input
stringlengths
1
130k
በሳዑዲ አረቢያ መገናኛ ብዙሃን ስማቸው ከተዘረዘረ ባለሀብቶች መካከል በኢትዮጵያ በርካታ የንግድ ተቋማት ባለቤት የሆኑት ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ አንዱ ናቸው፡፡
መገናኛ ብዙሃኑ ያወጧቸው መረጃዎች ባለሀብቱን ፎቶ ጭምር የያዙ ቢሆንም ከእርሳቸው ወገን የተሰጠ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ ባለመሰጠቱ ነገሩን ድፍንፍን አድርጎታል፡፡
ጉዳዩን እየተከታተለ የሚገኘው የሪያዱ ዘጋቢያችን ስለሺ ሽብሩ ግን የአላሙዲን መታሰር ከምንጮቼ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
አላሙዲ የተወሰኑት ታሳሪዎች እንዲቆዩ ተደርገውበታል በተባለው የሪያዱ ሪትዝ ካርልቶን ባለአምስት ኮኮብ ሆቴል ውስጥ እንደሚገኙ ምንጮቹ እንደነገሩት ገልጿል፡፡
የሞሮኮ መገናኛ ብዙሃን ጥቅማቸው ስለሆነ የእርሳቸውን መታሰር በሰፊው ዘግበውታል ይላል ስለሺ፡፡
የሚለውን ለማጣራት በአዲስ አበባ ጉዳዩ ወደሚመለከታቸው ደጋግመን ብንደውልም ምላሽ የሚሰጠን ማግኘት አልቻልንም፡፡
የአሁኑ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለመሪነት በዕጩነት በቀረቡ ጊዜ የወረፏቸው ሁሌም በምሳሌነት ይነሳል፡፡
ልዑሉ ትራምፕን ለመላው አሜሪካ ማፈሪያ ሲሉ የጠሯቸው ሲሆን ከዕጩነትም ራሳቸውን እንዲያገልሉ ሁሉ ጠይቀዋቸው ነበር፡፡
የሪያዱ ስለሺ የልዑል አልወሊድ መታሰር ከባድ እርምጃ ነው ይላል፡፡
እርሳቸው ማለት እኮ ታማኝ ሸሪካቸው እና በንጉሳውያን ቤተሰብ ውስጥ የሚታመን አይነት ሰብዕና ያላቸው ሰው ናቸው፡፡
በተወሰነ ደረጃም የንጉሳውያን ቤተሰቡን የንግድ ጥቅሞች የሚከታተሉ የነበሩ ናቸው፡፡
ለበርካታ የንግድ ሰዎች እርሳቸው ተያዙ ማለት ባጣሙኑ የሚያደናግር ነው ይላሉ የፖለቲካ ተንታኙ፡፡
እስከ ቅዳሜ ምሽት ድረስ የሀገሪቱ ብሔራዊ ዘብ ኃላፊ የነበሩት ልዑል ሚጠብ ስልጣናቸውን ተነጥቀው እምብዛም ሳይቆይ ነው ለእስር የተዳረጉት፡፡
ልዑል ሙጢብ በአንድ ወቅት አሁን ኛ ዓመታቸውን የያዙትን የንጉስ ሰልማንን ዙፋን የመረከብ ተስፋ የነበራቸው ነበሩ፡፡
እንዲያም ሆኖ በሳዑዲ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን እና የአልሳውድን ስርወ መንግስት የመጠበቅ ኃላፊነት የተሸከመው የብሔራዊ ዘብ ኃላፊነት ይዘው ቆይተዋል፡፡
የልዑል ሙጢብ መታሰር የአልጋ ወራሹን የሞሐመድ ቢን ሰልማንን ስልጣን ለማደላደል የተወሰደ እርምጃ አድርገው ከሚያስቡት መካከል የፖለቲካ ተንታኙ ግርሃም ግሪፍትዝ ይገኙበታል፡፡
ሞሃመድ ቢን ሰልማን መጀመሪያ የመከላከያ ሚኒስትሩን ቀጥሎ የጸረ ሽብር እና የሀገር ውስጥ ደህንነት አገልግሎትን በእርሳቸው የበላይ ጠባቂነት ስር እንዲሆኑ አደረጉ፡፡
የብሔራዊ ዘቡን አመራርን ለመለወጥ የነበሩ ሌሎች ዕቅዶች ቢኖሩም ነገር ግን ቀጥተኛ መነሻ ምክንያቱ ያ ነው ይላሉ ግሪፍትዝ፡፡
ይህ የገንዘብ ምዘበራ ጉዳይ በመንግስት ባለስልጣናት ብቻ ሳይሆን ጉዳዩን በቅርበት በሚከታተሉ በተወሰኑ ተንታኞችም ዘንድ የሚቀነቀን እንደሆነ ስለሺ ይናገራል፡፡
የሳዑዲ ፖለቲካ ተንታኝ እና ጋዜጠኛ ማንሱር አል አሚር የእስር እርምጃው ከፖለቲካዊ ይልቅ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት አለው ብለው ከሚያምኑት አንዱ ነው፡፡
በሙስና የተያዙት ሰዎች በከፍተኛ ስልጣን ደረጃ ላይ ያሉና በርካታ ገንዘብም ያላቸው ናቸው፡፡
ይህ መሪዎቻችን የኢኮኖሚውን ዘርፍ እንደ ጠቃሚ ጉዳይ መውሰዳቸውን መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡
የፖለቲካ ተንታኙ ግርሃም ግሪፍዝ ግን ጉዳዩ የሙስና ዘመቻ መሆኑ ላይ ጥርጣሬ ያላቸው ይመስላል፡፡
እኔ እንደሚመስለኝ ነገሩ በትከክልም የጸረ ሙስና ጉዳይ ቢሆንም መንግስት የሚጠራጠረውን የዓለም አቀፉን ህብረተሰብ ለማሳመን አስቸጋሪ ጊዜ የሚገጥመው ይመስለኛል፡፡
ሁሌም ቢሆን ይህ ከፖለቲካ ስሌት እና አጀንዳ ጋር የተያያዘ መሆኑ ላይ ጥርጣሬ ይኖራል፡፡
ነገር ግን በዚህ ወቅት ማንም ሰው በሙስና ጉዳይ ሊመረመር እንደሚችል ለብዙዎች በግልጽ መልዕከት ያስቀመጠ ነው ሲሉ የሳዑዲ እስር አንደምታው ያስረዳሉ፡፡
ፌስቡክ የአምደመረቦች ሁሉ ቀዳሚ ተጠቃሚዎቹ በቁጥር ወደ ሚሊዮን አሻቅበዋል።
የሚሊዮኖችን መረጃ እንደያዘ ሰሞኑን ለአክሲዮን ገበያ መቅረቡ በኒውዮርክ ተጠቃሚዎቹ በቁጥር ወደ ሚሊዮን አሻቅበዋል።
በማዕከላዊ ወህኒ ቤት የእስር ጊዜ ኣሳልፌያለሁ የሚሉት አቶ ታዬ ዜናዉን ዉሳኔዉ አስደስቷቸዋል።
ዓለም አቀፍ ደረጃዉን የጠበቀ የምርመራ ተቋም ይባል እንጂ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመሳሳይ የእስረኛ አያያዝ መኖሩን አቶ ተማም ይጠራጠራሉ።
በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል የፍትህ ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የሥራ ሒደት ኃላፍ ሆነው የተሾሙት አቶ ታዬ በዚህ ላይ የሚጨሩት አለ።
ማዕከላዊን መዝጋት አንድ ነገር ሆኖ እያለ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል መደበኛ ባልሆኑ እስር ቤቶች ዉስጥ ታስረዉ ስለሚገኙት ብዙዎች እጣፋንታም የሚያነሱ አሉ።
አቶ ታዬ በፌስቡክ ገጻቸዉ ላይ የጠቅላይ ሚንሥትሩን ንግግር አስመልክተዉ በጻፉት አስተያየት ንግግራቸዉ ህወሀትን ንፁህ አድርጎ ደርግን ብቻ ወንጅሏል።
አቶ ኃ ማርያም የህወሀትን ጥፋት በተቻለዉ ሁሉ ለማስተባበል ጥሯል።
የሰማያዊ አባላት ፍርድ ቤት ሲለቃቸዉ ፖሊስ ያዛቸዉ አውዲዮውን ያዳምጡ።
የኢትዮጵያውያን የትንሳኤ በአል አከባበር በፈረንሳይ ይዘት ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ዘ ሄይግ ኔዘርላንድ የሚገኘው ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት የቀድሞው የኮትዴቩዋር ፕሬዝደንት ሎሮ ባግቦ ላይ የመሠረተውን ክስ አቋረጠ።
ሁለቱም ተጠርጣሪዎች ጠበቆች ለቀረበባቸው ክስ በቂ ማስረጃ ባለመገኘቱ ዳኞቹ ክሱን እንዲያነሱላቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል።
በዛሬው ዕለት ግን አቃቤ ሕግ በቂ ማስረጃ ማቅረብ እንዳልቻለ ያመለከቱት የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ዳኞች ሁለቱንም ከክሱ ነፃ ብለዋቸዋል።
ሎሮ ባግቦ እና ሻርል ብል ጉዴንም በመከላከያው መሠረት ከቀረቡባቸው ክሶች ሁሉ ነፃ በማለትም በአንቀጽ መሠረት ባስቸኳይ እንዲለቀቁም አዝዟል።
የዳኞቹ ውሳኔ በፍርድ ቤቱ ውስጥ የተቃውሞ እና ደስታ ጉምጉምታን አስከትሏል።
የሁለቱም ተጠርጣሪዎች ጠበቆች ለቀረበባቸው ክስ በቂ ማስረጃ ባለመገኘቱ ዳኞቹ ክሱን እንዲያነሱላቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል።
ዶይቸ ቬለ ህወሓት ውህደቱን ተቃውሞ ስለመውጣቱ በግንባሩ ውስጥ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የሆኑ ግለሰቦችን ምልከታ እንዲሁም የኢዜማን አስተያየት አሰባስቧል።
በደርግ ጊዜም በአንድ ቀን ስብሰባ ከሌኒን በላይ ሌኒኒዝምን የሰበከ ቄስ በኢትዮጵያ እንደነበር ስታውቅ ደግሞ ነገሩ የተለመደ መሆኑን ትረዳለህ።
ያ ማለት ብሔሮችና ብሔረሰቦች ከመቼውም ጊዜ የበለጠ እኩልነትን እና ፍትሃዊነትን በእናት አገራቸው ውስጥ ይጎናጸፋሉ።
ያ ማለት አንዳንድ ብሔር ብሔረሰቦች ሁልጊዜ ታሪክ እየተመዘዘ አይደረጉም።
ይህ ሁሉ የሚሆነው በውህድ ፓርቲው ውስጥ ነው ሲሉ ጽፈዋል ።
የህወሓት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አማኑኤል አሰፋ እንዳሉት ህወሓት ከፓርቲም ሆነ መንግሥታዊ ሕግጋት ባፈነገጠ ሂደት ውስጥ መግባት አይፈልግም።
እንደዚያ አይነት በኢትዮጵያ ህግም ሆነ በፓርቲው በኢህአዴግም ሆነ ብሄራዊ ፓርቲ የሚመሩባቸው ህጎች እንደዚያ አይልም ብለዋል።
አሁን እኔ ስላልተሳተፍኩኝ የስራ አስፈጻሚ አባል ስላልሆንኩኝ ምን እንደነበር ግልጽ የሆነ ዝርዝር ነገሮችን አላገኘሁም ።
እኔ በመርህ ደረጃ የህወሓት እና የትግራይ ህዝብ አቋም ግን አውቀዋለሁ።
ህወሓት በዚህ በሚካሄደው መንገድ ገብቶ መንቦጫረቅ እንደማይፈልግ ቀድሞ ግልጽ አቋም አውጥቷል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
የሀገሪቱ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ወደ አንድ አገራዊ ፓርቲ መዋሃዱ በበጎ ጎኑ እንደሚመለከት የገለጸው ደግሞ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ኢዜማ ነው።
የፓርቲው ድርጅት ጉዳይ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ እንዳሉት ውህደቱ አገሪቱ ከዘውግ አስተሳሰብ የፖለቲካ ምሕዳር መውጣት ስለመፈለጓ አመላካች ነው።
መወዳደር ያለባቸው በዘር በሀይማኖት ወይም በአካባቢ ሳይሆን በሚያመነጩት ሀሳብ ነው ባይ ነኝ።
እያንዳንዱን ዜጋም በሰውነት በኢትዮጵያዊነት ማየት አለባቸው የሚል ነው ያለኝ።
አጠቃላይ ሃሳቡ ከእኛ ሃሳብ ጋር የሚጣጣም አልነበረም ከዚህ ቀደም።
ስለዚህ ወደዚህ መቀየሩ እንደተባለው በፖለቲካ ሜዳው ላይ የሚፈጥረው ልዩነት ይኖራል ሲሉ አቶ የሺዋስ ተናግረዋል።
ኢህአዴግ ወደ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ብልጽግና ፓርቲ የውህደቱ የመጨረሻ ምዕራፍ የሚያደርሰውን የፓርቲውን ንድፈ ሃሳብ በማጽደቅ ወደ ግንባሩ ጉባኤ ማምራቱን አስታውቋል።
በኢሕአዴግ አገዛዝ ደግሞ ከሀገር ተሰደው ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ አድርገው ነበር።
ከረዥም ዓመታት የጽሞና ጊዜ በኋላ ላለፉት ሁለት ዓመታት በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች በተለይም በፌስቡክ ብቅ ብለው በተከታታይ ጽሑፎችን ያቀርቡ ነበር።
ባለፈው እሁድ በተወለዱ በ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገልጧል።
ስለ አቶ አሰፋ ጫቦ የሕይወት ታሪክ ዶክተር ካሳ ከበደን በማናገር መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
የሶማሊያ ፕሬዝደንት አላሚ ሶማሊያ ዉስጥ ትወለድ እንጂ በስደት አድጋ ተምራ ነዉ የራሷን ቤተሰብ ያፈራችዉ።
አሁን የአራት ልጆች እናት የሆኑት ፋዱሞ ዳይብ በቅርቡ የሶማሊያ የመጀመሪያዋ የሴት ፕሬዝደንት የመሆን ህልም ሰንቀዋል።
በጎርጎሪዮሳዊዉ ዓ ም ሶማሊያ ዉስጥ በተባባሰዉ የእርስ በርስ ግጭት ጦርነት ከወላጆቻቸዉ ጋር ታስረዉ ከሀገር ተሰደዱ።
የከባድ መኪና ሾፌር ከሆኑ አባት እና ከአርብቶ አደር እናቷ ጋር ኬንያ ዉስጥ የቆዩባቸዉን ጊዜያት ወደኋላ ያስታዉሱታል።
የስደት ህይወት ኬንያ ዉስጥ ሳይደላቸዉ የፊንላንድ መንግሥት ጥገኝነት ሰጥቷቸዉ ወደሄልሲንኪ ተጓዙ።
በትንሿ የፋዱሞ ዳይብ አዕምሮ ዉስጥ ግን በኬንያም ሆነ ፊንላንድ ማኅበረሰብ ያለመፈለግ ምሬት ተቀርፆ አድጓል።
ቀደም ሲል በነርስነት ፊንላንድ ዉስጥ ሲያገለግሉ የቆዩት ዳይብ በተመድ በመቀጠር ወደፑንትላንድ ተጉዛ በሴቶች እና እናቶች የጤና ዘርፍም ሠርተዋል።
ለዚህ ያነሳሳቸዉን ሲገልፁ ለፕሬዝድንነት ለመወዳደር ያነሳሳኝ ሶማሊያ ዉስጥ ቀጣይ የደም መፋሰስን የማስቆም የሞራል እና የሲቪል ግዴታ አለብን ብዬ ስለማምን ነዉ።
ዳይብ በምርጫዉ ለመፎካከር መዘጋጀታቸዉን በመጪዉ ሐምሌ ወር ለሶማሊያ ምክር ቤት ማቅረብ እና ማረጋገጫ ማግኘት ይኖርባቸዋል።
በዚያም ላይ ወደ ሺህ ዶላር ገደማ ማስያዣ ማስገባትም ይጠበቅባቸዋል።
በሶማሊያ ማኅበረሰብ ይህ አልተለመደምና ምን ያህል ድጋፍ አገኛለሁ ብለዉ ያስቡ እንደሆነ ከዶቼ ቬለ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ዳይብ እንዲህ ይላሉ።
ከዚህ ባሻገር ለአዲሱ ትዉልድ የግለሰቡ ማንነት ሳይሆን የሚያሳስበዉ ወደጠረጴዛዉ ላይ የሚያመጣዉ ምንድነዉ የሚለዉ ነዉ።
በዚያም ላይ ከፆታቸዉ ይልቅ ችሎታና እና የአስተዳደር ብቃታቸዉን ነዉ የሚመለከተዉ።
ፋዱሞ ዳይብ ይህን ይበሉ እንጂ ከወዲሁ ተከታታይ የግድያ ዛቻዎች ደርሰዋቸዋል።
የሶማሊያ የመጀመሪያ ሴት ፕሬዝደንት ለመሆን ያለሙት ዳይብ ይህ በጣም ግራ አጋቢ ነገር ነዉ።
በዚያም ላይ እንዲህ ያለ ማስፈራሪ ለሚደርሳቸዉም ሆነ እኔን እንገልሻለን ብለዉ ለሚያስፈራሩኝ ሰዎች ትክክለኛዉን ነገር መሥራት እንዳለብኝም የሚያሳስብ ነዉ።
እነዚህ ሰዎች በጣም ስጋት ገብቷቸዋል ማለት ነዉ እኔን በማስፈራራትም ወደሀገሪቱ ላመጣ ያሰብኩት ነገር አስፈላጊ መሆኑን እያመኑም ነዉ።
በእኔ ዉስጥ የአስተዳደር ችሎታ ተመልክተዋል ራዕይ ያለዉ መሪ ህዝቡን አገልጋይ መሪ አይተዋል ማለት ነዉ።
ምክንያቱም እኔ ኃላፊነቱን ከያዝኩ ህልዊናቸዉ ስጋት ላይ እንደሚወድቅ ያዉቃሉ ማለት ነዉ።
ይህ ነዉ ሶማሊያ ዉስጥ በሺዎች ለሚቆጠሩት ሞት ምክንያት የሆነዉ።
ቀጣዩ ምርጫ የራሳቸዉን ጥቅም ብቻ የሚያስቡ ጥላቻን የተሞሉ የጎሳ መሪዎች የሚመረጡበት ከሆነ በጣም የተበላሸ ስርዓት ነዉ የሚሆነዉ።
በዚህ በአራት ነጥብ አምስት አካሄድ የሚመረጥ ማንኛዉም ፕሬዝደንት ከፍተኛ ብቃት የሌለዉ እና ሙሰኛ ሰዉ ነዉ የሚሆነዉ።
በፍቃዱ ኃይሉ ለዶይቸ ቬለ ከምልካቸው መጣጥፎች መካከል የበኩሬ በሆነው እና የኢሕአዴግ ዳግማይ ትንሳዔ ወይስ ዜና እረፍት
ይሁንና ከዓመት በኋላ ያንን ድምዳሜዬን የሚያስገመግም ፖለቲካዊ ለውጥ ተከስቷል።
አምና ኢሕአዴግ ከጥቂት አባላቱ በቀር በጅምላ ይቅርታ አግኝቶ ነበር አሁን ዓይንህን ላፈር የሚሉት እየበዙ ነው።
አምና እምነት ሰጪዎቹ እና ተስፈኞቹ ብዙ ነበሩ ዛሬ ተጠራጣሪዎቹ እና ድንጉጦች በዝተዋል።
አምና የግንባሩ አባል ድርጅቶች እየተጎሻሸሙም ቢሆን ኅብረታቸውን እንደጠበቁ ነበር ዘንድሮ ግን አብረን ለመሥራት እንቸገራለን እየተባባሉ ነው።
ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ እና አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አሁን ዛቻ እና ማስፈራሪያውን ይፋ አወጡት እንጂ በሐሳብ ደረጃ እንደተጣሉ ግልጽ ነበር።
እነሆ ተሳክቶላቸው ሥልጣን ከተቆጣጠሩ በኋላ መገለል ደርሶብኛል የሚለውን ሕወሓት አገሪቱ ውስጥ ለተከተለው አለመረጋጋት ተጠያቂ እያደረጉ ከርመዋል።
የኢሕአዴግ መፍረስ ምልክቶች ኢሕአዴግ የተመሠረተው በሕወሓት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።
ይሁንና ሕወሓት በመሠረተው ኢሕአዴግ ውስጥም ይሁን በብዙኀኑ ዘንድ ያልተመጣጠነ የሥልጣን የበላይነት በማከማቸት ሲታማ ኖሯል።
በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመጡ በኋላ ሕወሓት ኢሕአዴግ ውስጥ ብቸኛ ሀጢያተኛ ተደርጎ መሣሉ የአደባባይ ምሥጢር ነው።
ተቃዋሚዎችም ይህንን ሁኔታ የጠላቴ ጠላት በሚል መርሕ ተቀብለው ከቀሪዎቹ የኢሕአዴግ እህት ፓርቲዎች ጋር ስልታዊ ወዳጅነት ጀምረዋል።
የኢሕአዴግን መፍረስ የሚያመላክተው ሌላኛው ምልክት የደቡብ ክልል ለመበታተን መዘጋጀቱ ነው።
በቅርቡ ከታየው የፖለቲካ ለውጥ ወዲህ በደቡብ ክልል በርካታ ዞኖች የክልልነት ጥያቄ ማንሳታቸው ይታወቃል።
እነዚህ አዳዲስ ፓርቲዎች የኢሕአዴግ አባል ሆነው የሚቀጥሉበት ዕድል ያለ ቢሆንም፥
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ውሕድ ፓርቲ የመመሥረት ሕልም ሌላኛው የኢሕአዴግ ግንባር መፍረስ አይቀሬ መሆኑን አመላካች ነው።