና ኒዠር ቦኮሃራምን በጋራ ለመዋጋት ሠራዊት ያለው አዲስ ግብረ ኃይል ለማሠማራት አቅደዋል ።
በኢብራሂም እምነት የጋራው ስጋት በናይጀሪያ ይመራል የተባለው ግብረ ኃይል የታሰበለትን ዓላማ እንዲያሳካ ይረዳል።
በቅርብ ዓመታት ውስጥ ቦኮሃራም ያተኮረው በናይጀሪያ ላይ ነበር ።
ሶስቱ የናይጀሪያ ጎረቤቶች ኒዠር ቻድና ካሜሩን እስካሁን ድንበሮቻቸውን ከቦኮሃራም ጥቃት ሲከላከሉ ነበር የቆዩት።
አሁን ደግሞ ቦኮሃራምን ለመዋጋት በሚካሄደው እውነተኛው ውጊያ ውስጥ ሊገቡበት ነው ።
ሆኖም ሃገራቱ ያለፈውን ግጭት ለታሪክ በመተው አሁን የጋራ ጠላቸውን ቦኮሃራምን ለመዋጋት ተባብረው ለመሥራት ተስማምተዋል ።
ኢትዮጵያ የንቅሳት ጌጥ በአፍሪቃዉ ቀንድ የጥርሷ ንቅሳት ያንገቷ ሙስና ረቡዕ ያስገድፋል እንኳን ሐሙስና።
ንቅሳቷ ነዉ ዉበቷ በተራራ ፍየል ይመስላል ሰርገኛ የእገትዋ ንቅሳት አለዉ አማረኛ ንቅሳትሽማ ልብ ያስደነግጣል ከጀግናዉ ባለቤት ከተዋበች በልጦአል
አሁን አሁን ንቅሳት ባህል በገጠሩ አካባቢ ካልሆነ እንደቀድሞ ጊዜ የሚነቀስ አለ ማለት ይከብዳል።
በገጠሩ አካባቢ አዳጊ የስምንት ዓመት ሕጻናት ሁሉ ተነቅሰዉ ይታያሉ።
ታድያ በባህላዊዉ ንቅሳት አምራ አጊጣ የባህላዊ ቀሚስዋን አጥልቃ ያየ ሰዉ ነቃሽዋንም ተነቃሽዋንም ያሞካሻል በግጥም
ባህር ዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ግቢዉስጥ የተነሳችዉ ፎቶግራፍ ነዉ።
የሰዉነት ማስዋቢያ ድሪዳዋ ከተማ ላይ ባለንቅሳትዋ ሴት ጫት በመሸጥ ላይ ናቸዉ።
እንሶስላ የተባለዉ ተክል ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሰዉነት ማስዋቢያ በስፋት ይዉላል።
በተለይ በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ልጃገረዶችና ሴቶች እጅና እግራቸዉን እንሶስላ ይሞቃሉ።
ሰዉነትን በእንሶስላና ሂና ማሳመር እንደ እንሶስላ ሁሉ ሂናም ከጊዜ በኋላ የሚለቅ ከቅጠላ ቅጠል የሚሰራ የሰዉነት ቆዳ ማስጌጫ ነዉ።
በኢትዮጵያ በጎረቤት ሶማልያና ጅቡቲ ዉስጥም እንሶስላና ሂና በስፋት ለቆዳ ማስጌጫ ይጠቀሙበታል።
በፎቶ ላይ የምትታየዉ ወጣት በርበራ ከተማ ዉስጥ አንዲት ጠና ያሉት ሴት የእጅ ቆዳ በሂና ታሳምራለች።
ሴቶች በሂና እጅና እግራቸዉን ብሎም የእጅና የእግር ጥፍራቸዉን ያሳምራሉ ያስዉባሉ።
ሰዉነትን በንቅሳት ማሸለም ከሃያኛዉ ክፍለ ዘመን ወዲህ በዘመናዊ መልኩ በበርካታ የዓለማችን ክፍሎች እንደተስፋፋ ጽሁፎች ያመለክታሉ።
የንቅሳት ባህል ሊስፋፋ የቻለዉ የቴክኒክ እና የሥነ ጥበብ ስልጠና ያላቸዉ አዳዲስ ባለሞያዎች ወደ ዘርፉ በመግባታቸዉም እንደሆነ ተመልክቶአል።
ፎቶዉ ላይ የምትታየዉ ሃሚራ በሃርጌሳ በሚገኝ አንድ ባህላዊ ሆቴል ዉስጥ ትሰራለች።
ሃሚራ በሂና ቆዳዋን ለማሳመር የፈጀባት ደቂቃ ነዉ የከፈለችዉም ወደ አራት ይሮ ግድም ነዉ ።
ሃሚራ በምትኖርበት አካባቢ ሴቶች በሰርግ እንዲሁም በበዓላት ወቅት ሰዉነታቸዉን በሂና ያስዉባሉ።
አወዛጋቢዉ ዘመናዊነት በሃርጌሳ የ ዓመትዋ ናጂማ የቆዳ ማስዋብያ የተሰራዉ ከጥቁር አባያ ነዉ ።
በሶማሌ ላንድ ሴቶች ሂጃብ ይለበሳሉ እጅጌ ሙሉ ልብስም ነዉ የሚያደርጉት።
ግን በርካታ ሕዝብ በማይገኝበት ቦታ ላይ ሴቶች አለባበሳቸዉ ብዙ ሕዝብ እንደተሰበሰበበት ሁሉ ወግ አጥባቂ አይነት አይደለም።
እንደዉም ሰዉ ራሱ ላይ የሚያስረዉ ነገር ሳይሆን ራሱ ዉስጥ ባለዉ ይለካል የሚል አነጋገርም አላቸዉ።
የጅቡቲዉ ንቅሳት በጅቢቲና በሰሜናዊ ሶማሌላንድ በሂና የሰዉነትን ቆዳ ማስዋብ የተለመደ ነዉ።
በእነዚህ ሁለት አገራት የሚገኙ ማኅበረሰቦች ዘንድ ተመሳሳይ የሆኑ ባህልና ልማዶች ሲተገበሩ ይታያል።
ይህች የጅቡቲ ተወላጅ ታዳጊ ሕጻን ከጓደኞችዋ ጋር ሆና ዲግሪ ሴንቲ ግሪድ ሙቀት በሚለካበት እለት ጅቡቲ ባህር ዳርቻ ላይ ተቀምጣለች።
ይህም ለየሃገራቱ የልማት እንቅስቃሴ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ይታመናል ።
ታዲያ የአፍሪቃ ኤኮኖሚ ከውድቀት ሊድን የሚችለው እንዴት ነው ምክንያቶቹስ ምንድናቸው
የጀርመን የልማት ፖሊሲ ኢንስቲቲቱት የምጣኔ ሐብት ባለሙያ ታቲያና ቻሁድ በተለይ ሶሥት ነጥቦችን ዓቢይ መንስዔ አድርገው ይጠቅሳሉ።
ክፍለ ዓለሚቱ በተለይም በጥሬ ሃብት የታደሉት አገሮች ባለፉት ዓመታት ታላቅ ስኬት ነበራቸው።
ካህን እነዚህን ነጥቦች በማገናዘብ ለያዝነው ዓ ም ያቀረቡትን የአፍሪቃ ዕድገት ትንበያቸውን በሶሥት ከመቶ ገድበውታል።
ለዚያውም ቀውሱ ሥር መስደዱን ከቀጠለ ይህም የተጋነነ ግምት ነው የሚሆነው።
በመሆኑም ችግሩን መታገሉ በተቀዳሚ የአፍሪቃውያን የራሳቸው መሆኑን ቢያምኑም የበለጸጉት መንግሥታት ያለባቸውን ክፍለ ዓለሚቱን የመገደፍ ታሪካዊ ግዴታ አስረግጠዋል።
ዕርዳታችን እንደ መሰል የዓለም ነዋሪዎች ቀውሱ በአፍሪቃ የፖለቲካና የማሕበራዊ ኑሮ ላይ ባሳደረው ስጋት ሳቢያ የምናደርገው የሞራል ግዴታ ብቻ አይደለም።