input
stringlengths
1
130k
ከባለለፈው አጋማሽ ጀምሮ የ የመጀመሪያ ሶስት ወራት በአማካኝ በወር ወደ ስደተኞች ነበር የሚመጡት።
አሁን በሚያዝያ ወር ግን ቁጥሩ በ አራት እጥፍ አድጎ ከ በላይ ስደተኞች ናቸው የመጡት።
በምስራቅ ኣፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን ኢጋድ አማካኝነት ሲካሄድ የከረመው ድርድር አደራዳሪዎቹን ተስፋ አስቆርጦ ያለ ውጤት ተቋርጧል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለደቡብ ሱዳን ቀውስ ተጠያቂ የሆኑ ሰዎች የሚዳኙበት የፍትህ ሥርዓት ቢቋቋም አገራቸው በገንዘብ ለመደገፍ ዝግጁ ነች ብለዋል።
ባለፈው ወር እንኳ በአፐር ናይል እና ማላካል አካባቢዎች ግጭቶች መከሰታቸው ተሰምቷል።
ድርጅታቸው በዚህ አመት ብቻ ደቡብ ሱዳናውያን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ይጠብቃል።
አወዛጋቢው በአማራና በትግራይ ክልሎች ያለው የአስተዳደር ወሰን አውዲዮውን ያዳምጡ።
በኢትዮጲያ በፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ምክንያቶች በቡዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደ ተለያዩ አገራት ይፈልሳል።
ዓለም በ ከጥር እስከ ሰኔ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
አንጋፋ የእግር ኳስ ኮከብ ሚሼል ፕላቲኒ የተያዙት በ ዓ ም ኳታር የዓለም ዋንጫ እንድታስተናግድ ስትመረጥ ሙስና ተፈጽሟል በሚል ጥርጣሬ ነው።
የቀድሞው የአውሮጳ እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዝዳንት ሚሼል ፕላቲኒ ከሙስና ጋር በተያያዘ ዛሬ በፈረንሳይ ፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ።
አንድ የአሜሪካ ገለልተኛ መርማሪ ይፋ ባደረገዉ መረጃ ኳታር በ የዓለም እግር ኳስን ለማስተናገድ የምርጫ ድምፅን ገዝታለች።
በፍንዳታው የሞቱት እና የቆሰሉት በአሌክሳንድሪያ እና ታታ ከተሞች የሆሳዕናን በዓል በማክበር ላይ የነበሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ናቸው፡፡
የመጀመሪያው ፍንዳታ የደረሰው ከካይሮ በስተሰሜን ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በምትገኘው ታታ በተሰኘችው ከተማ ዛሬ ረፋዱ ላይ ነበር፡፡
ፍንዳታው የደረሰበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የሆሳዕናን በአል በሚያከብሩ ምዕመናን ተጨናንቆ እንደነበር አሶሴትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
በወደብ ከተማይቱ አሌክሳንድሪያ በሰዓታት ልዩነት በደረሰው ሁለተኛው ፍንዳታ ደግሞ ቢያንስ ሰዎች ሲሞቱ ቆስለዋል፡፡
በግብጽ ክርስቲያኖች ላይ ጥቃት እንደሚያደርስ ሲዝት የቆየው ራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ ቡድን ለሁለቱ ፍንዳታዎች ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡
ግብጽን በሚቀጥለው ሳምንት ይጎበኛሉ ተብለው የሚጠበቁት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ጥቃቱን አውግዘውታል፡፡
ካለፈው እሁድ ማታ አንስቶም የድምፅ ቆጠራ በመካሄድ ላይ ሲሆን ህዝቡ አሁን ውጤቱን ለማወቅ በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ነው የሚገኘው።
ሰዎችን ስታነጋግር የተለያዩ የራዲዮ ጣቢያዎችን ዘገባዎች ስታዳምጥ በተከታታይ በአገሪቱ በመላ ጊዜያዊ የድምፅ ውጤቶችን እንደሚያስተዋውቁ መገንዘብ ይቻላል።
በምርጫ ው ዘመቻ ዋናው የመከራከሪያ ነጥብ ኤኮኖሚ ሆኖ ተገኝቷል።
ምንም እንኳጋና ኤኮኖሚዋ እያበበ ነው ቢባልም ብዙሃኑ የአገሪቱ ተወላጆች በጉስቁልና በድህነት ነው የሚኖሩት ።
ይሁንና በወር ማለቂያ ላይ ደመወዝ ሲከፈላቸው ኑሮን ለመግፋት በቂ እንዳልሆነ ነው ተጨባጩ ሁኔታ የሚያሳየው።
መጓጓዣው ራሱ ከቤት ወደ ሥራ ቦታ ግማሹን የሠራተኛውን ደመወዝ እምሽክ ያደርገዋል።
በጋና ትምህርት ነጻ ቢሆንም እስከ ኛ ደረጃ ማለት ነው ወላጆች ለመጻህፍትና ተማሪዎች ለሚያስፈልጓቸው የትምህርት መሣሪያዎች መክፈል አለባቸው።
በዛ ያሉ ወጣቶች ሥራ በማጣት ሲንገላወዱ ነው የሚታዩት ።
ኤኮኖሚ ድህነት ትምህርት ከአነዚህም ጋር የጤና ጥበቃ ችግር የሀኪሞች እጥረት ሌላው ዐቢይ የመነጋገሪያ ርእስ እንደነበረ ቲጃኒ ጠቁሞአል።
ለየ ው ጋናዊ አንድ ዶክተር ነው የሚደርሰው የህክምና ዶክተር
በአገሪቱ በመላ ለየአሥር ሺው ጋናዊ አንድ ዶክተር ይደርሰዋል ቢባልም አብዛኞቹ ዶክተሮች የተከማቹት በደቡብ ነው በተለይ በአክራና በኩማሲ
የርእሳነ ብሔር ልውውጥ ሲደረግም ያሁኑ ኛ ጊዜ ይሆናል ማለት ነው።
የመጨረሻው ውጤት ከተገለጠ በኋላ መጥፎ ነገር ሁከት ወይም ይህን የመሰለ እንከን የሚያጋጥም አይመስልኝም።
የሴቶች መጠቃትና የሚንስትሮች ዉይይት የአፍሪቃ ሚንስትሮች ደግሞ በአፍሪቃዉያን ሴቶች ላይ ሥለሚፈፀመዉ ጥቃት ገና እየተወያዩ ነዉ።
የሕንድ አደባባዮችን ያጨናነቀዉ ሕዝብ የተቃዋመዉ ደፋሪዎችን ብቻ ሳይሆን የሴቶችን መደፈር በቅጡ አይከላከሉም፥
ጠንካራ ቅጣትም አይጥሉም ያሏቸዉን የሐገራቸዉን መንግሥትና ሕግ አስከባሪዎችን ጭምር ነዉ።
የአፍሪቃ ሚንስትሮች ደግሞ በአፍሪቃዉያን ሴቶች ላይ ሥለሚፈፀመዉ ጥቃት ገና እየተወያዩ ነዉ።
ትናንት አዲስ አበባ የተሰየመዉን ሥብሰባ የተከታተለዉ ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ የስብሰባዉ አለማ ሒደት እንደሚከተለዉ ዘግቦታል።
ሁለትም አልፈለጉም ሰወስትም ትዕግስታቸዉ እስኪያልቅ ስንት ሰዉ ሕይወቱን መገበር እንዳለበት አይታወቅም አውዲዮውን ያዳምጡ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ አምና በዚሕ ወቅት ሚሊዮነ ሚሊዮናትን ያስፈነደቀዉ የሠላም የዴሞክራሲ የፍትሕ ብልፅግና ተስፋ ዘንድሮ ባመቱ ባጨናገፍ ኮስምኗል።
በደስታ ተስፋ ፈንጠዝያዉ ምትክ በአብዛኛ ሐገሪቱ የጎሳ ግጭት ግድያ መፈናቀል ጥርጣሬና አለመተማመን ነግሷል።
ባለፈዉ አንድ ዓመት በነበረዉ ግጭት ቁርቁስ የተገደለዉን ሠዉ ብዛት በሺ የሚቆጠር ከማለት በስተቀር በትክክል የቆጠረዉ የለም።
በተፈናቃዮች ብዛት ግን ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንደሚሉት ኢትዮጵያ ታሕሳስ ምብቂያ በተጠናቀቀዉ የጎርጎሪያኑ ከዓለም አንደኛ ሆናለች።
ጠብ ዉዝግቡ ማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ወደ ስድብ ጥላቻ ቅጥፈት ክሕደት መድረክነት ለዉጧቸዋል።
ርዕሠ ከተማ አዲስ አበባ ሳትቀር የኔች አይደለችም ዱላ ቀረሽ ዉዝግብ ምክንያት ሆናለች።
የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅርብ የሚከታሉ እንደሚሉት አንዳድ አካባቢዎች የየራሳቸዉን ነፃ መንግስት የመሠረቱ ይመስላል።
ሁለትም አልፈለጉም ሰወስትም ትዕግስታቸዉ እስኪያልቅ ስንት ሰዉ ሕይወቱን መገበር እንዳለበት አይታወቅም።
ሌሎች የፖለቲካ ተንታኞች ኢትዮጵያ መንታ መንገድ ላይ ናት ይላሉ።
የሽግግሩን ሒደት የገጠመዉ እንቅፋት ምክንያቱና መፍትሔዉ የዛሬ ዉይይታችን ትኩረት።
ከተሜ ወጣቶችና አለባበሳቸው በአንዳንድ በኢትዮጵያ ከተሞች የሚኖሩ ወጣቶች ከምዕራቡ ዓለም የወሰዱት አለባበስ የሚያሳርፈው ተፅዕኖ መኖሩን አንዲት የማህበረሳብ ባለሙያ ገለፁ።
ጠ ሚ ዐብይ ዬኤስ አሜሪካን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል ይዘት ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የ ሚሊዮን ህዝብ መኖሪያ የነበረችዉ ደቡብ አረቢያዊቷ ሀገር የመን ላለፉት ዓመታት በጦርነት እየታመሰች ትገኛለች።
አቶ ስዩምና አቶ ታየ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የኢዴፓ መግለጫ የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በምህጻሩ አዴፓ ለመጪው ዓመት የታቀደው ምርጫ እንዲራዘም ጠየቀ።
የኢሕአዴግ መንገድ እና የልማታዊ መንግሥት እጣ ፈንታ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚዳንት ታቦ እምቤኪ ያደረጉት የሽምግልና ጥረትም አንዳች የተከረው ነገር የለም።
ውዝግቡ በአንዲህ ከቀጠለ ኮት ዲቯር እንደገና እርስ በርስ ጦርነት ውስጥ እንዳትገባ ብርቱ ሥጋት አለ።
አላሳነ ዑታራ ከመቶ ተፎካካሪያቸው ሎራ ግብግቦ ደግሞ ከመቶ ድምፅ ማግኘታቸው የተገለጠ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የዑታራን አሸናፊነት ተቀብሎታል።
አባላት ያሉት የአፍሪቃ ኅብረትም ተመሳሳይ አቋም ያለው በመሆኑ የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚዳን ታቦ እምቤኪ ይሸመግሉ ዘንድ ልኮ ጥረታቸው ፍሬ አላስገኘም።
ሎራ ግብግቦ በምንም ዓይነት ሥልጣን አሳልፌ አልሰጥም ከማለታቸውም የራሳቸውን የቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓት በማዘጋጀት ፕሬዚዳንትነታቸውን አውጀዋል።
የቀድሞው የአማጽያን መሪና ያሁኑ ጠቅላይ ሚንስትር ጊዮም ሶሮ ትናንት የዑታራ ተጓዳኞች የተባሉ የአዲሱ መንግሥት ሚንስትሮች ናቸው ያሏቸውን ሰዎች ሠይመዋል።
ሶሮ ለፈረንሳይ ራዲዮ በሰጡት ቃልም ኮት ዲቯር ከሁለት አትከፈልም ሲሉ ተናግረዋል።
በምርጫ መሸነፋቸውን አልቀበልም ያሉት ሎራ ግባግቦ በበኩላቸው የአቢጃ ዋና ዩኒቨርስቲ አስተዳዳሪ የነበሩትን የኤኮኖሚ ምሁር ን ጠ ሚንስትር እንዲሆኑ ሾመዋቸዋል።
የአፍሪቃ የሰብአዊ መብት ማኅበር በፈረንሳይ ዓለም አቀፍ ራዲዮ ባሰማው ቃል ላይ ሎራ ግባግቦ የመራጩን ህዝብ ፍላጎት ያከብሩ ዘንድ ጠይቋል።
የዚሁ ማኅበር ሊቀመንበር ኢብራሂም ኮነ ሎራ ግባግቦ ኀላፊነት የሚሰማው ሰው መሆናቸውን እንዲያሳዩ ለራሳቸውም ክብር ሲሉ ተገቢውን እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።
በኮት ዲቯር ህዝብ ለተመረጡትና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ድጋፍ ለተሰጣቸው አላሰነ ዑታራ ሥልጣኑን ቢያስከብሩ ይበጃል።
ይህን ማኅበረሰብ በመወከል የቡርኪና ፋሶው ርእሰ ብሔር ብሌስ ኮምፓዖሬ ይሆናሉ ለሽምግልና የሚሠማሩት።
በመሃሉም ፍጥጫው ያስፈራቸውበመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የዑታራ ደጋፊዎች በከፊል ከሚቆጣጠሩት የኮት ዲቯር ግዛት ወደ ምዕራብ እየሸሹ አጎራባች ላይቤሪያ ገብተዋል።
ሚሊዮን ዜጎች ያሏት ኮት ዲቯር አሁን በጭንቅ ላይ የምትገኝ ስትሆን ምን ቢደረግ ይበጃል
ለሚለው ጥያቄ መልስ ከመገኘቱ በፊት ታቦ እምቤኪ ትናንት አቢጃ እንደገቡ እንዲህ ብለው ነበር።
ምን ማድረግ እንደሚገባ ሃሳብም ሆነ ምክር ከማቅረባችን በፊት በዚህ ጉዳይ ላይ የሚነሱትን ነጥቦች ሁሉ ለማዳመጥ እንፈልጋለን።
ኮት ዲቯር እንደገና ወደ እርስ በርስ ጦርነት ካመራች የምዕራብ አፍሪቃ አገሮች ፀጥታ እንዳይታመስ በተጨማሪ ያሠጋል።
ማሊና ቡርኪና ፋሶም በፖለቲካና ምጣኔ ሀብት ረገድ ስደተኞችን የማስተናገድ አቅም የላቸውም።
ባለፉት ጊዜያት ህግ ወጥ በሆነ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመግባት ከጣሩት ምዕራብ አፍሪቃውያን አብዛኞቹ ከኮት ዲቯርና አጎራባቾቿ የፈለሱ መሆናቸውም ይነገራል።
ዓለም የአፍሪቃ መሪዎችና የአፍሪቃ እዉነታ ከነገ በሕዋላ የአፍሪቃ መሪዎች አዲስ አበባ መጡ፥
የኢየሩሳሌም የወጣቶች ባንድ በመካከለኛው ምሥራቅ ሙስሊም ክርስትያን እና አይሁዳውያን አብረው ይዘፍናሉ ቢባል በአካባቢው ከሚካሄደው ጦርነት ጋር አብሮ ላይሄድልን ይችላል።
ምንም እንኳን ፈታኝ ቢሆንም ኢየሩሳሌም ዩዝ ኮር የሚባል አንድ የወጣቶች የሙዚቃ ቡድን ውስጥ የተወሰኑ ወጣቶች አብረው ይዘፍናሉ።
እስራኤል ውስጥ በወጣት ፍልስጤማውያን እና የእስራኤል ፖሊስ መካከል በተደጋጋሚ ግጭት ተስተውሏል።
ግጭቱ እንደ ኢየሩሳሌም ባሉ አንዳንድ የአምልኮ ስፍራዎች ሳይቀር ይካሄዳል።
ኢየሩሳሌም መፍትሄ ካጣችለት የአይሁድ ፍልስጤም ግጭት ጋር ስትታገል የሚቻ ሄንድለር የሙዚቃ ቡድን ግን የተሳካለት ይመስላል።
ወጣት አይሁዳውያን ክርስትያን እና ሙስሊሞች በሳምንት አንድ ቀን አብረው ሙዚቃ ለመጫወት ይገናኛሉ።
የሙዚቃ ቡድኑ መሪ ሄንድለር ከሶስት ዓመት በፊት ነው ይህንን ፕሮጀክት የጀመሩት።
ፍቅር የሚያገኙበት የተሰማቸውን የሚገልጹበት እና ደስታ የሚሰጣቸው ስፍራ ነዉ።
ወጣቶቹ ልምምድ ከመጀመራቸው አስቀድሞ ሄንድለር የድምፅ ቅላፄዎችን በምዕራብ እና በምሥራቁ ክፍል ስላለው የሙዚቃ የአተረጓጎም ልዩነት እና የመሳሰሉትን ለወጣቶቹ ያብራራሉ።
ይህም የሁሉንም ባህል እኩል ለማስተናገድ እንዲቻል አስፈላጊ ነው ይላሉ አሰልጣኙ።
ለምሳሌ ልክ እንደ ኢላይ ኤታን እና ሊሞር ኢላይ ኤታን እባላለሁ።
ኢላይ ኤታን እና ሊሞር ኢየሩሳሌም ውስጥ ላለው አስቸጋሪ ሁኔታ ማሳያ ሊሆኑ ይችላሉ።
ኢላይ ኤታን የምትኖርበት ፒስጋት ዜፍ ፍልስጤማውያን የሚኖሩበት አካባቢ ነው።
ስትወለድ እናቷን የረዷት ሀኪም እስራኤላዊ ስለነበሩ የሳቸውን የአይሁዳውያን ስም ሰጥተዋታል።
እስራኤል ምሥራቅ እየሩሳሌምን ከተቆጣጠረች አንስቶ በአካባቢው በተደጋጋሚ ግጭቶች ተከስተዋል።
የአል አቅሳ መስጊድ የሚገኝበት ስፍራ ለክርስቲያኖች ለሙስሊሞችም ይሁን ለአይሁዳውያን ሃይማኖታዊ ክብደት የሚሰጠው ስፍራ ነው።
ዛሬ በሚቻህ ሄንድለር የሙዚቃ አዳራሽ ለመጫወት የተሰበሰቡት ተማሪዎች ሙስሊም እና ክርስትያን ናቸው።
በአንድ በኩል ወጣት ፍልስጤማውያን በእስራኤላውያን ላይ ስለት ሲመዙ በሌላ በኩል ደግሞ የእስራኤል ፖሊስ ያለ ርህራሄ በፍልስጤማውያን ላይ ይተኩሳል።
ስለሆነም በከተማዋ ያለው ስሜት ልክ እንደ ፀጥታው ሁኔታ ያልተረጋጋ ነው።
አዲስ በተቀሰቀሰዉ ግጭት ምክንያት ነገሮች በእርግጥም ከባድ እንደሆኑ ግልፅ ነው።
አንዳንድ ጊዜም ወላጆች ልጆቻቸውን ለልምምድ ወደዚህ ሲልኩ ስጋት እንዳይሰማቸው ከነሱ ጋር በደንብ መወያየት አለብን።
ይህ ቦታ አስተማማኝ ሳይሆን ቀርቶ ሳይሆን ከቤትም ወደትምህርት ቤት ሄዶ ለመምጣትም ሁኔታው ለሁሉም አስተማማኝ ባለመሆኑ ነው።
ስለዚህ በሁለቱም ወገን ያሉ ወላጆች ልጆቻቸው ጨርሶ ምንም ነገር ለማድረግ ከቤት መውጣታቸው ያሰጋቸዋል።
ፍልስጤማዊቷ ሊሞርን ለምሳሌ የእስራኤል ጦር ፍልስጤማውያንን ሲያስር ወይም አንድ አይሁድ አንድ አረብን ሲገድል መመልከቱም ሆነ መስማቱ ያስጨንቃታል።
ምንም እንኳን በመጨረሻም ወጣቶቹ አንድ ላይ ተገናኝተዉ ቢዉሉም የሚያጋጥማቸዉ ችግር ግን ይለያያል።
ወጣቶቹ በህብረት ዘፍነው ሲጨርሱም አብዛኛውን ጊዜ አማካሪዎች ከነሱ ጋር ስለዉሏቸዉና ተሞክሮዋቸው ይወያያሉ።
የ ኢየሩሳሌም ዩዝ ኮር የሙዚቃ ቡድን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተጉዞም ዝግጅቱን አሳይቷል።