input
stringlengths
1
130k
የጃማይካ ባህላዊ ሙዚቃዎቹን ከሂፕ ሆፕ የሙዚቃ ስልት ጋር አጣጥሞ ማቅረቡ በዚህኛው አልበሙም ተሳክቶለታል።
ቅዳሜ ምሽት በሰመርጃም መድረክ ላይ ሲወጣ ወገቡ ላይ የሚደርሱትን ድሬድ ፀጉሮቹን እያወዛወዘ ነበር።
የራፕ የሙዚቃ ስልት ላይ የምታተኩረው ኑራ ግጥሞቿ ለጆሮ የሚከብዱም ነበሩ።
በአንፃሩ ታዳሚውን ዘና እና ፈታ እንዲል ያደረገችው ሴት አቀንቃኝ የ ዓመቷ ጃማይካዊት ኮፊ ናት።
ከሰመርጃም የምትጠብቀቅ ደግሞ በትክክል አሁን እያገኘን ያለውን ነው የምጠብቀው።
አይሮፕላን ውስጥ ገብተን እስክናርፍ ድረስ ስንጠብቀው የነበረው ይሄንን ነው።
እኔም እዚህ ሰመርጃም ላይ የተገኙ ኢትዮጵያውያንን ወይም ትውልደ ኢትዮጵያውያንን አግኝቼ አነጋግሬያለሁ ይመስገን እባላለሁ።
እነሱን ለመጠየቅ እና ሰመርጃም ላይ ለመካፈል ብዬ ነው የመጣሁት።
ከይመስገን ጋር ከሲውዲን የመጡት ዘመጆቹ አማን እና ናዎሚም ደስ ብሏቸዋል ሰመርጃም የተዋጣለት ነው።
ናዎሚ ደግሞ በጣም ደስ ይላል ጥሩ ዘና ያሉ ሰዎች አሉ።
እንደዚህ አይነት ድባብ ለማግኘት ሩቅ መሄድ ያው ግድ ይላል።
በዚህ የሙዚቃ ድግስ ላይ ለመካፈል በርካታ ከብሪታንያ እና ከጀርመን ጎረቤት ሀገራት የመጡ ታዳሚዎች ገጥመውኛል።
ከነዚህ አንዱ የሆነው እና ከኦስትሪያ የመጣው ማርቲን የሬጌ ሙዚቃ አፍቃሪ መሆኑ እግሮቹን ሊነካ ትንሽ የቀሩት የድሬድ ፀጉሩ ከሩቅ ያመላክታሉ።
ከኦስትሪያ የመጣው ማርቲን አዎ በዚህ ዓመት እንደውም ትንሽ ይሻላል።
ባለፉት ዓመታት እኔም በተለይ በዚህ በአረንጓዴው መድረክ ላይ ሂፕ ሆፕ ብቻ ነበር የሚቀርበው ማለት ይቻላል።
በመጠኑ ሂፕ ሆፕ ቢኖር ምንም አይደል ብቻ የሬጌ ድግስ መሆኑን ይዞ ቢቀጥል ጥሩ ነው።
በዘንድሮው የሰመርጃም የሙዚቃ ድግስ የቦብ ማርሊይ ልጆችም ይሁኑ እንደ አልፋ ብሎንዲ ላኪ ዱበ የመሳሰሉ ዝነኛ የአፍሪቃ አርቲስቶች መድረክ ላይ አልነበሩም።
ይሁንና የቅዳሜው የመጨረሻ የመድረክ እንግዳ ቡጁ ባንቶን በጉጉት ሲጠበቅ ከነበሩት አርቲስቶች አንዱ ነው።
ቡጁ ባንቶን ገና የ ዓመት ወጣት ሳለ በአንድ ዓመት ውስጥ ከዝነኛው ቦብ ማርሊ የበለጠ በርካታ ዘፈኖቹ ቁጥር አንድ ሆነው ተጫውተዋል።
ተለማማጅ የሕክምና ባለሙያዎች ለተቃውሞ አደባባይ ወጡ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
አፍሪቃ ደቡብ ሱዳንን የራቀው የሰላም ተስፋ በውጊያ ጦርነቱ መሀል የደቡብ ሱዳን መንግሥት በሰጠው ምህረት መሠረት እስካሁን የፖለቲካ እሥረኞችን ፈቷል።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንደሚሉት በሺህዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን አሁንም በህገ ወጥ መንገድ እንደታሰሩ ነው።
ኂሩት መለሰ የደቡብ ሱዳን መንግሥት እና አማጽያን እዚህም እዚያም እየተዋጉ ነው።
በጦርነቱ የሰላማዊ ሰዎች ህይወት ማለፉና እና ዜጎችም ከቀያቸው መሰደዳቸው ቀጥሏል።
መንግሥት ከ ቀናት በፊት የአማፅያን ጠንካራ ይዞታ የነበረችውን ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የምትገኘውን የፓጋክ ከተማን መያዙን አስታውቆ ነበር።
አማጽያን ደግሞ ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ መልሰው በእጃቸው እንዳስገቧት ከትናንት በስተያ ተናግረዋል።
የደቡብ ሱዳን ውጊያ ማብቂያ ማጣቱ የሰላሙ ጥረትም አለመሳካቱ የሀገሪቱ እጣ ፈንታ ምን ይሆናል የሚለውን ጥያቄ ሁሌም ያስነሳል።
ላለፉት እና ዓመታት የታየው ችግር በአጭር ጊዜ የሚፈታ አይደለም።
ምክንያቱም ችግሮቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ መልካቸውን እና ይዘታቸውን እየቀየሩ የመጡበት ሁኔታ ነው ያለውና።
ጊዜም ጉልበትም የሰው ሀብትም የሀገር ሀብትም መብላቱ የማይቀር ነው።
በውጊያ ጦርነቱ መሀል የደቡብ ሱዳን መንግሥት በሰጠው ምህረት መሠረት እስካሁን የፖለቲካ እሥረኞችን ፈቷል።
እሥረኞቹ የተፈቱት ባለፈው ግንቦት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ብሔራዊ ውይይት ለማመቻቸት ባደረጉት ምህረት መሠረት ነው።
ሁሉም ማለት ይቻላል የታሰሩት የማጽያኑን መሪ የቀድሞውን ምክትል ፕሬዝዳንት ሪየክ ማቻርን ትደግፋላችሁ ተብለው ነው።
ኪር እነዚህን እሥረኞች ያለአንዳች ቅድመሁኔታ መፍታታቸው ችግሩን በሀገሪቱ ማቆሚያ ያጣውን ግጭት ለመፍታት መቁረጣቸውን ያሳያል ተብሏል።
ምክንያቱም የአማጽያን ኃይሎች ካቀረቧቸው ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ የታሰሩብን አባላት እና ደጋፊዎቻቸው ይፈቱ የሚል ነው።
የደቡብሱዳን መንግሥት የተቃዋሚዎችን ጥያቄ ተቀብሎ እንደተጠቀሰው የተወሰነ ቁጥር ያላቸውን ተቃዋሚዎች ከእስር ለቋል።
ይሄ በሁለቱ በኩል ያለውን የመቀራረብ እና ለመነጋገር ያለውን ፍላጎት የሚያሳይ ነው።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሰዎች ብቻ መፈታታቸው ችግሩን መሸፋፈኛ ነው ሲሉ አጣጥለዋል።
እነርሱ እንደሚሉት አሁንም በሺህዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን በህገ ወጥ መንገድ አሁንም እንደታሰሩ ነውና።
ዓመት ሊደፍን ጥቂት ቀናት የቀሩት የደቡብ ሱዳኑ ጦርነቱ ከሐገሪቱ ዜጎች አንድ አራተኛውን ማለትም ሚሊዮኑን አሰድዷል።
የማጽያኑ መሪ ማቻርም ዲፕሎማቶች እና የፖለቲካ ምንጮች እንደተናገሩት ደቡብ አፍሪቃ ነው የሚገኙት።
አቶ አበበ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ቀዳሚው ሚና የህዝቡ ሊሆን ይገባል ይላሉ።
በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ከጎረቤት አገሮችም ከዓለም አቀፉ ማህበራትም ይበልጥ የሱዳን መንግሥት እና የሱዳን ህዝብ ነው ባለቤቱ ።
በሦስተኛ ደረጃ ጎረቤት ሀገሮች እና ዓለም አቀፉማህበረሰብ የደቡብ ሱዳንን ችግር ለመፍታት ከመቼውም በላይ ካለፈው ስህተት ካለፈው ጉድለት ተምረው።
የሰብዓዊ ቀውስ በቻድ ሀይቅ አካባቢ በአፍሪቃ በቻድ ሀይቅ አካባቢ ዓለም አቀፉ ማህበረ ሰብ ያላስተዋለው ግዙፍ አሳሳቢ የሰብዓዊ ቀውስ ተከስቷል።
በቻድ ሀይቅ አካባቢ የናይጀሪያ ዓማፅያን ቡድን ቦኮ ሀራም ባስፋፋው ሽብርተኝነት ሰበብ ያካባቢው ሕዝብ ከመኖሪያው ተፈናቅሏል ወይም ለስደት ተዳርጓል።
ስፖርት ኅዳር ቀን ዓ ም በወልድያ ከተማ በደጋፊዎች መካከል ስለተፈጠረው ግጭት ስለእንግሊዝ ፕሬሚር ሊግ እና ጀርመን ቡንደስሊጋ ግጥሚያዎችን የምንለው ይኖረናል።
ሩስያ ከፒዮንግያንጉ የክረምት ኦሎምፒክ ውድድር ሙሉ ለሙሉ ልትታገድ ትችላለች።
በሁለቱ ቡድኖች መካከል ሊደርግ የነበረው ጨዋታም ለሌላ ጊዜ ተላልፏል።
በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ሳምንት ወሳኝ ጨዋታ አከናውኖ አራተኛ ደረጃን ተቆናጦ የነበረው አርሰናል በድጋሚ ደረጃውን አስረክቧል።
በጀርመን ቡንደስሊጋ የብሔራዊ ቡድኑ ተሰላፊ ወንድም ኬቪን ቦአቴንግ ፍራንክፉርትን የማታ ማታ ከጉድ አውጥቶታል።
በሩስያ ስፖርተኞች አበረታች ንጥረ ነገር ሲጠቀሙ መንግሥት እጁ ነበረበት ስለሚለው ክስ ነገ ውሳኔ ይሰጣል።
ሩስያ በደቡብ ኮሪያ የክረምት ኦሎምፒክ ሙሉ ለሙሉ ልትታገድም ትችላለች።
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ ውድድር ትናንት ወልድያ ከተማ ውስጥ ሊከናወን የነበረው ግጥሚያ ሳይካሄድ ቀርቷል።
ውድድሩ ሳይከናወን የቀረው በወልድያ ከተማ እና በመቀሌ ከተማ ቡድኖች ደጋፊዎች መካከል በተነሳው ግጭት ምክንያት ነው።
በግጭቱ የተነሳ በሰዎች እና በንብረት ላይ ስለደረሰው ጉዳት የተለያዩ ዘገባዎች በተለይም በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ወጥተዋል ።
የእግር ኳስ ደጋፊዎች ግጭት በየትኛውም ዓለም የሚከሰት ኩነት ነው።
ኾኖም ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰተ ያለው ግን ከሌሎቹ ለየት ያለ ይመስላል።
ከጊዜ ወደ ጊዜም የእግር ኳስ ደጋፊዎች በብሔር ተኮር ግጭቶች ሲሳተፉ መመልከት ተደጋግሟል።
ችግሩ ወደ አሳሳቢ ደረጃ ከመሻገሩ በፊትም የእግር ኳስ ግጥሚያዎችን የሚያደራጁ አካላት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጡት የሚገባ ጉዳይ ነው እንላለን።
ዛሬ ቡሩንዲ ከኢትዮጵያ እንዲሁም ኡጋንዳ ከዚምባብዌ ሊጫወቱ ቀጠሮ ተ ይዞ ነበር።
ሆኖም ዚምባብዌ ከውድሩ በመውጣቷ የዛሬ ግጥሚያ በኡጋንዳ እና ቡሩንዲ መካከል መሆኑ ተገልጧል።
ከተጀመረ ዓመታት ያስቆጠረው የሴካፋ ውድድር በአፍሪቃ አንጋፋ ውድድርነቱ ይጠቀሳል።
ዛንዚባር በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበራት ፌዴሬሽን የማኅበርነት ዕውቅና ለማግኘት ትግል ላይ ናት።
ሊቢያ እና ዚምባብዌ የዘንድሮ የሴካፋ ውድድር ተጋባዥ ቡድኖች ሲሆኑ ዚምባብዌ ከውድድሩ ወጥታለች።
ፕሬሚየር ሊግ በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ትናንት ዌስትሀምን ለ ድል ያደረገው ማንቸስተር ሲቲ ግስጋሴውን እንደቀጠለ ነው።
ከተከታዩ ማንቸስተር ዩናይትድ በስምንት ነጥብ በልጦ በያዘው ነጥቡ ደረጃውን እየመራ ይገኛል።
በአንጻሩ ቅዳሜ እለት ከዋትፎርድ ጋር አንድ እኩል የተለያየው የቶትንሀም ሆትስፐር አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ግን ቡድናቸው ዋንጫ የማግኘት ህልሙ መምከኑን አስታውቀዋል።
በነገራችን ላይ ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቶትንሀም ሆትስፐር ከአርሰናል የሚበለጠው በ ነጥብ ብቻ ነው።
ከስፓርታክ ሞስኮው ጋር የፊታችን ረቡዕ ለሚኖረው የሻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያ ጆዌል ተሽሎት ሊሰለፍ እንደሚችልም አሰልጣኙ አክለው ተናግረዋል።
ጆዌል በሌለበት የቅዳሜው ግጥሚያ የሊቨርፑሎቹ ተከላካዮች ኤምሬ ቻን እና አማካዩ ጊኒ ዊጅናልዱም ብቃታቸውን አሳይተዋል።
የቸልሲው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ደግሞ የቡድናቸው ወሳኝ ተጨዋች የሆነው ኤደን ሐዛርድ ብቃቱ ጫፍ ላይ አልደረሰም ብለዋል።
ዘንድሮ እስካሁን በተደረጉ ጨዋታዎችም ኤደን ሐዛርድ ግቦች ሲኖሩት ከመረፍ ያረፉ ኳሶችን ለቡድኑ አባላት አመቻችቶ መስጠት ችሏል።
ቡንደስሊጋ በጀርመን ቡንደስሊጋ መሪው ባየር ሙይንሽን ቅዳሜ እለት ሐኖቨርን ለ በመርታት ነጥቡን አድርሷል።
ቬርደር ብሬመን ሽቱትጋርትን ለ ቢያሸንፍም በ ነጥቡ ከደረጃ ሰንጠረዡ ወራጅ ቃጣና ግርጌ ከሚገኘው ኮሎኝ በ ነጥብ ከፍ ብሎ ይቃትታል።
ኛ ደረጃ ላይ ተዘርግቶ የሚገኘው ኮሎኝ እስካሁን በተደረጉ ግጥሚያዎች ያገኘው ነጥብ ብቻ ነው።
አንዷም ነጥብ ብትሆን ኮሎኝ ትናንት ከሻልከ ጋር ተጋጥሞ አንድ እኩል በመውጣት ያገኛት ናት።
አውስቡርግ ማይንትስን ትናንት ለ ሲያሸንፍ አይንትራኅት ፍራንክፉርት ቤርሊንን ለ ድል አድርጓል።
እነሱ እንዲያ ጥሩ በተጫወቱበት ልክ የእኛ አቋም መጥፎ ነበር።
አንድ እኩል አቻ ከወጣን በኋላ በእግርጥ በጣም ጥሩ ነበርን።
አይንትራኅት ፍራንክፉርት በ ነጥቡ ከአውስቡርግ እና ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ቦሩስያ ዶርትሙንድ የሚበለጠው በግብ ክፍያ ብቻ ነው።
አምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሆፍንሀይም በበኩሉ ከአይንትራኅት ፍራንክፉርት ጋር ያለው ልዩነት አንድ ብቻ ነው።
አሰልጣኙ ዳንኤል ዲቫዲ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ከቡድናቸው ገና ብዙ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
ያን ደግሞ ከሳምንታት በኋላ መስመር ስናስይ ያኔ ሌላ ቡድን ለመሆን አፍታም አይፈጅብን።
ቮልፍስቡርግ አራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቦሩስያ ሞይንሽንግላድባኅን ትናንት ለ ድል አድርጎ ነጥቡን ማድረስ ችሏል ደረጃውን ደግሞ ።
በደረጃ ሰንጠረዡ ላይፕትሲሽ ከሻልከ በአንድ ነጥብ በልጦ ሁለተኛ ነው።
ይህን ክስ የተከታተለው እና በ ዝርዝር ሰነድ ያቀረበው፦ ዓለም አቀፉ ጸረ ኃይል ሰጪ ንጥረ ነገር ኩባንያ ነው።
ሠነዱ በካናዳዊው ጠበቃ ሪቻርድ ማክላረን ይፋ ሲደረግ መላ ዓለም ጉድ ብሎ ነበር።
ሩስያ በዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ ስፖርት ውድድሮች ላይ ከዩናይትድ ስቴትስ እና ቻይና ጋር በመፎካከር ቀዳሚ መስመር ላይ ስትሰለፍ ቆይታለች።
በዚህ የስፖርት ቅሌት የሩስያ መንግሥት እጁ እንዳለበት ከተረጋገጠ ሩስያ ከሚቀጥለው የፒዮንግያንጉ የክረምት የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ሙሉ ለሙሉ ልትታገድ ትችላለች።
ደቡብ ኮሪያ ፒዮንግያንግ ውስጥ የሚከናወነው የክረምት ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ግጥሚያ ከሦስት ወራት ግድም በኋላ ከየካቲት እስከ የካቲት የሚዘልቅ ነው።
በልዩ ስብሰባው እነዚህና ሌሎችም የዓለም አቀፍ ስምምነቶች ረቂቅ አዋጆችን ምክር ቤቱ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡
ለገበያ ስፍራው ዝውውር ምክንያት የሆነውን የህዝብ መጨናነቅም ሆነ የፅዳቱን ጉዳይ የሚመለከታቸው አካላት ከወዲሁ መላ ቢሹለት የሚል ጥሪም ቀርቧል፡፡
ቻይና የባህላዊ መድሃኒቶችን በመጠቀም ስኬታማ በሆነ መልኩ የኮሮና ቫይረስን መቆጣጠር የቻለችባቸው መንገዶችን ለኢትዮጵያ ለማጋራት ፍቃደኛ መሆኗን ገልፃለች፡፡
በተለይ የቫይረሱ ህመም የመጀመሪያዎቹ ሁለት ደረጃዎችን ለማከም የተጠቀመችባቸውን ሁለት የመድሃኒቶች ዓይነቶች ለኢትዮጵያ በድጎማ መልክ ለመስጠት ተስማምታለች፡፡
የኢትዮጵያ የባህላዊ መድሃኒቶችም ህጋዊ ማዕቀፍ ኖሯቸው ወደ ስራ እንዲገቡ የተጀመረው ጥረት እንዲሳካም የቻይናን ልምድ ኢትዮጵያ ትፈልጋለች ብለዋል፡፡
ሸገር የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ ዶ ር ይናገር ደሴን አግኝቷል፡፡
ተህቦ ንጉሴ ጥሬ ልኮ ጥሬ መቀበል ኤፍሬም እንዳለ ሰውየው አሞሌ ጨው ሲስርቅ እጅ ከፍንጅ ይያዛል፡፡
ባለፉት አራት ወራትም ከእቅዱ በመቶ ቅናሽ ያለው ገቢ ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን ሰምተናል፡፡
በመመሪያው መሰረት ቀዶ ህክምና የሚደረግለት ሰው ከመደረጉ በፊት የቅደመ መከላከያ መድሃኒቶች መውሰድ አለበት፡፡