input
stringlengths
1
130k
ይህ ንግግር መቼም ተፈፀመ መቼ የኢሕአዴግ ፍፃሜ አይቀሬ መሆኑን ያመላክታል።
በኢሕአዴግ ውስጥ ሥነ ስርዓት መልሶ ማስፈን ለየትኛውም ጠቃሚ ንቅናቄ መፈጠር እንደ ቅድመ ሁኔታ አስፈላጊ ነው።
ኢሕአዴግ እንደ ግምባር በጋራ የፈጠረውን ችግር በጋራ ለመፍታት ፈቃደኛ አልሆነም።
ይልቁን በግለሰቦች ብሽሽቅ እና ኩራት ምክንያት የብዙኀኑን ጥቅምና ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል ሌላ አዲስ ገጽታ ያለው ችግር ፈጥሯል።
ይህንን ችግር ለመፍታት አባል ድርጅቶቹ በጥሞና የሚያስቡበት ጊዜ አሁን ነው።
የዶክተር ነገሪ ሌንጮ ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር በሶስት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት የመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክን ሲመርቁ እንደተናገሩት ፓርኮቹ በርካታ የሰዉ ኃይል በመቅጠርም የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራሉ ብለዋል።
የሕገ ወጥ ሰዉ አሸጋጋሪዎችን መረብ ለመከላከል በዓለም አቀፍ የባህር ላይ ያሠማራዉ ተልዕኮ አሉታዊ ዉጤት እንዳለዉ ተቺዎች እየጠቆሙ ነዉ።
የአዉሮፓ መርከቦች ከባህር ዳርቻ ሃገራቱ የባህር ክልል ከሆነዉ ከ ማይል ዞን ዉጭ ነዉ የሚንቀሳቀሱት።
እዉነት ነዉ ይህ ዘመቻ የመፍትሄዉ አካል እንዲሆኑ ሰዎቹን የመሳብ ሚና አለዉ።
እናም የሊቢያ መንግሥታዊ ይዞታ መስመር እስካልያዘ ድረስ ሕገ ወጥ ሰዉ አሸጋጋሪዎቹ ተግባራቸዉን ሊያቆሙ አይችሉም።
የሕገ ወጥ ሰዉ አሸጋጋሪዎቹን እንቅስቃሴ ለመግታት የሚደረገዉ የባህሩ ላይ ተልዕኮ አሉታዊ ዉጤት አስከትሏል ከተባለ ይህን ተግባር ማስቆም ታዲያ እንዴት ይቻላል
ማርቲን ኮብለር በአንድ በኩል ጠንከር ያለ ርምጃ መዉሰድ ያስፈልጋል።
ይህ ወንጀል ነዉ እናም ሰዎቹ ወደ ሕግ ፊት እየቀረቡ መቀጣት አለባቸዉ።
በሕገ ወጥ መንገድ አሸጋጋሪዎቹ ሰዎቹን ከሱዳና እና ኒዠር በሰሃራ በረሃ አቋርጠዉ እዚህ ድረስ ያመጧቸዋል።
እዚህ ደግሞ በመጠለያ ጣቢያዎች አንዳንዴም መንግሥት በሚያንቀሳቅሰዉ መጠለያ ዉስጥ ይቀመጣሉ።
ይህ ደግሞ አንዳንዴ የሰብዓዊ መብቶች የማይከበሩበት ሊሆን ስለሚችል እኛ ስጋት አለን።
ማርቲን ኮብለር ላለፉት አንድ ዓመት ሊቢያ ዉስጥ ለተመድ ተልዕኮ ድጋፍ የሚሰጠዉን ተልዕኮ ሲመሩ ቆይተዋል።
በዚህ ቆይታቸዉ ግን የታሰበዉን ያህል ማሳካት እንዳልተቻለ ነዉ የጠቆሙት።
ማርቲን ኮብለር በተልዕኮዬ ማብቂያ ላይ ያን ያህል ትልቅ የሚባል የሊቢያ መፍትሄ ላይኖር ይችላል።
በዚህ ዓመት ባደረግነዉ ደስተኛ አይደለሁም ለምሳሌ ስደትን በተመለከተ ማለት ነዉ።
ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ሊቢያን በተመለከተ ጠንከር ያለ አካሂድ ቢኖረዉ እመኛለሁ።
ከዚህ የአዉሮጳ ኅብረት አካል ወደሆነችዉ ወደ ማልታ የ ደቂቃ በረራ ብቻ ነዉ።
ሌላዉ ለማርቲን ኮብለር የቀረበዉ ጥያቄ ሊቢያ የከሸፈች መንግሥትና ሀገር ናት ማለት ይቻል ወይ
የሚል ነዉ ሊቢያ መንግሥትነቷን ያላረጋገጠች በትክክል አስቸጋሪ ሀገር ናት።
ከ ቱ የጋዳፊ አምባገነናዊ ዓመታት በኋላ ሀገሪቱን አንድ አድርጎ ለመምራት በጣም አስቸጋሪ ሆኗል።
የሊቢያን ብሔራዊ የጦር ሠራዊት ለማቋቋም የታሰበዉ እንደታቀደ እስካሁን ባይሳካም በቅርቡ ግን ይሳካል የሚል ተስፋቸዉንም ገልጸዋል።
ባህል የዓለም ከተማና የፋተርሽቴትን ወዳጅነት ሰላምታና ምስጋናን በአማረኛ ቋንቋ ያቀርባሉ ጀርመናዊዉ የፋተር ሽቴተን ከተማ ነዋሪ።
የዓለም ከተማ እና የፋተር ሽቴትን የእህትማማች ማህበት ዋና ተጠሪም ናቸዉ።
እስከ ዛሪ ለ ግዜአት ወደ ኢትዮጵያ ሄጄ ሀገሪትዋን ጎብኝቻለሁ።
በዚህም ኢትዮጵያን አንድ ቱሪስት ማወቅ ካለበት የበለጠ በደንብ አዉቃታለሁ ማለት እችላለሁ።
ገጠር ሄጄ ጎጆ ቤት ዉስጥ ኖሪ አዉቃለሁ በጎጆ ቤት ዉስጥ የሚኖሩ የምረዳቸዉ ቤተሰቦችም አሉኝ።
በጎ አ በ ዓ ም ይህ ማህበር ሲቋቋም ማህበሩ ዋና ተጠሪ በመሆን ለአስራ ሰባት ዓመታት አገልግለዋል።
በጀርመኗ በፋተርሽታትን ከተማ ነዋሪ የሆኑት የማህበሩ የኮሚቴ አባል ከሆኑ ወ ሮ ራሄል መኮንን ይህን ማህበር ከተቀላቀሉ አምስት ዓመት እንደሆናቸዉ ይናገራሉ።
ማህበሩን ተቀላቅለዉ ጀርመናዉያኑ በዓለም ከተማ ለሚገኙ ህዝቦች የሚያደርጉት ስራና ጥረታቸዉን እንዲህ ያደንቃሉ።
ማህበራችን በዓለም ከተማና ፋተርሽታትን ከተሞች መካከል ያለዉን ነዋሪ ህዝብ በወንድማማችነት ማስተሳሰር ነዉ።
ይህን ስል በመጀመርያ ደረጃ በአካባቢዉ ላይ ለህጻናት ትምህርት ድጋፍ መስጠት ነዉ።
እስካሁን ሁለት ህጻናት መዋያ ሰርተናል አንድ አነስተኛ ቤተ መጻህፍትም አለን።
በአሁኑ ወቅት ህጻናት በመዋለ ህጻናቱ ለአንደኛ ትምህርት የሚያበቃቸዉን የትምህርት ዝግጅት ያደርጋሉ።
በአስተማሪነት እና ህጻናቱን በመጠበቅ ባጠቃላይ አዋቂዎች በዚሁ የማዋለ ህጻናት ተቀጥረዉ ያገለግላሉ።
ለህጻናቱ በቂ የማንበብያ ቦታ ስለሌለን ተለቅ ያለ ህንጻ ሰርተን ከሰሞኑ ለማስመረቅ ዝግጅት ላይ ነን።
በዚህም የማህበሩ የመጀመርያ ተጠሪ ሴፕ ክሊመንት በጎ አቆጣጠር ዓ ም ኢትዮጵያን ለመጀመርያ ግዜ ለመጎብኘት ይጓዛሉ።
ኢትዮጵያ እንደገባሁ የተሰማኝ ይላሉ ሴፕ ክሊመንት በመቀጠል መጀመርያ ወደ ኢትዮጵያ ስሄድ የተሰማኝ ስሜት ከዝያ በፊት የማለዉቀዉ ስሜት ነበር።
ልክ ኢትዮጵያ እንደገባሁ ባዕድ ሀገር ሳይሆን እራሴ ሀገር እንደገባሁ ያህል ነበር የተሰማኝ።
የሰዉ ልጅ ህይወትን ከ እና በፊት ወደኋላ መለስ ብዪ እንዳይ እንዳስብ አድርጎኛል።
በጎ አቆጣጠር ዓ ም ኢትዮጵያ ዉስጥ የገጠመኝ የህዝቡ የአኗኗር ሁኔታ ከ ዓመት በታሪክ የማዉቀዉን የሰዉ ልጅን የአኗኗር ሁኔታ ነዉ።
ሰዎች ከባድ ሸክምን እየተሸከሙ በርቀት የሚጓዙበትን ነዉ ያየሁት እናም እነዚህ ሰዎች ለምን ብስክሌትን አልፈጠሩም ስል እራሴን መጠየቄን አስታዉሳለሁ።
ግን ሁኔታዉን ጠልቄ ስመለከተዉ እንኳን ስለ ብስክሌት ስለ ተሽከርካሪ ለማሰብ ቀርቶ ለእግር መንገድ አዳጋች ነዉ።
በመጀመርያ አካባቢዉ ላይ እንደመጣሁ ሴቶች በእንስራ ዉሃ ተሸክመዉ ረጅም መንገድን ሲጓዙ ነበር ያየሁት።
አሁን አሁን ደግሞ በቢጫ ደንበጃን ጭንቅላታቸዉ ላይ ተሸክመዉ ሲሄዱ ተመልክቻለሁ።
እና ይህ ሁሉ የባህል የአኗኗር ቀዉስን ሳይሆን በጣም የሚያሳዝን የሚያስጨንቅ ስሜት ነዉ የፈጠረብኝ።
የአለም ከተማ እና የፋተር ሽቴትን የእህትማማች ማህበር በዚህ ረገድ ያለዉ የስራ ግልጽነት እስከም ድረስ ነዉ
የወቅቱ የባህበሩ ሊቀመንበር ጀርመናዊዉ አንቶን ሽቴፈን እንደሚሉት ከሆነ ማህበራችን በርግጥ እጅግ ግዙፍ የሚባል አይደለም።
በዚህም እንደ ትልልቅ ድርጅቶች በታዋቂ የሂሳብ አጣሪዎች ወጪ ገቢ የሚታይበት ሳይሆን የማህበሩ አባላት ወጭ ገቢዉን ይቆጣጠራሉ ዓመታዊ ስብሰባንም ያደርጋሉ።
ኢትዮጵያ ደርሰን ስንመጣም ማህበሩ የሰራዉን በቦታዉ ላይ ያለዉን ነገር ለአባላቱ ስብሰባ በመጥራት እናሳዉቃለን።
ለሚደርስን ጥያቄዎች በግልጽነት መልስ እንሰጣለን ማህበሩ በኪሱ ያለዉንም ገንዘብ የማህበሩ አባላት ያሳዉቃሉ ገንዘቡን ይቆጣጠራሉ።
ይህንኑ ድግስና ጉዞ በቢዲዖ ቀርጸዉ በጀርመን በተለያዩ አጋጣሚዎችም በማሳየት ላይ ናቸዉ።
የስደተኞች ሞት ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ኑ በኢትዮጵያ ሥሩ የተባለበት መድረክ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ሳምንታዊ በሆነዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ ለሕዳሳዉ ግድብ በሚደረገው የቦንድ ሽያጭ መካከለኛዉ ምሥራቅ ከሚገኙ ዜጎች ከፍተኛው ገቢ መገኘቱም ተነግሯል።
መግለጫውን የተከታተለው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል።
በስድስት ወር ውስጥ ብቻ በ የምርጫ ወረዳዎች መድረስ መቻሉን ገልጿል
የፖለቲካው አየር ይበልጥ መዳመን ሲይዝ በብዙ ከተሜ ወጣት ኢትዮጵያውያን ዘንድ የሚጠበቅ አንድ ነገር አለ የኢንተርኔት መቋረጥ፡፡
በዚህ ረገድ ባለፈው ሳምንትም ተመሳሳይ ችግር እንዳጋጠማቸው የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች እማኝነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው እና ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የአዳማ ነዋሪ በተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸው ኢንተርኔትን አብዝተው እንደሚጠቀሙ ይናገራሉ፡፡
ከዓለም ጋር ከሀገር ውስጥም ከምንም ግንኙነታችን ተቋርጧል ይላሉ የአዳማው ነዋሪ፡፡
የከፍተኛ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት እኚሁ የአዳማ ነዋሪ ለትምህርታቸው የሚጠቅማቸውን መረጃ ብዙውን ጊዜ ከኢንተርኔት ያፈላልጋሉ፡፡
ካለፈው ሳምንት ወዲህ ግን ከኢንተርኔት መረጃዎች ማውረድ ዳውንሎድ ይቅርና ከጓደኞቻቸው ጋር እንኳ መልዕክት መለዋወጥ አልቻልኩም ይላሉ፡፡
የግድ ሲሆንባቸው ግን ብሮድባንድ እና ገመድ አልባ የኢንተርኔት ግንኙነት ያለባቸው ቢሮዎች እየሄዱ ደጅ ይጠናሉ፡፡
የተንቀሳቃሽ ስልክ ኢንተርኔት አገልግሎት ወደነበረበት ይመለሳል በሚል በየጊዜው መሞከራቸውንም አልተውም፡፡
እኛ ለዛሬ ማታ ዳውንሎድ እናደርጋለን ብለን ከገዛን ወይም ዛሬ ቀን ካደረግን ከ ሰዓት በኋላ የለም፡፡
የአዳማው ነዋሪ የኢንተርኔት መቋረጡ በእርሳቸው ከተማ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎችም እንደሚስተዋል ይናገራሉ፡፡
የአዳማውን ነዋሪ እማኝነት ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የሱሉልታ ነዋሪም ይጋራሉ፡፡
በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የኢንተርኔት ብቻ ሳይሆን የመደበኛ የተንቀሳቃሽ አገልግሎት የኔትወርክ ችግር እንዳለ ከዘመድ ጓደኞቻቸው መስማታቸውን ይናገራሉ፡፡
የኔትወርክ ሙሉ ለሙሉ የመቋረጥ ችግር ትላንት ማክሰኞ ታኅሳስ በሱሉልታም ተከስቶ እንደነበር ያስረዳሉ፡፡
በአካባቢያቸው ስላለው የተንቃሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት አገልግሎት ችግር ደግሞ ተከታዩን ብለዋል፡፡
በተለይ በኦሮሚያ ክልል ወደዚህ ወደ ሱልልታ ጭራሽ ዳታው አይከፍትም፡፡
የሱሉልታው ነዋሪ የኢንተርኔት አገልግሎት መስተጓጉሉን ከባድ ችግር ነው ይሉታል፡፡
በሀገሪቱን ሁኔታ አንዳንድ የምናገኘውን መረጃ አለማግኘት ራሱ በጣም ከባድ ነው ይላሉ ነዋሪው፡፡
ከሱሉልታ አቅራቢያ በምትገኘው በመዲናይቱ አዲስ አበባም የኢንተርኔት ችግር ይስተዋላል፡፡
አገልግሎቱን በተለይ ማግኘት የማይቻለው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ለመጠቀም ሲሞከር እንደሆነ ተገልጋዮች ይናገራሉ፡፡
ማንነቱ እንዳይገለጽ የሚፈልግ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ ይህን የተጠቃሚዎችን አስተያየት ያረጋግጣል፡፡
በተለይ ደግሞ ቫይበር እና ዋትስ አፕ ላይ የጽሁፍ ግንኙነት የተፈቀደ ቢሆንም ፎቶዎች እና ቪዲዮዎችን መለዋወጥ የተከለከለ ነው፡፡
ምክንያቱም ለምሳሌ ጠዋት አካባቢ ቫይበርም ሆነ ዋትስ አፕ አይሰራም ነበር፡፡
ግልጽ ሆኖ እነኚህ ተዘግተዋል እነዚያ አይዘጉም ለማለት የሚያስቸገርበት ቦታ ላይ ነው ያለነው ይላል ባለሙያው፡፡
በኢትዮጵያ ያሉ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች እንዲህ እንዳሁኑ ጊዜ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን እንዳይጠቀሙ እቀባ ሲጣልባቸው እገዳውን ጥሰው አገልግሎቱን የሚያገኙባቸው ዘዴዎች ነበሩ፡፡
እንደ ሳይፎን ኦፔራ ማክስ እና አልትራሰርፍ አይነት አፕልኬሽኖችን በመጠቀም የተከለከሏቸውን ድረ ገጾች ሲጎበኙ ቆይተዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ የነበረው የኢንተርኔት እገዳ እነዚህንም ከአገልግሎት ውጭ ያደረገ ነበር፡፡
ከቀናት በኋላ የተወሰኑት እንደቀድሞው መልሰው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ተጠቃሚዎችም ሆነ ባለሙያው ይገልጻሉ፡፡
በኢትዮጵያ እንዲህ ሄድ መለስ የሚል የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት ለተጠቃሚዎች እንግዳ ነገር አይደለም፡፡
ኢንተርኔት ተዘጋ ሲባል ግን ወይ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎቱ ይቋረጣል አሊያም የተወሰኑ አገልግሎቶች ተለይተው እገዳ ይጣልባቸው ነበር፡፡
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያው ባለፈው ዓመት ከግንቦት ወር መጨረሻ ግድም ጀምሮ የነበረውን የኢንተርኔት መቋረጥ ከአሁኑ የአገልግሎቱ እቀባ ጋር ያነጻጽራል፡፡
ባለፈው ዓመት መጀመሪያ አካባቢ የሆኑ ድረገጾች ወይም የሆኑ አፕልኬሽኖች በግልጽ ተዘግተው ነበር፡፡
ጭራሽ የሆነ ጊዜ ላይ ምንም አይነት የ ግንኙነት በስልክም በኮምፒውትርም በኤድኤስኤልም በገመድ አልባም የለም ነበር፡፡
ከዚያ በኋላ ወደ ተመጣና የቀሩት ድረ ገጾች ተለቀቁ ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ነገ ደግሞ ያለው ሁኔታ አሁን የሆነ ነገር ብልህ ተቀይሮ ነው የሚጠብቅህ ሲል በየጊዜው ተለዋዋጭ ስለሆነው የኢንተርኔት አዘጋግ ያስረዳል፡፡
እንዲህ በየጊዜው ተቀያያሪ በሆነው የኢትዮጵያ የኢንተርኔት ክልከላ ለተጠቃሚዎች ሁነኛ መላ የሆነው የ ግንኙነትን አሊያም ፕሮክሲ ሰርቨሮችን መጠቀም ነው፡፡
ኢንተርኔት በሚዘጋባቸው በሌሎች ሃገራትም በመፍትሄነት እያገለገሉ ስለሚገኙት ስለእነዚህ ሁለት ዘዴዎች ባለሙያው ማብራሪያ አለው፡፡
በኢንተርኔት ውስጥ የትም አካባቢ ሆነህ የራስህ የሆነ ትንሽዬ ኔትወርክ መፍጠር ነው ፡፡
በመላው ዓለም ባሉ የተወሰኑ ኮምፒውተሮች ላይ እንደዚያ አይነት ኔትወርክ መስራት ነው የ ሀሳብ፡፡