input
stringlengths
1
130k
ኒክሰን የማኦዋን ቻይና መጎብኘታቸዉን በዩናይትድ ስቴትስ የሚደገፉት የታይፔ የቶኪዮና የሶል መሪዎች አጥብቀዉ ተቃዉመዉት ነበር።
ጉብኝቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፖለቲከኞችን የፖለቲካ አዋቂዎችን ጋዜጠኞችንና ያኔ ብዙም የማይታወቁትን የመብት ተሟጋቾችንም በመደገፍና በመቃወም ለሁለት የገመሠ ነበር።
በ ኛ ዓመቱ ዘንድሮ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ሊያደርጉት ያቀዱት ጉብኝት በዓላማ በይዘት በክብደት ቅለትም ከኒክሰን ጋር በጭራሽ የሚስተካከል አይደለም።
ሁለቱ ጉብኝቶች በአላማ ይዘት ክብደት የመለያየታቸዉን ያክል አንድ የሚሆኑበት አንድ ምክንያት መኖሩ ሐቅ ነዉ።
ዘመን የማይሽረዉ ዓለም የሚያዉቀዉ እነሱም የሕዝብና የሐገር ብሔራዊ ጥቅም እያሉ የሚያንቆለጳጵሱት ዕዉነት።
እርግጥ ነዉ ኦባማ በያዝነዉ ወር ያደርጉታል የተባለዉ ጉብኝት አሜሪካኖችን ሊያከራክር ቀርቶ መሪዉ ጥንታዊቱን አፍሪቃዊት ሐገር እንደሚጎበኙ የሚያዉቀዉም ጥቂት ነዉ።
የሚያዉቁትም ያላወቁት ቢያዉቁትም የጉብኝቱ ዓላማ በትልቅቱ ሐገር የመርሕ መዘዉር ላይ የሚሾር መሆኑን እንደሚያዉቁት ለማወቅ ተንታኝ አያስፈልግም።
የታቀደዉ ጉብኝት ወትሮም አንድ ያልሆኑትን ኢትዮጵያዉያንን ግን እሁለት ገምሶ ለማነታረክ ለአደባባይ የተቃዉሞ ሰልፍ ለማሳደምም ትልቅ ርዕስ ነዉ።
ተወዛጋቢዎች ለየአቋማቸዉ ማስረገጪያ የሚያቀርቧቸዉ ምክንያቶች የመቃረናቸዉን ያክል የጉብኝቱ ዋና መሠረት አንድ መሆኑን እኩል ያዉቁታል።
ተከሳሾቹ አሉ እንደተባለዉ ፍርድ ቤቱን እንደ ፍትሕ ማዕከል ሳይሆን እንደ የመንግሥት ባለሥልጣናት ትዕዛዝ ፈፃሚ መቁጠራቸዉን አለመሸሻጋቸዉ እንጂ ክፋቱ።
ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ እንዳሉት ሆነም አልሆነ ተከሳሾች በአስር ቀን ዉስጥ የቅጣት ማቅለያ እንዲያቀርቡም ወስኗል።
በልማዱ የቅጣት ማቅለያዉን የሚያቀርቡት ወይም የሚያዘጋጁት የተከሳሾች ጠበቆች ናቸዉ።
የፍትሕ ሚንስቴር ባለሥልጣናትን መልስ እንዲሰጡ በተደጋጋሚ ሥልክ ብንደዉልም ልናገኛቸዉ አልቻልም።
በዚሕም ምክንያት መታሰር መከሰሷ እንጂ የታሰረችበት ትክክለኛ ምክንያት አይታወቅም።
እንደ እስራቱ ሁሉ መለቀቋ እንጂ የተለቀቀችበት ትክክለኛ ምክንያት አይታወቅም።
ከዓመት ከሰወስት ወር በፊት ከዘጠኝ ባልረቦቹ ጋር ድንገት ታሰረ።
ከአሸባሪዎች ጋር በመተባበር ወንጀል ተከስሶ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ሲጠብቅ ድንገት ክሱ ተሰርዟል አንተም ተለቀሐል አሉት።
የፌስ ቡክ ምፀተኞች ደግሞ ብዙ እስረኞች እንዲፈቱ ምናለ ኦባማ ኢትዮጵያን ደጋግመዉ ቢጎበኙ።
ለመብት ተማጋቹ ለያሬድ ሐይለማርም ግን ድንገት የመፍታቱ ዘመቻ ጥቅም የተሰላበት ግን የዘፈቀደ ፖለቲካዊ ዉሳኔ።
ኢትዮጵያ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጥረት በትራፊክ አደጋ በርካታ ሰዎች ከሚሞቱባቸው ሃገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት።
በኢትዮጵያ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ችግሩን ለመቀነስ ይረዳሉ ያሏቸውን ልዩ ልዩ ጥረቶች እያደረጉ ነው።
ከመካከላቸው በብሉምበርግ በጎ አድራጎት ድርጅት አስተባባሪነት በኢትዮጵያ የመንገድ ደህንነትን በማሻሻል ጤናማ ከተሞችን ለመገንባት የሚከናወነው ሥራ አንዱ ነው።
የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጥረት ለሰዎች ሞት እና የጤና ችግሮች ምክንያት ከሆኑት መካከል የመኪና አደጋዎች ተጠቃሽ ናቸው።
በየዓመቱ በትራፊክ አደጋ በርካታ ሰዎች ከሚሞቱባቸው ሃገራት አንዷ እና ግንባር ቀደምዋ ኢትዮጵያ ናት።
አደጋው አሳሳቢ በሆነባት በኢትዮጵያ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ችግሩን ለመቀነስ ይረዳሉ ያሏቸውን ልዩ ልዩ ጥረቶችን እያደረጉ ነው።
ሰሞኑን ከተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት የመጡ ባለሞያዎች በተለይ በአዲስ አበባ ችግሩን ለመከላከል የተከናወኑ ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ጉብኝቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቷል።
የማሻሻያ መርሐ ግብሩ ቢሊዮን ብር ገደማ ቢሊዮን ዶላር ይፈጃል
ዓለም የሳኻሮብ ሽልማት በዐረቡ ዓለም አምና ስለተቀሰቀሰው የዴሞክራሲ ጥያቄና የለውጥ ትግል በየጊዜው እስካሁን ብዙ በመጻፍ ላይ ነው።
የህዝብ ሰፊ አመጽ ረጅም ጊዜ በሥልጣን ላይ የቆዩ አምባገነን መሪዎች እንዲገረሰሱ አድርጓል።
ለውጥ ካስገኘው ከህዝባዊው ንቅናቄ በስተጀርባ አንዳንድ ለውጥ እንዲቀሰቀስ ያደረጉ አንዳንድ ግለሰቦች መወሳታቸው አልቀረም።
ከእነዚህም መካከል ቱ በዛሬው ዕለት እሽትራስቡርኽ ውስጥ በአውሮፓ ፓርላማ የሳኻሮቭ ሽልማት ተሰጥቶአቸዋል።
በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ እሽቴፋኒ ዱክሽታይን ያቀረበችውን ዘገባ ተክሌ የኋላ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።
የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት የርዚ ቡዜክ ባለፈው ጥቅምት የዘንድሮዎቹን የሳኻሮቭ ሽልማት አሸናፊዎች ሲያስታውቁ ልዩ ስሜት እንዳሳደረባቸው በድምጻቸው ይታወቅ ነበር።
የአውሮፓ ፓርላማ የዘንድሮውን ለመንፈስ ነጻነት የሳኻሮብን ሽልማት ለ የዐረቡ ዓለም የጸደይ ወቅት ተወካዮች ያቀርባል።
ቱኒሲያዊው የፍራፍሬና አትክልት ነጋዴ ሞሐመድ ቡዓዚዚ ገና የ ዓመት ወጣት ነበረ።
ድምፅ የተቃውሞ በ ኛው ሳምንትም ሞሀመድ ቡዓዚዚ ሀኪም ቤት ውስጥ ህይወቱ አለፈች።
ይሁን እንጂ ራሱን አቃጥሎ ህይወቱን ማሳለፉ በመላይቱ ቱኒሲያ የተቃውሞ ማዕበል ቀሰቀሰ።
በቱኒሲያ ብቻ ሳይሆን የተቃውሞው ማዕበል ወደ ሌሎቹ የዐረብ ሃገራት ተሸጋገረ።
የቀረጸችውን የቪዲዮ ፊልም በ ፌስቡክ ዓምድዋ ላይ እንዲታይ ለቀቀችው።
ወደ ታህሪር አደባባይ ብቅ በሉና እጅ ለእጅ ተያይዘን እንነሣ
ልባዊ የሆነውን የነጻነት ጥሪዋን የተገነዘቡ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ግብጻውያን ተቀበሉላት።
ማኅበራዊ ፍትኅ መሠረታዊ መብት የዴሞካራሲ ተኃድሶ ለውጥ ያቀረበቻቸው ጥያቄዎች ነበሩ።
በአሁኑ ጊዜ አስማ ማኅፉዝ ገደማ የፌስቡክ ደንበኞች ወይም ወዳጆች አሏት።
ግብጻዊቷ አስማ ማህፉዝ ዛሬ ሽልማት ስትቀበል ባሰማችው ንግግር እንዲህ ነበር ያለች።
በዚህ አገር የምኖርና ከአነርሱ መካከል አንዷ በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል።
የጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ሻልተር ሽታይንማየር በጋና ያካሄዱትን የሁለት ቀናት ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ጋምቢያ ገብተዋል።
የአምነስቲ መግለጫ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የጤፍ የባለቤትነት መብትን የማስመለስ ዘመቻ ይዘት ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
አሁን በለውጥ ሂደት ላይ በምትገኘው በኢትዮጵያ ባለፉት ወራት የሰብዓዊ መብት ይዞታ የመሻሻል አዝማሚያ እያሳየ ነው የሚሉ አስተያየቶች ይሰጣሉ።
በሰው ልጅ መገኛነትና በተለያዩ ቅርሶችዋ የምትታወቀው ጥንታዊቷ ሀገር ኢትዮጵያ እንደ እድሜዋ የሚያኮራ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ታሪክ የላትም።
ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በየዓመቱ በሚያወጧቸው ዘገባዎች በሀገሪቱ ይፈጸማሉ የሚባሉ የመብት ጥሰቶችን በዝርዝር ሲያሳውቁ ቆይተዋል።
የዛሬው እንወያይ በለውጡ ሂደት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኩራል።
የሕዋ ቴክኒዎሎጂ ብሔራዊ ፖሊሲ በኢትዮጵያ ኢትዮጵያ በ ዓም ጥቅምት ወር ላይ ሳተላይት እንደምታመጥቅ የኢትዮጵያ ሕዋ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ተቋም አስታወቀ።
ሊዲያ በፈረንሳይ የሚካሔደውን የዓለም ዋንጫ ለመዳኘት ከተመረጡ ሦስት አፍሪቃውያን መካከል አንዷ ናት።
ኢትዮጵያዊቷ የእግር ኳስ ጨዋታ ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ከስድስት ወር በኋላ ለሚካሔደው ለስምንተኛው የዓለም የሴቶች ዋንጫ ዝግጁ መሆኗን ለ ተናግራለች።
ኢትዮጵያውያኑ ጋዲሳ ሹሜ እና ባለው ደረሰ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነው አጠናቀዋል።
በዕለቱ የስፖርት መሰናዶ ከእነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች በተጨማሪ በሳምንቱ መገባደጃ የተካሔዱ የተለያዩ ጨዋታዎችን ይዳስሳል።
ባለፈው ሰኞ ህዳር ቀን በቤልጄየም መዲና ብራስልስ የተሰባሰቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የልማት ስብሰባ አካሂደው ነበር።
በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የሀሰተኛ ምስክር በዜጎች ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ እንደሆነ ነው የፍትህ አካላትና ነዋሪዎቹ የሚገልፁት፡፡
ችግሩ በክልሉ ምክር ቤት ጉባዔዎች ሳይቀር በተደጋጋሚ እየቀረበ ውይይት ቢደረግበትም መሻሻል እንዳልታየበት ነው የአነጋገርናቸው አካላት የሚናገሩት፡፡
የችግሩ የስፋት መጠን ሰፊ መሆኑን የሚናገሩት አቶ አማረ ይህን ለማወቅ ጥናት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
የደ ሱዳን የረሃብ አደጋና ስጋቱ በርስ በርስ ጦርነት በተመሰቃቀለችዉ ደቡብ ሱዳን ዉስጥ በሚሊዮኖች የሚገመቱ ዜጎች ለምግብ እጥረት መጋለጣቸዉ ተገለጸ።
የተመድ የዝናቡ ወቅት እየቀረበ በመጣበት በዚህ ወቅት ለእርሻ መዘጋጀት በማይታሰበብት ሁኔታ የገጠመዉ የምግብ እጥረት የከፋ ቀዉስ እንዳያስከትል አስጠንቅቋል።
ከታህሳስ ወር አንስቶም ከ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋ።
በተለያዩ አካባቢዎች ለሠፈሩ ወገኖች የምግብ ርዳታ ለማድረስም ዉጊያዉ እንቅፋት እንደሆነበትም ድርጅቱ ሲያመለክት ቆይቷል።
እናም ከዚህ ቀደም የምግብ እጥረት የመኖሩ እዉነታን በማሰብ በግጭቱ ምክንያት በርካቶች ከቤት ንብረታቸዉ ስለተፈናቀሉ ችግሩ የከፋ ሊሆን እንደሚችል በመገመት ነዉ።
በአሁኑ ጊዜም በብዛት ከዩጋንዳ ይመጣ የነበረዉ የምግብ አቅርቦትም የንግድ እንቅስቃሴዉ በመስተጓጎሎ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል።
አንድሩዉ አታ አሳሞሃ ችግሩ ሳይባባስ አሁን ባለበት ደረጃ የሚሰነዘረዉ ማሳሰቢያ አዎንታዊ ነዉ ይላሉ።
ዓለም ዓቀፉ ኅብረተሰብ ሊያደርገዉ የሚችለዉን አስመልክተዉ ደግሞ የማምረቱ ሂደት በተስተጓጎለበት በዚህ ወቅት ሊያደርጉ የሚችሉት የእርዳታ ጥሪ ማስተላለፍና አስቀድሞ ማቀድ ነዉ።
የተመድ ተቋማትም ደቡብ ሱዳን ዉስጥ ርዳታዉን ለማዳረስ ግፊት ያደርጋሉ።
እናም በዚህ ተግባር የሚሳተፉት ሁሉ ዝግጅት እንዲያደርጉ በበቂ ሁኔታ አስቀድሞ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ነዉ ብዬ አስባለሁ።
በዚህም ዓለም ዓቀፉ ኅብረተብ በመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት የሚታየዉን ችግር ለመቅረፍ አቅም እንዲኖረዉ ድጋፋቸዉን ሊሰጡ እንደሚገባም አመልክተዋል።
ለችግሩ መፈጠርና መባባስ ምክንያት የሆነዉ የቀጠለዉ የፖለቲካ ተቀናቃኝ ኃይሎች ዉጊያ መሆኑ ግልፅ ነዉ።
በእነዚህ ወገኖች መካከልም የተጀመረዉ የሰላምድ ድርድር በያዝነዉ ሳምንት ዳግም ተጀምሯል።
እስካሁን በተካሄደዉ ድርድር የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት ማለትም ሰላም ለማዉረድም ሆነ አዲሲቱን ሀገር ለማረጋጋት ያከናወነዉ እንዴት ይገመገማል
አንድሪዉ አታ አሳሞሃ ሂደቱን በሁለት ደረጃ ከፍለዉ ይመለከቱታል እስካሁን ያለዉን በሁለት ደረጃ ከፍሎ መመልከት ይቻላል።
የመጀመሪያዉ አካሄዱን ይመለከታል ተገቢዉን ሰዎች ይዘዋል ወይ የሚለዉ ነዉ።
በሁለተኛዉ የማየዉ ጥቅል መፍትሄዉን ነዉም ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት የሆነ ማዕቀፍ ማየት ነበረብን።
በአንድ ወገን ለዉጤት የሚጠቅሙ ሰዎች ይዟል በሌላ ወገን ደግሞ ዉሳኔዉን የማስፈፀም አቅም አይታይም።
እናም እንደጠንካራ የአካባቢዉ ቡድን ተዋናዮቹ የተስማሙበትን እንዲያከብሩ የመግፋት አቅሙን አልተጠቀመም።
ሆኖም ካምፓላ የፕሬዝደንት ሳልቫ ኪርን ለመደገፍ ጦሯን እዚያ ካሰማራች ሰንብታለች።
የካምፓላ ወታደራዊ ኃይል እዚያ መገኘት ድርጅቱ ሰላም ለማዉረድ የሚያካሂደዉን ጥረት የማደናቀፉ ሁኔታ እንዴት ይታያል
እዉነታዉ ዩጋንዳ ዉስጥ ቁልፍ ሚና አላት በዚያዉ መጠን ደግሞ በግልፅ በማጥቃት በኩል ወገን ይዛ የሳልቫኪርን አስተዳደር ለመታደግ ድጋፍ እየሰጠች ነዉ።
እናም እንደሚመስለኝ ይህ የ ን ሕጋዊነት ዝቅ የሚያደርግ ነዉ።
ምክንያቱም ከማን ወገን ነዉ በሚል ከ በኩል ጥያቄዎችን ያስነሳል።
የረጲ ኃይል ማመንጫ ግንባታ እየተጠናቀቀ ነው ስዊዲን ቆሻሻ ከሌሎች ሀገሮች ማስገባት ሁሉ ጀምራለች፡፡
ስዊዲን ሚሊዮን ከሚጠጋው ህዝቧ የሚሰበሰበውን በመቶ ቆሻሻ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ መልሳ ጥቅም ላይ ማዋሏ ነው የቆሻሻ ያለህ
የሀገሪቱ ይፋዊ ድረ ገጽ እንደሚጠቁመው ከየቤቱ ከሚሰበሰበው ቆሻሻ ውስጥ በመቶው ለኃይል ማመንጫነት ይውላል፡፡
በስዊዲን ቆሻሻን በማንደድ ሙቀት እና የኤሌክትሪክ ኃይልን የሚያመነጩ ተቋማት አሉ፡፡
አውሮፓዊቷ ሀገር የመጀመሪያውን እንዲህ አይነት ተቋም በዋና ከተማይቱ ስቶኮሆልም ያቋቋመችው እንደጎርጎሮሳዊው በ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ከስዊዲን አንድ ምዕት አመት ዘግይታም ቢሆን መንገዱን ተያይዛዋለች፡፡
ከቆሻሻ ኃይል የሚያመነጭ ተቋም ለመገንባት ግንባታ ከጀመረች ሶስት ዓመት አለፋት፡፡
ቦታው ደግሞ የመጋቢት ሁለቱ አስደንጋጩ አደጋ ከደረሰበት አቅራቢያ ነው፡፡
በዚያ አዲስ አበባ በ ዓ ም ለደረቅ ቆሻሻ መጣያነት ስራ ያስጀመረችው የቆሻሻ መድፊያ ከእነ ክምር ቆሻሻው አለ፡፡
ረጲ የደረቅ ቆሻሻ ማመንጫ የተሰኘው አዲሱ ፕሮጀክት ግንባታው ወደ መገባደዱ ቢቃረብም ይህን ለዓመታት የተከማቸ ቆሻሻ ወደ ኃይል የሚለወጥ አይደለም፡፡
ይልቅስ ከአዲስ አበባ በየቀኑ ከሚሰበሰበው ወደ ሁለት ሚሊዮን ኪሎግራም ቆሻሻ ውስጥ በመቶውን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል የመቀየር እቅድ ያለው ነው፡፡
አቶ ሳሙኤል አለማየሁ የኃይል ማመንጫውን በመገንባት ላይ ያለው የካምብሪጅ ኢንዱስትሪስ የአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ናቸው፡፡
ቆሻሻዎቹን በደንብ አድርገን ውሃቸው ጠልሎ እንዲወጣ ካደረግን በኋላ ወደ ማንደጃ ውስጥ እንከታቸዋለን፡፡
ቆሻሻው እነዚህ ማንደጃዎች ውስጥ በ ዲግሪ ሴንትግሬድ ላይ ነው የሚነደው፡፡