input
stringlengths
1
130k
ፕሮክሲም በተመሳሳይ ነገር ነው የሚሰራው ግን የደህንነት ነገሩ ትንሽ አስቸጋሪ ነው፡፡
ስለዚህ ያችን የጎረቤት ሀገር እንደ ወይም እንደ ተጠቀመባት ማለት ነው፡፡
በአሁኑ የኢንተርኔት እገዳ የተወሰኑ የ አፕልኬሽኖች ለቀናት መዘጋታቸው ምኑን መፍትሄ ሆኑት
እርሱ በነጻ አይገኝም ግን የአፕልኬሽኑ በደንብ ይሰራል እስካሁን ምንም ዓይነት ችግር አላየሁበትም፡፡
ወይም ደግሞ ከጓደኞቻችሁ ን በመጠቀም መለዋወጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡
ሶፍትዌር መጫን ለማይችሉ ለ ተጠቃሚዎች ደግሞ የሚባል ድረገጽ አለ፡፡
ከዚያ ላይ የመጠቀሚያ ስም እና የይለፍ ቃል ብቻ በማውረድ የ አገልግሎት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ተጨማሪ ሶፍትዌር መጫን ሳያስፈልግ አፕል ስልኮች ላይም ሆነ ማክ ኮምፒውተሮች ላይ ይሄን ነገር መጠቀም ቀላል አማራጭ ነው ይላል ባለሙያው፡፡
ባለሙያው እንደዚህ አይነት ቪ ፒ ኤኖችን አስመልክቶ የመጨረሻ ምክር አለው፡፡
ከጉብኝቱ በፊት፧ የጀርመን የአረንጓዴው ፓርቲ፧ ብርቱ ተቃውሞ ያሰማ ሲሆን፧ ጉዱንም ለፓርላማ በማቅረቡ፧ ከነገ በስቲያ ክርክር ይደረግበታል።
የ ተ መ ድ፧ልዊስ ሞሬኖ ኦካምፖ፧ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በዳርፉር፧ ግፍ ሳይፈጽሙ እንዳልቀሩ የጠረጠሯቸውን ሱዳናውያን ባለሥልጣናት ሥም ጠቅሰዋል።
ወደ ሱዳን ተጎዞ ከነበረው የልዑካን ቡድን አባላት መከከል፧ የተሰኘውን የኢንዱስትሪ ኩባንያ ተጠሪ ን የዶቸ ቨለዋ አነጋግራቸዋለች ተክሌ የኋላ አቀናብሮታል።
ያም ሆኖ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሁኔታዎችን ለማስተካከል ሥርዓት ለማስያዝ በመሞከር ላይ መሆኑን ነው ያስረዱት።
ደቡብ ሱዳን ውስጥ ብዙ መሠራት እንዳለበት ነው ጎብኚው በበኩላቸው ያስገነዘቡት።
የሱዳን ማዕከላዊ መንግሥት፧ በዳርፉር የሚካሄደውን የህዝብ ጭፍጨፋ እንዲገታ እርምጃ ባለመውሰዱ፧ ዘወትር እንደተወቀሰ ነው።
የልዑካኑ ቡድን፧ ለመሆኑ፧ በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ተነጋግሮ ነበር ወይ
መንግሥት ራሱ፧ በዚህ ጉዳይ ላይ በፍጹም የመወያየት ፍላጎት አላሳየም።
የልዑካኑ ቡድን አባላትም፧ የፖለቲካ ጉዳዮችን እንዲያነሱ ኀላሲነት የተሰጣቸው አልነበሩም።
ከልዑካኑ ጉዞ በፊት የአረንጓዴው ፓርቲ፧ የዳርፉር ውዝግብ ይበልጥ በተባባሰበት በአሁኑ ወቅት፧ የኤኮኖሚ ትብብር ማድረግ አስፈላጊ አይደለም ሲል ነቀፌታ ሰንዝሯል።
ለሚለው ጥያቄ፧ ፊሊፕ ሙዑለር፧ እንዲህ ዓይነቱ ጥያቄ፧ በእርግጥ ከንግድ ጋር የተያያዘ ነው።
ገጠሩን ሱዳን፧ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር የሚያስተሣሥር ሲሆን፧ ለአገሪቱ የኤኮኖሚ ግንባታም፧ እጅጉን ተፋላጊ ነው።
እናም ይህን የአረንጓዴውን ፓርቲ ጥያቄ አግባብነት ያለው ሆኖ አላየውም።
ያም ሆኖ ዚመንስ ኩባንያ ከሱዳን ከወጣ በኋላ፧ ለሱዳን በሰፊው የተጠየቀውን ላማቅረብ መዘጋጀቱ የሚገርም ነው ።
ተጎጂዎች እንዲካሱ ተጠያቂዎች ለሕግ እንዲቀርቡ አሳስበዋል ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ብንያም በለጠ ወጣት ብንያም የከፈተው ሜቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በአሁኑ ጊዜ እስከ ሰዎች ለሚጠጉ ሰዎች ርዳታ ይሰጣል።
ብንያም በለጠ በዶቼቬለ አድማጮች ጥቆማ በአካባቢያቸው በአርአያነት ከሚጠቀሱ ሰዎች መካከል ከፍተኛውን ድምፅ በማግኘት በአንደኝነት ተመርጧል።
የአዲስ አበባ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ከወጣቱ ጋር ቆይታ አድርጓል።
ከተያዙት መካከል የክልሉ የፀጥታ ሃላፊ እና የቀድሞ ባለሥልጣናት ይገኙበታል ነው የሚባለው።
በድሬዳዋ አስተዳደር ቀበሌ ባለፈው እሁድ በደረሰው ግጭት እና ሑከት በትንሽ ግምት ሰዉ መገደሉ ተዘግቧል።
ሁከት እና ረብሻዉን ቀስቅሰዋል ወይም አባብሰዋል ተብለዉ የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ከሚሽን ሰሞኑን አስታውቋል።
ሻለቃ አሊ ሰመሪ ሲገዱ የተቃዋሚው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር የኦብነግ እና የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጥምረት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ናቸዉ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዋና ሳጂን ባንተ ዓለም ግርማ ግጭት በመቀስቀስ የተጠረጠሩ ሰዎች መታሰራቸውን ተናግረዋል።
በሻለቃ አሊ እምነት የድሬዳዋውም ሆነ የሶማሌ ክልሉ ሁከት እና ረብሻ መነሻ ምክንያት አንድ ነው።
ሳጂን ባንተ ዓለም አያይዘውም ድሬዳዋን ለማረጋጋት ፖሊስ እና ህብረተሰቡ በጋራ እይተንቀሳቀሱ መሆኑን ተናግረዋል።
በደቡብ ክልል የደራሼ ወረዳ ወቅታዊ ሁኔታ በደቡብ ክልል ደራሼ ወረዳ ተነስቶ በነበረዉ ግጭት ፊደራል ፖሊስ ገብቶ ሁኔታዉን በአንፃራዊ ማረጋገጡ ተነገረ።
ኮንጎ ምርጫ እና ጠመንጃ ታሽስኬዲ እና ደጋፊዎቻቸዉ ትናንት የምርጫ ኮሚሽኑን ሕንፃ ከበዉ ምርጫዉ እንዳይጭበረበር ሲጠይቁ ነበር።
የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የረጅም ጊዜ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ካቢላ በመጪዉ ታሕሳስ ሊደረግ በታቀደዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እንደማይወዳደሩ ትናንት በይፋ አስታዉቀዋል።
ትራንስ አትላንቲኩ የነጻ ንግድ ጽንሰ ሃሣብ እርግጥ አዲስ ባይሆንም የአሁኑን ያህል እጅግ አስፈላጊ የሆነበት ቀደም ያለ ጊዜ አይታወስም።
ይህም በዓለም ላይ ያለውን የሃይል አሰላለፍ በጣሙን መቀየሩ አልቀረም።
የቡድን ሃያ ሚናም እንዲሁ ቀውሱን ተከትሎ እያደገ መምጣቱ ይታወቃል።
እንግዲህ አሜሪካና የአውሮፓ ሕብረት በመካከላቸው ነጻ የንግድ ውል በማስፈን በተለይም ቻይናን ለመቋቋም ማለማቸው ጎልቶ የሚታይ ነገር ነው።
በዓለምአቀፉ ንግድ ላይ መልሶ በመጠናከር ይበልጥ ተጠቃሚ ለመሆን ይፈልጋሉ።
የአውሮፓ ሕብረትና የዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት በዓለም ላይ በሁል አቀፍነቱ ሰፊው ነው።
ግማሹን የዓለም ገቢ የሚጠቀልል ሲሆን በያመቱ የሚደረገው ንግድና የሚሰጠው አገልግሎት ዋጋ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገደማ ይጠጋል።
በትራንስ አትላንቲኩ የነጻ ንግድ ውል ድርድር መጀመር ደግሞ የጀርመኗ ቻንስለር ወሮ አንጌላ ሜርክልም ታላቅ ደስታ እንደተሰማቸው ነው የገለጹት።
የዚህ መሰሉ የነጻ ንግድ ውል ሃሣብ ትልቅ ደጋፊ ነኝ።
በሌላ በኩል ታዳጊ ሃገራት እንዲሁም የአሜሪካ የቆዩ የንግድ ሸሪኮች ሜክሢኮና ካናዳ ተጎጂ ሊሆኑ ይችላሉ።
ለማንኛውም የአውሮፓ ኮሚሢዮን ፕሬዚደንት ሆሴ ማኑዌል ባሮሶ ከአሜሪካ ጋር የሚደረግ የነጻ ንግድ ውል ለሕብረቱ የሚኖረውን ጠቀሜታ ከማመልከት ወደ ኋላ አላሉም።
በእርሳቸው ዕምነት ውሉ ገቢር ቢሆን የአውሮፓን አጠቃላይ ብሄራዊ ምርት በ ከመቶ ከፍ ሊያደርግ የሚችል ነው።
በአንድነት በዓለም ላይ ታላቁ የሆነውን የነጻ ንግድ ክልል ለመፍጠር እንፈልጋለን።
ስምምነቱ ሰፍኖ በተግባር መተርጎም ከያዘ የአውሮፓ ኤኮኖሚ ከአጠቃላይ ምርቱ አንጻር ከመቶ ዕድገት የሚያስቆጥር ይሆናል።
ይህን የሚሉት የሕብረቱ የንግድ ኮሜሣር ካሬል ዴ ጉህት ሲሆኑ ጉዳዩ ኩባንያዎችንና ፖለቲከኞችን የሚያበረታታ ነው።
ለነገሩ ለዚህም ነው ሁለቱ ወገኖች ነጻ ንግድን ለማስፈን መጣር የሚኖርባቸው።
በተለይ በውጭ ንግድ ላይ ያተኮረው የጀርመን ኤኮኖሚ ደግሞ በዚህ ይበልጥ ተጠቃሚ ነው የሚሆነው።
እንግዲህ ከኤኮኖሚ ስሌት ቢነሱ ሁሉም ነገር የነጻውን ንግድ ውል የሚደግፍ ይሆናል።
በዚህ ጉዳይ ተጠራጣሪ ሆነው የሚገኙት የተጠቃሚው ጠበቆችና በአውሮፓ ፓርላማ የአረንጓዴው ወገን ፖለቲከኞች ናቸው።
በእርግጥም የምግብ መርት ደህንነት ዋስትናን በተመለከተ ሁለቱ ወገኖች በጣሙን የተራራቁ ናቸው።
ለምሳሌ ያህል የአሜሪካ የጸጥታ ተቋማት የአውሮፓ ዜጎችን የኢንተርኔት የግል ዳታዎች በሰፊው ይዘዋል።
በአውሮፓ ፓርላማ የሶሻሊስቱ ወገን መሪ ሃነስ ስዎቦዳ ሰሞኑን አመኔታ ጠፍቷል ሲሉ ነበር የተናገሩት።
እንደራሴው የአውሮፓ ሕብረት ለንግድ ውሉ ሲል የዳታ ጥበቃ ዋስትናውን አሳልፎ መስጠት የለበትም ባይ ናቸዉ።
የአውሮፓ ብዙ ወጥ ፊልሞች በሆሊዉድ የገንዘብ ልዕልና መፎካከር አቅቷቸው እንዳይጠፉ ትልቅ ስጋት ነው ያለው።
ለማንኛውም ድርድሩን በተመለከተ የአውሮፓው ፓርላማ ዘጋቢ ቪታል ሞሬይራ እንዳሉት በመሠረቱ የባሕል እጦት ፍርሃቻ ሊኖር አይገባም።
ይህ በአውሮፓ ሕብረት ውል ውስጥም በአንቀጽ ሶሥት በግልጽ የተቀመጠ ነገር ነው።
ታዲያ ማንኛውም ስምምነት ውሉን ካላከበረ ሕግ መንግሥቱን የሚጻረር ይሆናል።
እናም በፍርድቤት ክስ ሊያስነሣ የሚችል ጉዳይ ነው አውሮፓውያን እንደሚያደርጉት ሁሉ አሜሪካም በበኩሏ ለምሳሌ የፊናንስ አገልግሎቱን ዘርፍ ለራሷ ከልላ መያዙን ትሻለች።
ሁለቱም ወገን እንግዲህ ከድርድሩ ተነጥሎ እንዲቀር የሚፈልጉት ነገር አለ ማለት ነው።
እናም ይህ ከሆነ ትራንስ አትላንቲኩ የነጻ ንግድ ውል ቢሰፍንስ ምን ይጠቅማል የሚል ጥያቄን ማስነሣቱ አይቀርም።
በሌላ በኩል እጅግ ጠቃሚ ስለሆነው ስለ ቻይና ጉዳይ በይፋ አንድም ነገር አልተባለም።
እንደ ዕውነቱ ከሆነ ድርድሩ የተነሣው በቻይና ምክንያትና ለቻይና አለን ገና አስፈላጊ ነን የሚል መልዕክትም ለማስተላለፍ መሆኑ ግልጽ ነው።
ለቻይና ገና አሁንም ጠቃሚ ነን የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ መሆኑ የተሰወረ አይደለም ለኤኮኖሚው ባለሙያ ታዲያ ይህ የኋልዮሽ ሂደትን ያህል ነው።
ለማንኛውም አሁን በመጀመሪያ በድርድሩ የአሜሪካና የአውሮፓ ጋራ ፍላጎት ምን ያህል ገፍቶ ሊሄድ እንደሚችል መታዘቡ ይመረጣል።
ኢትዮጵያ ፍትሐ ነገሥት ከሚባለዉ ጥንታዊ የነገሥታት ደንብ ተላቃ ከዘመናዊ ሕገ መንግሥት ጋር ከተዋወቀች ዘንድሮ ዓመት ደፈነች።
በ የመጀመሪያዉ ዘመናዊ ሕገ መንግሥት መፅደቁ ከተነገረበት ጊዜ ወዲሕ በአማካይ በየሃያ ዓመቱ አዳዲስ ሕገ መንግሥት ፀድቆላታል።
በዚሕም ሰበብ ኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ከማሻሻል ይልቅ ባጭር ጊዜ ብዙ በመቀያየር ከሚታወቁ ጥቂት ሐገራት አንዷ ናት።
አራተኛዉ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ከፀደቀ ሃያኛ ዓመቱን በቅርቡ ደፍኗል።
ሥራ ላይ ከዋለ ደግሞ ኝ ዓመት ከመንፈቅ ግድም ቢሆዉ ነዉ።
ከከዛኽስታን ወደ ጀርመን በመመለስም የጀርመን የጀርመን የሕዋ ምርምርና የጠፈርተኞች ማሠልጠኛ እሚገኝበት ኮሎኝ ገብቷል።
ይሁንና ጉዞው የተለያዩ ሳንኮች ሊያጋጥመው ይችል እንደነበረ ሊዘነጋ አይገባም።
መንኮራኩሩ ወደ ምድር ከባቢ አየር ሲገባ ትክክለኛ ማዕዝን ተክትሎ መብረር ይኖርበታል።
ከአየር ወደ ምድር መውረጃው ልዩ ጃንጥላ መከፈት መቻል አለበት የመንኮራኩሯ ፍጥነት መግቻ መሳሪያም በትክክል መሥራት ይጠበቅበታል።
ይህ ሁሉ ያላንዳች ሳንክ የሚከናወን ነው ብሎ መጠበቅ አይቻልም።
በሕዋ የሚደረገው ምርምር ውጤት በምድር ላይ ለሚኖሩ ሰዎች የሚሰጠው ጠቀሜታ እስከም ን ድረስ ነው
ከምድር ርቆ ክብደት ትርጉም የለሽ በሆንበት ማለትም የስበት ኃይል ፈጽሞ በሌለበት ቦታ በሰው ሰውነት ውስጥ ምን ዓይነት ለውጦች ናቸው የሚታዩት
ጠፈርተኞች በሕዋ ረጅም ጊዜ ቆይተው ወደ ምድር ሲመለሱ የስበት ኃይል መኖርና አለመኖር ምን ያስከትልባቸዋል
ለዚህም ነው ጠፈርተኛ አሌክሳንደር ጌርስት ትናንት ኮሎኝ መዳረሻ ፖርትዝ በሚገኘው ቤተ ሙከራ እንደደረሰ አጠቃላይና ሰፊ የጤና ምርምራ እንደሚደረግለት የተገለጠው።
ከተተኮረባቸው ዐበይት ጉዳዮች መካከል በተለይ የሰውነት አካላት ቶሎ የማርጀት ጉዳይ ዋናው ነው።
የቆዳ መጨማተር የአጥንት መሟሸሽ በአፋጣኝ የሚከሠተው ከመሬት ይልቅ በሕዋ ነው።
ስለሆነም በአንድ በኩል ለጠፈርተኞች ደሕንነት ማሰቡ እንዳለ ሆኖ በህክምና ረገድ የሚደረገው ሰፊ ምርምርም ትልቅ ትርጉም ነው የሚሰጠው ።
ቀስ በቀስ በምድር ላይ ካለው ብርቱ የስበት ኃይልም ሆነ ክብደት ጋር እንደገና የመለማመዱ ሂደት በጥሞና ክትትል የሚደረግበት ይሆናል።
ወራት ከስበት ኃይል ቁጥጥር ውጭ የቆየ ሰው ወደ ምድር ሲመለስ በመጀመሪያ ግር የሚያሰኝ ሁኔታ ያጋጥመዋል።
ልብ በሉ ሰው ሲጋደም የራስ ቅሉ ከቀሪው የሰውነቱ ክፍል ሁሉ የተዘቀዘቀ መስሎ ሲሰማው
የስበት ኃይል በሌለበት በሕዋ ደም ሲዘዋወር ባመዛኙ ወደ ጭንቅላት ነው የሚሠራጨው ።
በመሬት ጭንቅላት ከላይ እግር ከታች ሆኖ ነው ደም በመላ ሰውነት ውስጥ የሚዘዋወረው።
ታዲያ የቦታ ለውጡ በጤንነት ላይ የሚያስከትለው የሆነ ሳንክ እንዳይኖር በጥሞና መከታታል ተፈላጊ ይሆናል።
ምዕራባውያን ጠፈርተኞች ከሕዋ መልስ ለምርመራ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የበረራና የሕዋ አስተዳደር መቤት ነበረ የሚላኩት።
አሁን ግን በፖርትዝ ኮሎኝ በሚገኘው በመባል በታወቀው ዘመናዊ ልዩ ቤተ ሙከራ ነው ምርመራው የሚካሄደው።
ልዩውን የህክምና ምርመራ ለማከናወን ብቃቱ ያላቸው ሃኪሞች መኖራቸውን ጀርመናውያን ን ማሳመን እንደቻሉም ነው የገለጡት።
መልስ ጉዞው በሕዋ ጣቢያ ላቦራትሪ ም መሥራቱም ቢሆን ሁሉም ከአደጋ ነጻ ነው ማለት አይቻልም።
በመጀመሪያ ሳይንስ ምንጊዜም ሰዎችን እንደሚጠቅም እንደሚረዳ ነው የምገነዘበውና ተስፋም የማደርገው።
በዓለም አቀፍ የሕዋ ቤተ ሙከራ የሚካሄደው ምርምር ምድር ላይ ሰዎችን ይጠቅማል።